#Update በአዲስ አበባ #ለውጭ_ሀገራት የስራ ስምሪት ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ ተገለፀ። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአዲስ አበባ ከተዘጋጁት የስልጠና ማእከላት ውስጥ የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የንፋስ ስልክ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ ማዕከላትን ተመልክቷል። እነዚህ ማዕከላት ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት ስራ ለሚሄዱ ዜጎች ስልጠና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅቶች ማድረጋቸውን ነው መታዘብ የተቻለው። ማዕከላቱ ዘመናዊ የቤት ውስጥ መገልገያ መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የማብሰያና ሌሎች የቤት ውስጥ ቁሳቆሶችን ለማሟላት ሞክረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia