TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ንግሥት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አሥፈፃሚነት ራሷን #አገለለች። በደብረብርሀን እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ የ2012 እቅድ አፈፃፀም ድምፅ ሊሰጥ ሲቃረብ ደራርቱ" በቃኝ ከፍተኛ #መገለል እየደረሠብኝ ነው። ወደዚህ ጉባኤ እንኳን ስመጣ በግል እንጅ እንደሌላው ምንም መጥሪያ አልደረሠኝም ብላለች። ሁላችሁንም እወዳችኋላሁ ያለችው ደራርቱ ሥፖርቱ እንዲያድግና የሀይሌ ራእይ እንዲቀጥል ነው ፍላጎቴ አሁን ግን ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አሥፈፃሚነት ይበቃኛል በማለት ተናግራለች።

ዶ/ር አሸብር በበኩላቸው ያለደራርቱ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ማሠብ ከባድ ነው ጉዳዩን ቁጭ ብለን እንፈታዋለን ብለዋል። ደራርቱ የተከፋችበት ጉባኤ መሆኑ አሳዝኖናል ደራርቱ ትመለሳለች፤ ትመለሳለች፤ ትመለሳለች ሲሉም ተናግረዋል። ቀጣዩ የ2012 ጠቅላላ ጉባኤ ትግራይ የ2013 ደግሞ አማራ ክልል እንዲያዘጋጁ ተወሥኗል። ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክሥ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት ሥትሆን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ አባል ነች።

Via ግርማቸው እንየው/ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8/
@tsegabwolde @tikvahethiopia