ዛላምበሳ‼️
ባለፈው የመስከረም ወር የተከፈተው የዛላምበሳ ድንበር ባልታወቀ ምክንያት ከፌደራል መንግሥት ፍቃድ ለሌላቸው ተጓዦች #መከልከሉን የጉሎመኸዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረህይወት ገብረየሱስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ድንበር በኩል "ከፌደራል መንግሥት ፈቃድ መያዝ አለባችሁ" የሚል ምላሽ እንተደተሰጣቸውና ከኤርትራ በኩል ደግሞ የይለፍ ወረቀት እየተዘጋጀ መሆኑን" ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚመላለሱ መንገደኞች ያለችግር ገብተው መውጣት ይፈቀድላቸው ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ያለ ይለፍ ወረቀት ከሁለቱም በኩል መንቀሳቀስ አይችልም።
በተጨማሪም በኤርትራ በኩልም ድንበር ጥበቃውን እንዲያጠናክሩ በድንበር ጥበቃ ላይ ለተሰማሩ ከላይ መመሪያ እንደተሰጣቸውም ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ ከኤርትራ መንግሥት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
Via BBC Amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ " በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይቻል ይታወቅ " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቢከለከልም " ይሄን አልሰማንም " ያሉ ሰዎች የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ገዝተው ወደ ሀገር እያመጡ ይገኛሉ ተብሏል። ይህ የተሰማው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች…
#ኢትዮጵያ
ገንዘብ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ #አለመከልከሉን ገለጸ።
ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢል እንዳይገቡ #መከልከሉን ማሳወቁ አይዘነጋም።
የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህግ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ ምን አሉ ?
- በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በመከልከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ የሚፈቅድ ምንም አይነት መመሪያም ሆነ ውሳኔ የለም።
- ገንዘብ ሚኒስቴር እያከናወነ ያለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማበረታታት እና በነዳጅ የሚሰሩ በብዛት እንዳይገቡ ተስፋ ለማስቆረጥ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ የተደነገገበት ሁኔታ አለ።
- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማገድ በዓለም የንግድ ድርጅት ህግ መሰረት የማይቻል በመሆኑ የሀገሪቱን የቀረጥ ስርዓት በመጠቀም ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቀሙትን ማበረታታት ጎጂ የሆኑትን እንዳይስፋፉ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው።
- በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ለፓርላማ ስለቀረበው ጉዳይ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።
- ገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንዲገቡ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ተደርጓል። አዋጁ፦
* ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው ለሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች 5% ኤክሳይዝ ታክስ
* ተበታትነው ገብተው ሀገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚያስችል ነው።
* በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንደሚጠቀሙት የነዳጅ መጠን 10% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተደርጓል።
- የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ነጋዴዎች ተግባራዊ ማድረግ የሚጀምሩት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት 38 የተለያዩ ምርቶች ከባንክ ፍቃድ /letter of credit/ እንዳይከፈትላቸው የሚከለክለው እገዳ ከተነሳ በኃላ ነው።
- በአሁን ወቅት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ያሉት ተሽከርካሪዎች ክልከላው ከመደረጉ በፊት ተከፍቶ በነበረ LC እንጂ በልዩ ሁኔታ ተፈቅዶላቸው የሚያስገቡ ነጋዴዎች የሉም።
- የLC እገዳው ካልተነሳ በስተቀር ለንግድ ወይም ለመንግሥት መስሪያ ቤት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች በገንዘብ ሚኒስቴር እውቅና ብቻ አይገቡም። ክልከላው የማይመለከታቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ቢሆኑም በነዳጅ የሚሰራ ተሽከርካሪ በሚያስገቡበት ጊዜ በኤክሳይዝ ታክስ ተስተናግደው ነው።
ይህ የገንዘብ ሚኒስቴር አስተያየት በተመለከተ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ኃላፊ እገዳው በመመሪያ / በውሳኔ የተገለፀ አይደለም ብለዋል።
ግን ሁሉም የሚመለከታቸው መ/ቤቶች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በ100 ቀናት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በተደረገ ግምገማ በተሰጠው አቅጣጫ በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎች እንዳይገቡ መከልከሉን ገልጸዋል።
አንድ የጉምሩክ ኮሚሽን ኃላፊ ደግሞ በአሁን ወቅት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው በብሄራዊ ባንክ የወጣው ውሳኔ ላይ በመሆኑ ውሳኔው በተዘዋዋሪ በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ የተከለከለው አሁን አዲስ በተሰጠ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ብቻ አይደለም ብለዋል።
ብሄራዊ ባንክ ጥቅምት 4/2015 ይፋ እንዳደረገው ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ የተደረገባቸው 38 ምርቶች ውስጥ ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል። ከሞተር ነክ ምርቶች የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የተካተቱ ሲሆን እገዳው በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን እንደማያካት ይታወቃል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/reporter-01-31
ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።
@tikvahethiopia