TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መቄዶንያ የረሱላችንን (ሰ · ዐ · ወ) ውዴታ የምናሳይበት ትልቁ መንገዳች ሰደቃችን ነው። ኑ! እነኚህን የስው ፍቅር የተጠሙ አረጋዊያንን በዚህ ቀን አብረናቸው። በመሆን አለንላቹ እንበላቸው።

ማክሰኞ ከ 9 ሰአት ጀምሮ
#በመቄዶንያ_የአረጋዊያን_
#መቄዶንያ

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ዘመናዊ ሆስፒታል እና የአረጋውያን መኖሪያ ህንፃ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል።

አሁን ላይ ግንባታው በፎቶው የምትመለከቱት ደረጃ ላይ ደርሷል።

ይህ ህንፃ ሃምሳ በመቶ (50 %) የደረሰ ሲሆን ማህበሩ የህንፃውን ግንባታ ማጠናቀቀ እንዲችል ጠጠር፣ አሻዋ፣ ሲሚንቶ፣ ቁርጥራጭ ብርት፣ የፊኒሽንግ ቁሳቁሶችን እንደሚያስፈልጉት ለዚህም የሁሉም እገዛ እንደሚያስፈልገው አሳውቋል።

8161 ላይ " OK " ብሎ በመፃፍ ለተጀመረው ህንፃ ግንባታ የበኩልዎን አስተዋፅዎ ማድረግ እንደሚቻል ሜቄዶኒያ ገልጿል። ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ደግሞ በ 0979797979 መደወል ይቻላል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#መቄዶንያ❤️

🔵 “ የጎዳና ኑሮ ከባድ ነው፣ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ” - የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ

🔴 “ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል ” - ቀሲስ ታጋይ ታደለ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኀበር ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ በመቄዶንያን ቅጥር ግቢ ውስጥ አረጋዊያን በተገኙበት ዛሬ የጸሎት መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ነበር።

ጸሎቱን የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ሁሉም በዬእምነታቸው መርሀ ግብሩን በጸሎት አስጀምረው፣ የጸሎት መርሀ ግብሩ ተከናውኗል።

የጸሎት ፕሮግራሙ ዓላማ አረጋዊያንን ጋር ተኩኖ ቢጸለይ ፈጣሪ ሰላሙን፣ ፍቅሩን እንደሚሰጥ በማሰብ እንዲሁም የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በሚደረገው ለመቄዶንያ ርዳታ የማሰባሰብ መርሃ ግብር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ርብርብ ያደርጉ ጥሪ ለማቅረብ ነው።

የመቄዶንያ መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ምን አሉ?

“ እንደሚታወቀው መቄዶኒያ የዘር፣ የሃይማኖት፣ የጾታ ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ነው የሚረዳው።

ሁሉም የእምነት ተከታዮች በመቄዶንያ አሉ።
መቄዶንያ ውስጥ ፕሮቴስታንቶች፣ ሙስሊሞች፣ ኦሮቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች አሉ።

እንዲያውም የሚጠበቅብን ምግብ፣ ልብስ መጠለያ ማሟላት ነው። ነገር ግን ከሚጠበቅበት በላይ ድርጅቱ መንፈሳዊ ፍላጎቶችንም ጭምር እያሟላ ይገኛል።

ዛሬ ስለመጣችሁ በጣም ደስ ብሎናል ምክንያቱም ሁሉም የሃይማኖት ተከታዮች እዚህ ስላሉ እናንተን ሲያዩ በጣም ደስ ይላቸዋል። ወደፊትም በሚመቻችሁ ጊዜ እንደዚሁ እየመጣችሁ ብትጎበኙን በጣም ደስ ይለናል።
 
በአሁኑ ወቅት በጣም በርካታ ሰዎች እየረዳን እንገኛለን። 5 ወለል ያለው ህንጻ እየገነባን እንገኛለን። በክልሎችም እንደዚሁ በተለያዩ ቦታዎች ግንባታዎች እየተፋጠኑ ይገኛሉ።

ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ኮንሶ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋና ሌሎችም ቦታዎች
መቄዶንያ አለ። በተለይ ደግሞ እኛ የምንረዳቸው የአልጋ ቁራኛ፣ የጎዳና ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን ነው። 

የጎዳና ኑሮ በጣም ከባድ ነው፣ የሚገርማችሁ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው እዚህ የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ። ብርድ የመታቸው ሰዎች ወደ ህክምና የሚወስዳቸው የለም ”
ብለዋል።

በመሆኑም የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በሚደረገው ዓለም አቀፍ ገቢ የማሰባሰብ መርሀ ግብር፣ ሁሉም አካላት ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ በ8,000 አረጋዊያን ስም ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ መርሀ ግብሩ የተዘጋጀው ከአረጋዊያኑ ጋር ቢጸለይ ፈጣሪ ጸሎት ይሰማን ተብሎ ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።

ቀሲስ ታጋይ ምን አሉ ?

“ ዛሬ በመቄዶንያ የተገኘነው ሁለት ጉዳዮችን መሠረት አድርገን ነው። አንደኛው ጸሎት ለማድረግ ነው። 

በአገር ሰላም ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የድርሻቸውን እንዲወጡ በማሰብ ጸሎት ማድረግና የሰላም ጥሪ የቀረበላቸው ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመለሱ አስቸኳይ ሁኔታ ለመፍጠር የተደረገ ነው።

ሁለተኛው በመቄዶንያ የተገኘንበት ምክንያት በመቄዶንያ ከ8,000 የሚልቁ ለችግር የተጋለጡ፣ ጎዳና ላይ የወደቁ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን፣ ሙስሊሞች ክርስቲያኖች በኀብረት አሉ።

ስለዚህ ከእነርሱ ጋር ሆነን ብንጸልይ፣ ወደ ፈጣሪ ብናነባ ፈጣሪ ምህረት፣ ቸርነት ያደርግልናል በሚል እሳቤና መቄዶንያም መደገፍ ስላለበት ድጋፍ እንዲደረግለት በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ለማቅረብ ነው።

ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል። ሰላምን በማረጋገጥ ግን ጥቅም ይገኛል ”
ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia