" ክረምቱ ይገባል በኛ በኩል ጊዜውን ከዚህ በላይ መግፋት አንችልም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
" ምርጫው የሚደረግባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታ፣ የበጀት እና ድምፅ የሚሰጥበት ቀን እና ጊዜ ይታሰብበት " - ተፎካካሪ ፖርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፀጥታ ችግር ምክንያት 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያልተደረገባቸው እና ቀሪ ምርጫ የሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ አራት ክልሎች በሰኔ 6 2016 ዓ/ም ምርጫ የሚደረግ መሆኑን አሳውቋል።
ምርጫ ቦርድ ከጥር 22 ፥ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የምርጫ ቢሮዎችን የመክፈት እንቅስቃሴ በመጀመር ፣ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ምልመላ እያከናወነ ሲሆን የመራጮች ምዝገባ ከሚያዚያ 7 እስከ ሚያዚያ 21 / 2016 ዓ/ም ለማድረግ አቅዷል።
ምርጫ ያልተደረገባቸው እና ቀሪ ምርጫ የሚደረግባቸው ፦
👉 4 ክልሎችን ፣
👉 29 የምርጫ ክልሎችን ፤
👉 1146 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎችን፣
👉 በ34 የሀገር ውስጥ የተፈናቃዮች የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ወደ 5730 የሚሆኑ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ባካተተ መልኩ ለ9 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እና ለ26 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ምርጫ ይደርጋል።
የሲቪክ ማህበራት እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምን አሉ ?
- የምርጫ ጊዜው ክረምት መሆኑ አብዛኛው መራጭ አራሽ ገበሬ መሆኑን ያላገናዘበ መሆኑ ፤ በተጨማሪም የምርጫው ቀን ሰኔ 6 2016 ዓ/ም ቀን ሐሙስ የሚውል መሆኑን ተከትሎ ቀኑ እንዲሻሻልና በእረፍት ቀናት እንዲደረግ ሀሳብ አላቸው።
- ለመራጮች ምዝገባ የተሰጠው ቀን ከሚያዚያ 7 እስከ 21 መሆኑ እና የእጩዎች ምዝገባና ከሚያዚያ 7 እስከ ሚያዚያ 16 ፥ 2016 ዓ/ም መሆኑ የሚያንስ ስለሆነ ቀኑ እንዲጨመር ጠይቀዋል።
- ምርጫ ከሚደረግባቸው ክልሎች አንዱ በሆነው ቤንሻንጉል ክልል መተከል እና ካማሺ እና ሌሎች አካባቢዎች ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት ምርጫውን ለማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ ቦርዱ አራቱ ክልሎች ያሉበትን የፀጥታ ሁኔታን የሚለይ ግምገማ አድርጎ ከሆነ ጥያቄ ቀርቦለታል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወ/ሮ ሜላተ ወርቅ ሀይሉ ለጥያቄዎቹ ምን ምላሽ ሰጡ ?
የምርጫ ቀኑ #ሐሙስ እንዲሆን የተወሰነው ቅዳሜ እና እሁድ የእረፍት እና የገበያ ቀናት በመሆናቸው ምክንያት ያን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
ቦርዱ ጥያቄውን #የሚቀበለው መሆኑን እና ቀኑ ወደ እረፍት ቀናት ሊቀየር የሚችልበትን ሁኔታ እንዳለ ፍንጭ ተሰጥተል።
ቀኑ አጠረ ስለተባሉት የምዝገባ ቀናት ከጊዜ እጥረት አኳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ቦርዱ ምርጫ በሚደረግባቸው ክልሎች ያሉበትን የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ከሚመለከተው አካል መረጃ ጠይቆ በመጠባበቅ ላይ ነው።
ቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፀጥታ ሁኔታ ግምገማ ስብሰባ እንደሚኖር በመግለፅ የፀጥታ ሁኔታውን ለባለድርሻ አካላት ይፋ የሚያደርግ መሆኑን አመልክተዋል።
@tikvahethiopia