TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ፤ ገቢ የተሽከርካሪ ጭነቶችን በባቡር የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ተሽከርካሪዎች በባቡር ሲጓጓዙ ደህንነታቸው ተጠብቆ ፣ በፍጥነት ፣ በብዛት እና በቀነሰ ወጪ ሀገር ውስጥ ለማድረስ እንደሚያስችል ድርጅቱ አመልክቷል።

ኢባትሎአድ ፤ #ለመጀመሪያው_ጊዜ ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ በባቡር ያጓጓዛቸው ተሽከርካሪዎች በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት " እንዶዴ ባቡር ጣቢያ " ተራግፈው ወደ ገላን የተሽከርካሪ ጊዜያዊ ማቆያ ተርሚናል መጓጓቸውን አሳውቋል።

ተሽከርካሪዎችም ሆኑ ሌሎች ጭነቶች ከ3 እስከ 4 ቀናት በፈጀ ጎዞ ነው ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ የሚደርሱት ጭነቶች በተለይም ተሽከርካሪዎች #በባቡር ሲጓጓዙ ደህንነታቸው ተጠብቆ ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ በሰዓታት ውስጥ ወደ ሀገር እንዲገቡ እንደሚያስችል አመልክቷል።

#ኢባትሎአድ

@tikvahethiopia