" ... 49 የንግድ ቦታዎች በታላላቅ ባለሀብቶች እጅ የተገኙ ሲሆን 17 ቦታዎችም በአመራሩና የመንግስት ሰራተኛዉ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ እጅ ብቻ 32 ሼድና ኮንቴነሮች ተይዘዉ ተገኝተዋል " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች
በሀዋሳ ከተማ ለወጣቶች ከተላለፉ የንግድ ቦታዎች ሰባ በመቶው (70%) በህገወጥ መንገድ ላልተገባ አገልግሎት መዋሉን የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
በኦዲት ሪፖርት መሰረት ከ1525 ኮንቴነርና ሸዶች ወስጥ ወጣቶች በአግባቡ እየተጠቀሙባቸዉ ያሉት 342 ብቻ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያው የገለጹት የቢሮዉ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረጺዮን አበበ ቀሪዎቹ 1183 ሸዶችና ኮንቴነሮች #ላልተፈቀደለት አገልግሎት መዋላቸዉን ገልጸዋል።
በ5 አመት መመለስ የነበረባቸዉ የመስሪያ ቦታዎች ሼዶችና ኮንቴነሮች እስከ 20 አመታት ድረስ በግል ይዞታነት መቆየታቸውን የሚገልጹት ኃላፊዋ አሁን ላይ አንዳንዶቹ ቦታዎች ላይ በብሎኬት ገንብተዉ በማጭበርበር " ህጋዊ ነን " የሚሉ መኖራቸዉን ያነሳሉ።
በሌላ በኩል በማህበር ተደራጅተዉ የተቀበሉትን የመስሪያ ቦታ በማከራየት እንደገና በስራ ፈላጊ ከሚመዘገቡት በተጨማሪ የተሰጣቸውን የንግድ ቦታ #ወደመኖሪያ ቦታነት የቀየሩ እንዳሉም የኦዲት ግኝቱ ይጠቁማል።
ከዚህ በተጨማሪም 49 የንግድ ቦታዎች በታላላቅ ባለሀብቶች እጅ የተገኙ ሲሆን 17 ቦታዎችም በአመራሩና የመንግስት ሰራተኛዉ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ እጅ ብቻ 32 ሼድና ኮንቴነሮች ተይዘዉ ተገኝተዋል።
የኦዲት ግኝቱ ካመላከታቸዉ ህገወጥ ድርጊቶች ውስጥ በከተማዉ ለወጣቶች ከተሰጠ 15 ሄክታር መሬት አንድም ቦታ በወጣቶች እጅ አለመገኘቱና መቶ በመቶ በባለሀብቶች እጅ መገኘቱን የሚያነሱት ወይዘሮ ሀገረጺዮን አሁን ላይ እንዲህ ያሉትን ወንጀሎች ተከታትሎ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጉዳዩ ለከተማ አስተዳድሩ መሰጠቱን ገልጸዋል።
በመሆኑም ወጣቶች የተሰጣቸዉን ጥሩ እድል አሳልፈዉ ከመስጠት ተቆጥበዉ ራሳቸውን እንዲቀይሩ ጥሪ ያቀረቡት ኃላፊዋ ይህ የክትትልና የማጣራት ስራ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተደራሽ እንደሚደረግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia