TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኬንያ በደረሰ የሄሊኮፕተር #መከስከስ አደጋ የ4 አሜሪካዊ ቱሪስቶች ህይዎት አለፈ። አደጋው የደረሰውም በትናንትናው ዕለት በሰሜን ኬንያ ግዛት አካባቢ አሜሪካዊ ቱሪስቶችን አሳፍራ ትጓዝ በነበረች ሄሊኮፕተር ላይ ነው ተብሏል። በሄሊኮፕሯ ላይ በደረሰ የመከስከስ አደጋም አብራሪውን ጨምሮ የ5 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ነው የተገለፀው። የአደጋው መንስኤ  እስካሁን አለመታወቁም በዘገባው ተመላክቷል።

ምንጭ ፦አናዶሉ(fbc)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የበረራ አስተናጋጇ አያንቱ🔝

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን #መከስከስ ሕይወቷን ያጣችው የ24 ዓመቷ የበረራ አስተናጋጅ #አያንቱ_ግርማ አባት አቶ #ግርማ_ሌሊሳ ልጃቸው በአየር መንገዱ መሥራት ከጀመረች ሁለት ዓመታት ማስቆጠሯን ገልጸው፣ አስከሬን አይተው ካልቀበሩ በስተቀረ ማመን እንዳልቻሉ ይናገራሉ፡፡ አደጋው መከሰቱን በሚዲያ የሰሙ ሰዎች በስልክ እንደነገሯቸው የገለጹት አቶ ግርማ፣ ልጃቸው በግንቦት ወር 25ኛ ዓመቷን ትይዝ ነበር ሲሉም #በሀዘን ተናግረዋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውሮፕላን ተከሰከሰ👆

በጅማ ዞን ኦሞ ቤየም ወረዳ በአቢሲኒያ ፍላይት መለማጀማ አውሮፕላን ላይ #መከስከስ አደጋ መድረሱ ተገለፀ። የአቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስ የፕሮጀክት ማናጀር አቶ #አሸናፊ_ፀጋዬ ለfbc እንዳስታወቁት፥ አደጋው በዛሬው እለት ጠዋት ላይ ጎና ቤየም በሚባል ቀበሌ አሰንዳቦ አካባቢ ነው የደረሰው።

በአውሮፕላኑ ላይ የመከስከስ አደጋው የደረሰው አንድ ተለማማጅ የአውሮፕላን አብራሪ በማብረር ላይ እያለ መሆኑንም አስታውቀዋል። የመከስከስ አደጋው የደረሰበት አውሮፕላን “C 172” ሞዴል ሲሆን፥ አራት መቀመጫዎች ያሉት ነው ብለዋል አቶ አሸናፊ።

በአሁኑ ወቅትም የአደጋውን የጉዳት መጠን እና #መንስኤ ለማጣራት የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም አስታውቀዋል። ወደ ስፍራው የተጓዘው የባለሙያዎች ቡድን ወስጥም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የፍለጋ እና የነብስ አድን ሰራተኞች እና የአቢሲኒያ ፍላይት የደህንነት አባላት የተካተቱበት ነው።

የአደጋው መንስኤም እስካሁን አለመታወቁን እና በመጣራት ላይ መሆኑንም የአቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስ የፕሮጀክት ማናጀር አቶ አሸናፊ ፀጋዬ ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia