TIKVAH-ETHIOPIA
" ... በከተማው የንጥቂያ እና ዝርፊያ ወንጀሎች #መባባስ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ እያስነሳ ነው " - የጋምቤላ ፖሊስ በጋምቤላ ከተማ በሞተር ሳይክሎች ላይ የሰዓት ገደብ ተጣለ። በጋምቤላ ከተማ በተሽከርካሪ የሚፈፀም ስርቆትና ዝርፊያን ለመከላከል ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች ላይ እገዳ መጣሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ…
በወንጀል ድርጊት የተማረሩት ነዋሪዎች . . .
በጋምቤላ ከተማ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መፍትሄ ያገኙ ዘንድ በጋምቤላ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠየቁ።
አንድ ነዋሪነቱ በጋምቤላ ከተማ የሆነ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ በከተማው ማታ እንዲሁም በቀን ሳይቀር ዘረፋና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች መበራከቱን ገልጸው የጋምቤላ ክልል መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
" ቀን ላይ እንኳ ከዋናው አስፓልት በቀር አብዛኞቹ ቦታዎች ላይ ሰው ብቻውን ለመሄድ እስከሚሰጋ ድረስ ነው ወንጀል የተበራከተው " ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
ሌላ የጋምቤላ ቲክቫህ አባል ፤ በከተማው የወንጀል ድርጊት እጅግ መስፋፋቱን በመግለፅ እንደ ከዚህ ቀደሙ በነፃነት ወጥቶ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ሆኗል ሲል ገልጿል። በመሆኑም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የከተማው ደህንነት እንዲጠበቅ ማድረግ ይገባል ሲል አስገንዝቧል።
ሌሎችም የቤተሰቦቻችን አባላት በከተማ ዝርፊያ፣ ንጥቂያ እና ሌሎችም ወንጀሎች መስፋፋታቸውን በመጠቆም አስቸኳይ እና አስተማማኝ መፍትሄ እንዲበጅ ጥሪ አቅርበዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት የጋምቤላ ፖሊስ ፤ በጋምቤላ ከተማ የንጥቂያና ዝርፊያ ወንጀሎች #መባባሱንና ይህም በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ እያስነሳ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።
በተለይ በተሽከርካሪ የሚፈፀም ስርቆትና ዝርፊያን ለመከላከልም ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች ላይ እገዳ ጥሏል።
እንደ ፖሊስ መረጃ በከተማዋ እየተስፋፋ በመጣው የዝርፊያና መሰል ወንጀሎች በዋናነት ተጠቂዎቹ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ናቸው።
Via @tikvah_eth_BOT
@tikvahethiopia