TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰኔ 15 ጦር ሀይሎች አካባቢ ምን ተከሰተ?
/ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

ሰኔ 15 ቀን አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ አካባቢ የተከሰተው ግርግር እና ግድያ ብዙ ትኩረት ቢስብም #ጦር_ሀይሎች በተለምዶ ሲግናል (በድሮ አጠራሩ #መኮ) የተከሰተው ሁነት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ቢያንስ ሶስት ምንጮች አረጋገጡልኝ እንዳለው ጦር ሀይሎች አካባቢ በነበረው ግጭት ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። እስከ ለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር። ይህ ክስተት በእለቱ ከነበሩት ሌሎች ግድያዎች ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

በቅርቡ ስለ ጉዳዩ በAPው ጋዜጠኛ የተጠየቁ አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ "ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም። አጣርቼ መልስ ልሰጥህ እሞክራለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ አለኝ ያለ አንድ ግለሰብ ለጋዜጠኛው ተከታዩን መረጃ አቀብሎ ነበር፦

"ስለ ሰኔ 15ቱ (የጦር ሀይሎች አካባቢ ጉዳይ) የተወሰነ መረጃ አለኝ። መረጃውን ላገኝ የቻልኩት ደግሞ በዛ ምሽት ከሞቱት ሶስት የፌዴራል ኮማንዶዎች አንዱ የአክስቴ ልጅ ስለነበር ሬሳ ለመቀበል ከቤተሰብ ጋር በሄድንበት ጊዜ የአሟሟቱ ጉዳይ ስለተነገር ነው። እናም ጉዳዩ ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረ አንድ ኮሎኔል ለመያዝ በሄዱበት ጊዜ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነው። ግን እስካሁን አንድ የመንግሥት አካል ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር አለማለታቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል።"

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia