TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሀሳብ ማዕድ!

#ማዳመጥ #መረዳት #መናገር #መግባባት

በዓለማቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አዘጋጅነት የሚካሄደው ሁለተኛው የአክቲቪስቶች የውይይት መድረክ በቀነኒሳ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የሚዲያ ባለሞያዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በውይይቱ መጀመሪያ ላይ አዘጋጁ እንደተናገረው ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችና አክቲቪስቶችን አቀራርቦ ማወያየት የዝግጅቱ ዋነኛ ዓላማ ነው፡፡ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር አደረ አብደላ እንደገለጹት በአክቲቪስቶች መካከል በመደማመጥ ላይ ያተኮረ ሁሉም ሃሳቡን በእኩል ማካፈልና ከተቻለ የጋራ መግባባትን መፍጠር ካልሆነም ልዩነቶችን አቻችሎ ለሀገር ደህንነትና ሰላም በጋራ መቆም ይኖረባቸዋል ብለዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሌሎች እንዲያደምጡን ብቻ ሳይሆን እኛም ሌሎችን ማድመጥ የምንችልበትን መድረክ ማመቻቸት የዚህ ዓላማ ዋነኛው ዓለማ ነው በማለት አክለው ገልጸዋል፡፡ ፕሮግራሙ አካታች ለማድረግ ጥረት የተደረገ ሲሆን በዚህ ውይይት 12 አክቲቪስቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በመድረኩ የሚነሱ ሃሳቦችን እየተከታተልን እናሳውቃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia