TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጄነራሉ ምን አሉ ?

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ለመከላከያ ሰራዊት ቴሌቪዥን ፕሮግራም ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል።

ይኸው ቃለመጠይቃቸው ዛሬ ለህዝብ ተሰራጭቷል።

ጄነራሉ ምን አሉ ? በተለይም ስለ ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ጉዳይ ምን ሃሳቦችን አንስተው ተናገሩ ?

ጄነራል አበባው ታደሰ ፦

- መላ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን የምንፈልገው በሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል እንዲገነባ ህገመንግስቱ የሚፈቅደው #መከላከያ_ሰራዊትና #ፌዴራል_ፖሊስን ነው።

- በየክልሉ ያለው ልዩ ኃይል በሳይዙ ልክ አለው ፤ በሌላ አነጋገር ሀገር በሚመስል ደረጃ 14 እና 15 ሬንጀር አለው ይሄ ፈፅሞ አይቻልም።

- አሁን ያለው የክልል ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት ስራ ዛሬ የተጀመረ / በሞራል የተገባበት ሳይሆን ከዚህ ቀደም ለረጅም ጊዜ ጥናት ተደርጎበት ነው።

- የክልል ልዩ ኃይሎች ፦ የክልልን ፀጥታን ይጠብቁ ነበር ፣ ከእኛ (ከመከላከያ) ጋር ሆነው ይሞቱ ነበር ህይወታቸውን አሳልፈዋል ፣ ቆስለዋል ደምተዋል። ይሄ ኃይል ይሄን የመሰለ ትልቅ ኳሊቲ ነበረው።

- ከህገመንግስት አንፃር ስናየው እነዚህ ኃይሎች ህጋዊ አይደሉም ህገመንግስቱ እውቅና አይሰጣቸውም። ለክልል ኃይል የሚሰጠው መደበኛ ፖሊስን ብቻ ነው። ህገመንግስቱ የታጠቀ ኃይል የሚያውቀው አንደኛ መከላከያ፣ ሁለተኛ ፌዴራል ፖሊስ፣ ሶስተኛ መደበኛ ፖሊስ ነው ከዚህ ውጭ ህገመንግስቱ አይልም።

- የኃይል አገነባቡ (የልዩ ኃይል መዋቅር) ብሔር ተኮር ነው ፤ ለኦሮሞ ህዝብ እሞታለሁ ብሎ ቃል ይገባል አማራውስ ? ጉዳዩ አይደለም ማለት ነው በግልፅ አማርኛ ፤ አማራው ደግሞ ይመጣና ለአማራ ህዝብ እሞታለሁ ይላል ኦሮሞውስ ? ጉዳዩ አይደለም ። ብሄር ተኮር ስለሆነ ሀገር አቀፍ የሆነውን አብሮነት የመኖር ፤ የህዝቦችን አንድነት ይሸረሽረዋል።

- የክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ፕሮግራም ወደ መከላከያ ሰራዊት ማስገባት፣ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ማስገባት፣ ወደ መደበኛ ፖሊስ ማስገባት ነው። በማን በራሱ ምርጫ፣ በምን ? ክብሩን ሞራሉን ፣ ጥቅሙን በማይነካ ሁኔታ።

- አፈፃፀሙ በተመለከተ ሁሉንም እኩል እደራጀዋለን ፣ በጥንቃቄም ይሰራል።

- አንደኛውን ክልል ኃይል እንዲኖረው ሌላውን ክልል ኃይል እንዳይኖረው አናድረግም። ይሄ ኢትዮጵያ ውስጥ አይታሰብም።

- የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ለምሳሌ የትግራይ የትግራይ ክልል እንደማንኛውም ክልል መደበኛ ፖሊስ ብቻ ነው የሚኖረው ፣ የታጠቀ ልዩ ኃይል የሚባል በፍፁም አይኖረውም።

- በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢና ዩኒቶች ካልሆነ በስተቀር አማራ ልዩ ኃይል የሚባለው በአብዛኛው ተቀብሎታል ፤ ይሄ በኮሚኒኬሽን ያለ ችግር ነው ይሄን የኮሚኒኬሽን ችግር እየፈታን ነው ያለነው። አፈፃፀሙ ላይ የታየው ጉድለት ይሄ ነው እንዲህ አይነት ነገር ሊኖር እንደሚችል እንጠብቃለን አስበንም ነው የገባነው። ከዛ  ውጭ ባወጣነው ፕሮግራም መሰረት ይሄን ኃይል ወደምንለው ፕሮግራም እናስገባዋለን ሁሉንም እኩል አድርገን።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-07