TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ይሄንን ሙሰኛ አስተዳደር በማስወገድ ሰላምን ለማስፈን ወስነናል " - የጋቦን ወታደሮች

በጋቦን መፈንቅለ መንግሥት ተደረገ።

ባሳለፍነው ቅዳሜ በአፍሪካዊቷ ሀገር ጋቦን ምርጫ ተደርጎ ነበር በዚህም ምርጫ ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ማሸናፋቸው ተነግሮ ነበር።

ነገር ግን የሀገሪቱ ወታደሮችየተካሄደውን ምርጫ ውጤት በመሻር ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎን ከስልጣን ገልብጠው መንበሩን መቆጣጠራቸውን አሳውቀዋል።

በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ' ጋቦን 24 ' ላይ ቀርበው ወታደራዊ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት " የጋቦንን አስተዳደር ይዘናል " ብለዋል።

ቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ ከቀረቡት ወታደሮች አንደኛው " ይሄንን ሙሰኛ አስተዳደር በማስወገድ ሰላምን ለማስፈን ወስነናል " ብሏል።

" አስተዳደሩ ኃላፊነት የጎደለውና ወዴት እንደሚሄድ የማይታወቅ ስለሆነ የአገሪቱን ማኅበራዊ ኑሮ በማመሳቀል ወደ ቀውስ ከቶናል " ሲልም ገልጿል።

በብሔራዊ ቴሌቭዥኑ የቀረቡት 12 ወታደሮች ሲሆኑ ፕሬዜዳንት አሊ ቦንጎ ያሸነፉበትን የምርጫውን ውጤት እንደሰረዙት ገልጸዋል።

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን እንዳለው ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ አግኝተው ነበር ምርጫውን ያሸነፉት።

ተቃዋሚዎች ግን ምርጫው ተጭበርብሯል ብለዋል።

በወታደራዊ አመራሮች ከሥልጣን ተወግዷል የተባለው የአሊ ቦንጎ ቤተሰብ ጋቦንን #ለ56_ዓመታት መርቷል ፤ ከነዚህ አመታት ውስጥ አሊ ቦንጎ ብቻቸው 14 ዓመት ሀገሪቱን መርተዋል።

አሊ ቦንጎ ከዚህ ቀደም 2019 ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮባቸው ከሽፎ ነበር።

በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት መፈንቅለ መንግሥት ሲደረግ በተደጋጋሚ መሰማቱ ይታወቃል።

በቅርቡ እራሱ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኒጀር #ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት አውጀው ስልጣን እንደያዙ ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ በቅርብ ዓመታት በመፈንቅለ መንግሥት ምክንያት ታምሰው እንደነበር አይዘነጋም።

መረጃው ከቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ እና ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን የተሰበሰበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ይሄንን ሙሰኛ አስተዳደር በማስወገድ ሰላምን ለማስፈን ወስነናል " - የጋቦን ወታደሮች በጋቦን መፈንቅለ መንግሥት ተደረገ። ባሳለፍነው ቅዳሜ በአፍሪካዊቷ ሀገር ጋቦን ምርጫ ተደርጎ ነበር በዚህም ምርጫ ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ማሸናፋቸው ተነግሮ ነበር። ነገር ግን የሀገሪቱ ወታደሮችየተካሄደውን ምርጫ ውጤት በመሻር ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎን ከስልጣን ገልብጠው መንበሩን መቆጣጠራቸውን አሳውቀዋል። በአገሪቱ…
#Update

የጋቦን ወታደሮች አሊ ቦንጎን የቤት ውስጥ እስረኛ አድርገዋቸዋል።

መፈንቅለ መንግሥት የተደረገባቸው ፕሬዜዳንት አሊ ቦንጎ ካሉበት ቤት ውስጥ ሆነው " እርዱኝ " የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ለወዳጆቻቸው በቪድዮ አሰራጭተዋል።

ምንጩ በትክክል ባልታወቀውና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰጨው ቪድዮ ፕሬዜዳንት አሊ ቦንጎ " በዓለም ዙሪያ ያሉ ወዳጆቻቸው ሁሉ ድምፅ እንዲያሱም " ተማፅነዋል።

" እዚህ ያሉ ሰዎች እኔን እና ቤተሰቦቼን አስረዋል ፤ ልጄ የሆነ ቦታነው ያለው፤ ባለቤቴ ሌላ ቦታ ነች ፤ እኔ ደግሞ አሁን ያለሁት በመኖሪያ ቤቴ ውስጥ ነው። ምንም እየተፈጠረ አይደለም ፤ ምን እየሆነ እንዳለም አላውቅም። " ብለዋል።

በመሆኑም በዓለም ዙሪያ ያሉ ወዳጆቻቸው ድምፅ እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ዕለት በጋቦን ምርጫ ተደርጎ የነበር ሲሆን በምርጫው ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ማሸናፋቸው ተነግሮ ነበር።

ነገር ግን የሀገሪቱ ወታደሮች የተካሄደውን ምርጫ ውጤት በመሻር ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎን ከስልጣን ገልብጠው መንበሩን ተቆጣጥረዋል።

ወታደራዊ አመራሮች በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት " የጋቦንን አስተዳደር ይዘናል " ብለዋል።

" ይሄንን ሙሰኛ አስተዳደር በማስወገድ ሰላምን ለማስፈን ወስነናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" አስተዳደሩ ኃላፊነት የጎደለውና ወዴት እንደሚሄድ የማይታወቅ ስለሆነ የአገሪቱን ማኅበራዊ ኑሮ በማመሳቀል ወደ ቀውስ ከቶናል " ሲሉም ተናግረዋል።

ወታደሮቹ ፕሬዜዳንት አሊ ቦንጎ ያሸነፉበትን የምርጫውን ውጤት ሰርዘውታል።

በወታደራዊ አመራሮች ከሥልጣን ተወግዷል የተባለው የአሊ ቦንጎ ቤተሰብ ጋቦንን #ለ56_ዓመታት መርቷል ፤ ከነዚህ አመታት ውስጥ አሊ ቦንጎ ብቻቸው 14 ዓመት ሀገሪቱን መርተዋል።

@tikvahethiopia