የ3 ዓመት ህፃን ልጅን አስገድዶ ለመድፈር የሞከረው የ31 ዓመት ግለሰብ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።
ተከሳሽ አቶ ሙላት ይርጋ ደስየ ዕድሜው 31 ዓመት ሲሆን ግለሰቡ ከእሱ ጋር ተቃራኒ ፆታ ያላትን የ3 ዓመት ዕድሜ ያላትን ህፃን ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 11:30 ሰዓት አካባቢ ከታላቅ እህቷ ጋር እየተጫወተች እንዳለ ቤተሰብ መስሎ በመጠጋት ጎንጯን አዟዙሮ በመሳም ልዩ ቦታው " አደንጉር " ከተባለው ስፍራ አዳዲስ ከተሰሩ ቤቶች ውስጥ እጇን ይዞ ሰው ከማይኖርበት ቤት አስገብቶ ሊደፍር ሲል ሰዎች ይደርሱበታል።
በዚህም ወቅት ግለሰቡ ሩጦ ለማምለጥ ሲሞክር ሊያዝ ችሏል።
ህፃኗ በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎላት ክብረ ንፅህናዋ ያለና በግራ በኩል የብልት ቆዳ መላጥ የደረሰባት መሆኑን በህክምና መረጃ ተረጋግጧል።
ክስ የቀረበበት ተጠርጣሪው የወንጀል ድርጊቱን ክዶ ቢከራከርም ዓቃቤ ህግ ባቀረባቸው የሰው ምስክሮችና የህክምና ማስረጃ ጥፋተኝነቱ #ሊረጋገጥ ችሏል።
ሆኖም ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የወልድያ ከተማ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ ተከሳሽን ያስተምራል ሌላውን ማህበረሰብ #ያስጠነቅቃል ያለውን የ16 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት አሳልፏል።
መረጃው ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።
@tikvahethiopia