TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ሕግ ፊት እናቀርበዋለን " - ፌዴራል ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፤ በሃይማኖታዊ ስፍራ ላይ ጥይት ወደ ላይ ሲተኩስ የነበረው አባሉ በቁጥጥር ስር እንደሚኝ ገልጿል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሰ ግለሰብ በቤተክርስቲያን ውስጥ እየተዘመረ በነበረበት ሰዓት ወደ መድረክ ወጥቶ በተደጋጋሚ ሲተኩስ የሚያሳይ ቪድዮ ተሰራጭቷል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባሉ ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ እንደሚባል ገልጿል።

ክስተቱ የተፈጸመው ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተላከበት ወቅት መሆኑን አመልክቷል።

" ጥር 5/2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን በመገኘት ነው የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ የነበረው " ያለው ፖሊስ ይህ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ ነው ብሏል።

የፖሊስ አባሉ ይህን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ውሎ የፈፀመው ድርጊትም በተቋሙ #ሕገ_ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አመልክቷል።

ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት ያቀርበዋል ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia