TIKVAH-ETHIOPIA
" ኑሮ ውድነቱ መፍትሄ ይሻል። መፍትሄ እንሻለን " - የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የስራ ግብር እንዲቀነስ ፤ የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ከኑሮ ውድነቱ አንፃር የዘገየው የሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እና የግብር ቅነሳ…
#ሜይዴይ
“ ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛው ሊቋቋመው አልቻለም ” - አቶ ካሳሁን ፎሎ
ዛሬ የሜይዴይ በዓል እየተከበረ ነው።
በዓሉ አስመልክቶ ትላንት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ተገኝቶ ነበር።
ኮንፌዴሬሽኑ ፤ በባለፈው ዓመት በተከለከለው ሰልፍ ሳቢያ ከመንግሥት ጋር የገጠማችሁ አለመግባባት ተፈታ ? የሠራተኞች ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ አሁንስ ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል።
የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ “ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው ክልከላው ደርሶን የነበረው። በመነጋገር መፍታት አልቻልንም በወቅቱ ” ብለዋል።
“ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደተከለከልን ከመንግሥት አካላት ጋር በየደረጃው ተወያይተናል። ክልከላው ሆን ተብሎ ሠራተኛው ያለውን ጥያቄ እንዳያቀርብ የተደረገ እንዳልነበር ተግባብተናል ” ሲሉ ገልጸዋል።
“ ከዚያም ጥያቄያችንን አደራጅተን ለጠ / ሚኒስትሩ አቅርበን ግብር እንዲቀነስ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ስኬል እንዲወሰን መጠየቃችን ይታወቃል። ጠ/ሚኒስትሩ በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ እንደሚሰጥ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ያኔ ” ሲሉ አስታውሰዋል።
“ አቅጣጫ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች እየተከታተልን ነው ” ያሉት አቶ ካሳሁን ፣ “ ነገር ግን አቅጣጫ የተሰጠባቸው የኑሮ ውድነቱን የተመለከቱ ጥያቄዎች ምላሽ አሁንም ዘግይቷል። ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛውም ሊቋቋመው አልቻለም ” ብለዋል።
አሁን ምን አዲስ ነገር አለ ? ለሚለው ፦
➡️ ከሠራተኛው በነጻ መደራጀት ጋር በተያያዘ ለሁሉት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው መንግስትና ሠራተኛ ቁጭ ብለው የሚወያዩበት የአሰሪና ሠራተኛ አማካሪ ቦርድ ዘንድሮ ሥራ ጀምሯል፡
➡️ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሁሉም ክልሎች ሠራተኛ እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች በሚገኙበት ስብሰባ ግምገማ ማካሄድ ተጀምሯል ጥያቄዎች በዚሁ አካሄድ ይፈታሉ ሲሉ አስረድተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia