TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናውን ውጤት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ። ውጤት የሚታየው ፦ ► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et ► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284 ► በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.iss.one/EAESbot ላይ ነው። ከፍተኛ የኔትዎርክ መጨናነቅ ስለሚኖር በትዕግስት ይሞክሩት። በ2016 ዓ / ም ለፈተናው ከተቀመጡት…
#ዮናስንጉሰ #ሔለንበርኸ👏

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሀገሪቱ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው የትግራይ ፣ የቓላሚኖ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪው ዮናስ ንጉሰ ነው።

በትግራይ ሀገር አቀፉ ፈተና ከ700 መሰጠቱ ይታወሳል።

ተማሪ ዮናስ ንጉሰ ከ700ው 675 በማምጣት በሀገር ደረጃ ታሪካዊ ነው የተባለውን ውጤት አስመዝግቧል።

ከዚህ ቀደም ከ700 በተሰጠ ፈተና ይሄን ያህል ከፍተኛ ውጤት (675) በሀገር ደረጃ ሲመዘገብ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።

ሌላኛዋ የቓላሚኖ ተማሪ ሔለን በርኸ 662 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።

ሌሎችም የቓላሚኖ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸው ተሰምቷል።

የትግራይ ልማት ማህበር በተመዘገው ውጤት መደሰቱን ገልጿል።

ትምህርት ቤቱ እጅግ ጎበዝ የሚባሉ ተማሪዎች የሚማሩበት ነው።

@tikvahethiopia