TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ‼️

በጉለሌ ክ/ከተማ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 120 የቀበሌ ቤቶችና 64 ሼዶች #ለችግረኞች ተሰጡ።

ከህብረተሰቡ የተወጣጡ ከ200 በላይ አባላት ያሉት ኮሚቴ የሚደርሰውን ጥቆማ በማጥራት በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን ለማስለቀቅ እየሰራ መሆኑን የክፍለከተማው የስራ ሀላፊዎች ገልፀዋል።

የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ በክፍለከተማው ከተገኙት 120 ቤቶች 53 ቤቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች የተላለፉ ሲሆን ቀሪዎቹ ቤቶች ለልማት ተነሺዎች ተሰጥተዋል።

በተመሳሳይ በክፍለ ከተማው ያላግባብ ተይዘው የነበሩ የጥቃቅንና አነስተኛ መስሪያ ቦታዎችን በማስለቀቅ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ተደራጅተው በመስሪያ ቦታ እጦት ወደ ስራ ላልገቡ ወጣቶችና ሴቶች ተሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም ኢ-መደበኛ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊነት በማምጣት ለ1046 ነዋሪዎች በክፍለከተማው ባሉ 5 ሳይቶች ቦታ በማመቻቸት ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታም ተመቻችቷል፡፡

ምንጭ፡- የከንቲባ ጽ/ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia