#MoE
" የትምህርት ሥርአቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤትና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት የጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ " በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ስራዎች እየተሠሩ ነው ፤ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም ይገባል " ብለዋል።
" የትምህርት ሥርአቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም " ያሉት ሚኒስትሩ " በሚታዩት ውጤቶች ሳንደናገጥ ዘርፉን ለመለወጥ ጠንክሮ መሥራት ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።
👉 የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማነስ ፣
👉 ተስፋ መቁረጥ፣
👉 የመምህራን እጥረትና ተነሳሽነት አለመኖር፣
👉 የትምህርት ቤቶች መሠረተልማት መጓደልና ለመማር ማስተማር ምቹ ያለመሆን
👉 የትምህርት ቤቶች አመራር መጓደል #ለውጤቱ_መውደቅ ምክኒያቶች መሆናቸው በጥናቱ ተመላክቷል።
የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥም የትምህርት ዘርፍ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባም ተገልጿል።
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በቀጣይ ወር የሚጀመር ሀገራዊ ንቅናቄ እንደሚኖር እና ማህበረሰቡን በማስተባበር ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ሥራ እንደሚሰራ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
በዚህ ሂደት ወላጆች የትምህርት ቤቶች ባለቤቶች መሆናቸውን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባቸውና ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤት(NLA) እና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት በባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
ምንጭ፦ የትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopia