TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ጀሞ 28 ፣ 14 እና 42 ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው የምርጫ ሂደቱን ገምግመዋል።

የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫውን ትክክለኛ የድምፅ መስጫ ወረቀት #ለማስተማሪያነት ሲጠቀሙ ወ/ሪት ብርቱካን ተመልክተው እርምት እንዲደረግ አድርገዋል።

ሌሌችም የተመለከቷቸውን ክፍተቶችን ሲያስተካክሉ ነበር።

በሌላ በኩል ምርጫ ጣቢያ 42 ዘግይቶ ነው የተከፈተው እንደታዛቢዎቹ ገለፃ ከሆነ ጣቢያው ዘግይቶ መከፈቱ መራጩን አጉላልቷል። ከላይ በተገለፁት ምርጫ ጣቢያዎች ረጅም ሰልፍ መኖሩን በአካል ተገኝተን ተመልከተናል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ቆየት ብለን እናካፍላለን።

(የቲክቫህ አባላት)

@tikvahethiopia