TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጫሞ በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ ላይ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች፤ ባጋጠማቸው የማዕበል አደጋ ምክንያት ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ። " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ትላንት ቅዳሜ ከሰዓት ለኃላ ነው። ባለሞተር ጀልባው የአማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ ቀበሌ ነዋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው…
" ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው ተሟጧል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ

የደቡብ ፖሊስ ትላንትና በ #ጫሞ_ሐይቅ ላይ ለሰመጠችው ጀልባ መንስኤው ከመጠን በላይ መጫን እና ባልተለመደ ሁኔታ የተከሰተ ማዕበል ነው ብሏል።

የዞን ፖሊስ በበኩሉ ጀልባዋ ከሥምንቱ ሰዎች በተጨማሪ #ሙዝ እና #ዕቃ መጫኗን አሳውቋል።

የሕይወት አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያለው ፖሊስ ለዚህም የተለያዩ ጀልባዎችና ዋናተኞች ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

በተከናወነው የፍለጋ ሥራ ከጫማዎች እና የተለያዩ አልባሳት ባለፈ የተገኘ ነገር እንደሌለ ተገልጿል።

የአማሮ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል እስካሁን ድረስ በሕይወት የተገኘ አለመኖሩን ጠቁመዋል።

ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው መሟጠጡንም ቢሮው ገልጿል።

(ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopia
😢1.96K👍567109😱59🙏39🕊31🤔22🥰18👎1😭1