#ሜትርታክሲ #ሀይገርባስ
ገቢዎች ሚኒስቴር ስለ ሀይገር ባስ እና ሜትር ታክሲዎች ምን አለ ?
የገቢዎች ሚኒስቴር ፤ የሀይገር ባስ እና የሜትር ታክሲዎች የታክስ አከፋፈል ስርዓት ውሳኔ ሳያገኝ በእንጥልጥል ቆይቷል ብሏል።
ነገር ግን ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ በንግድና በታክስ ህጉ መሠረት ተፈጻሚ መደረግ እንዳለበት ተገልጾ ከገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ እንደተሰጠበት ገልጿል።
በዚህም ፦
1ኛ. የታክሲ ማህበራት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 17 መሰረት የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚጠበቅባቸው የደረጃ " ሀ " ታክስ ከፋዮች በመሆናቸው የሂሳብ መዝገብ ይዘው የሚጠበቅባቸውን ግብር አስታውቀው እንዲከፍሉ፤
2ኛ. ዓመታዊ ግብራቸውን በሂሳብ መዝገብ ካላቀረቡ በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 እና በመመሪያ ቁጥር 138/2010 በትራንስፖርት ቁርጥ ግብር ስርአት መሰረት አመታዊ የገቢ መረጃ እየተወሰደ እንደ ድርጅት በተሸከርካሪዎቹ ዓይነትና ምርት ዘመን ግብር በሚከፈልበት ገቢ ላይ 👉 30 በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር በግምት እንዲሰላና መዝገብ ባለመያዝ በህጉ መሰረት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጠየቁ፤
3ኛ. የአክሲዮን ማህበራት በንግድ ህጉ መሠረት ለአባላት የሚከፈለው የትርፍ ድርሻ (Dividend) ግብር የሚከፈልበት ስለሆነ የሂሳብ መዝገብ ካልያዙ አመታዊ የተጣራ ትርፍ ላይ ወይም በቁርጥ ግብር የገቢ መጠን ተመስርቶ የንግድ ትርፍ ግብር ከተከፈለ ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ የተከፈለው ግብር ተቀንሶ ቀሪው መጠን ላይ ህጉን ተከትለው ካፒታላቸውን እስካላሳደጉ ድረስ የትርፍ ድርሻ ግብር 👉 10 በመቶ እንዲከፍሉ እንዲደረግ እንደተወሰነ ለግብር ከፋይ የሀይገር ባስና ሜትር ታክሲ ባለንብረቶች አሳውቋል።
@tikvahethiopia

😡397❤189👏51😭51🙏37🕊31😱25😢22🥰9