TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 “ በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል ” - ማኀበሩ 🔵 “ 20% የደመወዝ ጭማሪ አድርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል ” - ሠራተኞቹ ✅ “ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰናል ” - ፌደሬሽኑ በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ መሠራተኞች ማኀበር ሥር የሚተዳደሩት የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና…
#Update
“ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” - ሠራተኞቹ
በርካታ ቅሬታዎች ያደሩባቸው ከ350 በላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሱቫል ሠራተኞች ለቅሬታቸው አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም።
“ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሩቫል ሰርቪሶች ተቋርጠዋል ” ብለው የነበረ ሲሆን፣ ሠራተኞቹን የሚያስተዳድረው አይሰን የተሰኘው ድርጅት ቅሬታውን በውይይት እንደፈታ ትላንት ምላሽ ሰጥቶን ነበር።
የትራንስፖርት መገናኛ ሠራተኛ ማኀበራት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን፣ ሠራተኞቹ ደመወዝ ሊጨመርላቸው ስምምነት ላይ እንደተደረሰ፣ ሌሎች ጥያቄዎቻቸው በሂደት እንዲፈቱ፣ ለዛሬ ሠራተኞቹ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ነግሮን ነበር።
ሠራተኞቹ አቋርጠውት ወደነበረው ሥራ ተመለሱ ?
ለቅሬታዎቻችሁ " መፍትሄ አላገኘንም " በማለት መብታችሁን ለማስከበር ካደረጋችሁት የሥራ ማቆም አድማ በኋላ ዛሬስ ወደ ሥራ ተመለሳችሁ ? ስንል ጠይቀናቸዋል።
ሠራተኞቹም፣ “ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” የሚል ምላሽ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
ሠራተኞቹ ፦
“ ሥራ ጀምረናል። ግን ገና ብዙ የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ። ሁሉም ቀስ እያሉ ይስተካከላሉ። የደመወዙ ጭማሪ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።
ሌሎቹን ጉዳዮች በተመለከተም ከቀጣይ ሳምንት ጀምረን ወደ ድርድር እንገባለን።
ሁሉም ሠራተኞች ወደ ስራ ተመልሰዋል። ምክንያቱም ማንም ሰው ባደረገው የሥራ አድማ ምክንያት አሉታዊ ነገር እንዳይደርስበት ተፈራርመን ነው የተመለስነው ” ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የሚፈጠር አዲስ ነገር ካለም የምንከታተልና መረጃም የምናደርሳችሁ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Hibir Diaspora
For Ethiopians & Ethiopians with foreign nationalities who are living and working abroad.
For more information visit our website
https://www.hibretbank.com.et/diaspora/
Hibret Bank
United, We prosper!
📞Call us toll-free at 995.
🤳 Join our Telegram community and connect with us. https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 Follow us across all our social media platforms and visit our website on linktr.ee/Hibret.Bank

Photo
#Update
" እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውጤቱ ህዝብን እና አገር የሚያጠፋ አካሄድ በመሆኑ መቆም አለበት " - የተለየ አቋም ያላቸው ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች
በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ የትግራይ ኃይል አመራር መኮንኖች ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ያወጡት መግለጫ ተቃውሞ እየገጠመው ነው።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደርን በመቃወም በብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ያልተሰጠው ጉባኤ ያካሄደው በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት እውቅና እንደሚሰጡ ያስታወቁት የትግራይ ኃይል አመራሮችን ጊዚያዊ አስተዳደሩ በፅኑ ተቃውሟቸዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩን መግለጫ ተከትሎ በአመራሮቹ ሰብሰባ ላይ የተሳተፉ የተለየ አቋም እንዳላቸው የገለጹ ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች ፥ " የሰራዊት አመራር በመሆን የፓለቲካ ፓርቲ የሚመስል ሰራዊት ለመገንባት የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤቱ ህዝብን እና አገር የሚያጠፋ አካሄድ እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።
የተለየ አቋም እንዳላቸው በመግለጫቸው ያሳወቁት ከፍተኛ አመራሮቹ ፤ " አንድ የፓለቲካ ፓርቲ እና በዚህም በዚያም ያሉት ቡድኖችን የሚመለከት አጀንዳ ላይ መወያየት እና አቋም መያዝ ከሰራዊቱ ተልእኮ ውጪና ወታደራዊ ወንጀል በመሆኑ በጥብቅ እንቃወማለን " ሲሉ አብራርተዋል።
" ስለሆነም ከሰራዊቱ ተልእኮ እና የስራ ስምሪት ውጪ ' ጠላት ነው ' በሚል ፍረጃ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ፕሬዜዳንት ለመቀየር የሚደረግ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ተቋማዊ አሰራር የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም በጥብቅ እንጠይቃለን " ሲሉ አክለዋል።
የክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡብ ምስራቃዊ ፣ የደቡባዊ ዞን ኦፍላ ወረዳ እንዲሁም በራስ ተነሳሽነት መሰባሰባቸውን የገለፁ የመቐለ ከተማ ወጣቶች ባወጡት መግለጫ ፤ " ወታደራዊ መኮንኖች ከተልእኮ እና ከተሰጣቸው ህዝባዊ እና መንግስታዊ ስምሪት ባፈነገጠ መልኩ ወደ አንዱ ቡድን በማዳላት ያወጡት መግለጫ በአስቸኳይ እንዲያርሙት " ሲሉ ጠይቀዋል።
የትላንቱ የመግለጫ ተቃዋሚዎች ፤ " አመራሮቹ ያወጡት ህገ-ወጥ መግለጫ ጅምር ሰላሙ የሚያጨልምና የሚያመክን በመሆኑ ፤ ለህግ እና ስርዓት ተገዢ ከሆኑ አመራር እና አባላት ጋር በመሆን እስከ መጨረሻ ብፅናት እንደምንታገላችሁ ልናሳውቃችሁ እንፈልጋለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የትላንቱን መግለጫ በመቃወም ለቪኦኤ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " የትግራይ ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ እንዲሆን የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ስህተት ነው ፤ ወታደራዊ መኮንኖቹ ፓለቲከኛ መሆን ካሰኛቸው ወታደራዊ ሃላፊነታቸው በመተው የፈለጉት ፓርቲ አባል መሆን ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ያደረጉት ስህተት ግን በአስቸኳይ እንደሚያሩሙት ተስፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

ተረጋግተን በጥንቃቄ ብናሽከረክር ምናለበት ?
" በአደጋው ከሞቱት ሦሥቱ የግብርና ባለሙያዎች የተቀሩት ነዋሪዎች ናቸው " - የስልጤ ዞን አስተዳደር
ትላንትና #ሀሙስ ጥዋት በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።
አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ወደ አርባ ምንጭ ሲጓዝ የነበረ ሀገር አቋራጭ አውቶቢስ ከቢለዋንጃ ወደ ሁልባራግ ኬራቴ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ/ባጃጅ በመጋጨቱ ነው።
የስልጤ ዞን አስተዳደር " በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ ህዝብና መንግሥት የጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ደፋ ቀና የሚሉ ሦስት የግብርና ባለሙያዎች አሉበት ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው " ብሏል።
የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ፥ በባጃጅ ሲጓዙ የነበሩ 8 ተሳፋሪዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ገልጾ " አደጋው ዘግናኝ ነው " ብሎታል።
የሟቾቹ አስክሬን በመቆራረጡና በደም በመጨማለቁ ፊታቸውን በማጠብ ነው ማንነታቸውን መለየት የተቻለው።
ፖሊስ " ጉዳት አድራሹ አውቶብስ በከፍተኛ ፍጥነት ይሽከረከር እንደነበር መረጃዎች አሉ ነገር ግን ተጨማሪ የማጣራት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ " ሲል ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ገልጿል።

" ይሄ የመጨረሻ ደብዳቤያችን ነው ! " - ጠቅላይ ምክር ቤቱ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጨረሻ ያለውን ደብዳቤ ጻፈ ለትምህርት ሚኒስቴር ፅፏል።
ምክር ቤቱ ፤ ኢስላማዊ አልባሳት ስለለበሱ ብቻ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው የሚጠይቅ የመጨረሻ ያለውን ደብዳቤ ለትምህርት ሚኒስቴር ጽፏል፡፡
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢስላማዊ አለባበስ ጋር በተያያዘ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጫናና ከትምህርት መፈናቀል በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ውይይቶች ሲያደርግ መቆየቱንና በዚህ ወር ብቻ ለትምህርት ሚኒስቴር ሶስት ጊዜ ደብዳቤዎችን መጻፉን ጠቅሷል፡፡
ይሁን እንጂ ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር እስከ አሁን ተገቢ ምላሽ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳላገኘና አሁንም ችግሩ በዲላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ መፈፀሙን አመላክቷል፡፡
ጠቅላይ ም/ቤቱ የመጨረሻ ባለው በዚህ ደብዳቤ ኢስላማዊ ልብስ ስለለበሱ ብቻ ትምህርት የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተገፎ ወደ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ የተከለከሉ የዲላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአፋጣኝ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱና ለችግሩ ዘላቂ አስተዳደራዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቋል፡፡

ባለቤቱ ላይ ለመስማት የሚከብድ እጅግ ዘግናኝ የወንጀል ድርጊት የፈጸመው ግለሰብ በሞት ተቀጣ።
(ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ)
" የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት " ይላል ይህ የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ።
ተከሳሽ ግለሰቡ ፀሃዬ ቦጋለ በየነ ይባላል።
ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን እንድትስት ያደርጋል።
በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት ያስገባታል።
ከዛም አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ ይጨምራል።
የቆረጠውን እግሯም ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ይቆያል።
በኋላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ይጣራል።
ግለሰቡም በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል አልቻለም።
በዚህም ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ይወስናል።
ግን ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

🌟 ቴሌብር ሱፐርአፕን በዋይፋይ መጠቀም ተቻለ!!
ቴሌብር ሱፐርአፕዎ ላይ መለያ (Account) ይግቡ፣ በመቀጠል Access on Wi-Fi የሚለውን በመመምረጥ እና መስማማትዎን በማረጋገጥ ለተገደበ ጊዜ አልያም ለሁልጊዜ ደኅንነቱ እንደተጠበቀ ማስተካከል ይችላሉ፡፡
💁♂️ አንድ ጊዜ ካስተካከሉ በኋላ በድጋሚ ማስተካከል ሳይጠበቅብዎ በዋይፋይ ወይም በሌላ ሲም ካርድ ዳታ ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕዎ መግባትና መጠቀም ይችላሉ፡፡
⚠️ ከአገር ውጪ ቴሌብር ሱፐርአፕን መጠቀም ከፈለጉ ከአገር ከመውጣትዎ በፊት እንዲያስተካክሉ ይመከራል፡፡
🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

#Ethiopia
ግምሩክ ኮሚሽን አምራቾች ወደ አገር ዉስጥ እቃዎችን ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ ብቻ እንዲስተናገዱ ፈቅዷል።
ኮሚሽኑ በአምራቾች ወደ አገር ዉስጥ የሚገቡ ዕቃዎች የዋጋ አተማመን ስርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።
158/2011 የተደነገገውን በጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ አተማመን መመሪያ እንዲከለስ ማድረጉን ነዉ የተገለጸው።
ይህ መመሪያ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ በሚወስንበት ወቅት የሚወስደው ጊዜ ከአምራቾች ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ ይገኛል።
ይሄን ተከትሎ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ አተማመን ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን ተነግሯል።
መመሪያ ቁጥር 158/2011 እስኪሻሻል ድረስ በክሊራንስ ጊዜ የዋጋ ማጣራት ሃደቱ የሚወስደውን ጊዜ ለማስቀረት በሚል አምራቾች እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ እንዲስተናገዱ ኮሚሽኑ በላከው ሰርኩላር ፈቅዷል።
ይህ ሰርኩላር ፦
- አምራቾች
- ልዩ መብት የተሰጣቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ፕሮግራም ተጠቃሚ ድርጅቶች፥
- ለኢንቨስትመንት ሥራ ዕቃዎችን በቀረጥ ነፃ የሚያስገቡ ድርጅቶች፤
- የመንግስት ፕሮጀክትን ለመስራት በግል ድርጅቶች የሚገቡ ዕቃዎች፣
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የፌዴራልና የክልል መንግስታት ተቋማትን ይመለከታል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካቲፓል ጋዜጣ ነው።

🔴 “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” - ሙስሊም ተማሪዎች
🔵 “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” - ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው እየተስተጓጎሉ በመሆኑ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠንከር ያለ ስሞታ አቅርበዋል።
የተማሪዎቹ ዝርዝር ስሞታ ምንድን ነው ?
“ ኒቃብና ጥቁር ማስክ እንዳንለብስ ነው የተከለከልነው። ክልከላው የጀመረው ከአንድ ወር በፊት ነበር። በዚህም ማመልከቻ አስገብተን ነበር መልበስ እንዲፈቀድልን። ሆኖም ግን ምላሽ ሳይሰጠን ቆዬ።
ትምህርታችን በስርዓት እንዳንከታተል አስተጓጎሉን። ቅዳሜ፣ አንዲት እህት ማስክ አድርጋ፣ ሂጃብ ለብሳ በምትገባበት ወቅት ኦዲያ ካምፓስ በሁለቱም በሮች እንዳትገባ ከልክለዋታል።
እንዲያውም ወንዶቹ የግቢው ጥበቆች አስፈራርተው ፊቷን አስከፍተዋታል። እንደዛም ሆኖ ማስክ ለብሳ ወደ ግቢ መግባት እንደማትችል ነግረው መልሰዋታል።
ቅዳሜ ከሰዓት ሁለት ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎች ግቢ ሊገቡ ሲሉ ተከልክለዋል። ለምን እንደተከለከሉ ሲጠይቁ ‘ ለደህንነት ሲባል ፊታችሁ መሸፈን የለበትም ’ አሏቸው።
ለደኅንነት ሲባል ከሆነ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በሴት ጥበቃ ተፈትሸው፣ አይዲያቸውን አሳይተው እንዲገቡ ሲጠይቋቸው ‘ ያንችን ፊት ማየት ምንም አይሰራልኝም። ፊትሽን ለምታሳይው አሳይ ’ የሚል መልስ ተሰጠን።
ከዚያ በኋላም ሰኞ እለት ደግሞ ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ መልበስ እንደማይቻል በፕሬዜዳንቱ ጭምር ተወሰነ። የተማሪ ተወካዮች ጠርተው ይህን አሳወቋቸው።
ጥበቃዎቹም ውሳኔውን በመጥቀስ ‘አናስገባም’ አሉን። ማክሰኞ እለት ማታ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን።
ረቡዕ ጠዋትም ከለር ማስክ አድርገው የገቡትን በፌደራል ጭምር አስፈራርተው ፊታቸውን እንዲገልጡ አድርገው፣ ሂጃብም ማውለቅ እንዳለባቸው አሳሰቧቸው።
ከሰኞ ጀምሮ ክላስም እየተከታተልን አይደለም፣ ኤግዛም አልፎናል፣ አሳይመንትም እያለፈን ነው። ማውለቅ ስለማንችል ከግቢ ውጪ ነን። በቃ ከተማሪነት ውጪ ባለ ህይወት ነን። እንደ ሴትነታችን ትልቅ የመብት ጥሰት ነው የተፈጸመብን።
ከምሽቱ 3 ሰዓት እንዳንገባ ሲከለክሉን የት እንድናድር፣ ምን እንድንለብስ፣ ምን እንደምንምገብ ያሰቡትን አናውቅም። ስለዚህ እንደንገባ ቢፈቅዱም እንዲህ ያደርጉበት ምክንያትን ሊጠየቁ ይገባል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅናቸው ስማቸው እንዲነገር ያልፈቀዱ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ ስለጉዳዩ በዩኒቨርሲቲው ፌስ ቡክ ገጽ የወጣውን መረጃ እንድንጠቀም ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎቹ ነቃብ፣ ማስክና ሂጃብ ለብሰው እንዳይገቡ ተከልክለው ከግቢ ውጪ በመሆናቸው ትምህርት እያለፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፤ መከልከሉ ልክ ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።
በምላሻቸው፣ “ እንዲህ አይነት ነገር የለም። የተሳሳተ መረጃ ነው። ማንም ተማሪ እዚህ ግቢ በተፈቀደለት ሰዓት ይገባል፤ ይወጣል ” ሲሉ መልሰዋል።
“ የተቋሙንም ሆነ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት አስተዳደር መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” ብለዋል።
ተማሪዎቹ በተጨባጭ ከግቢ ውጪ እንደሆኑ፣ ክላስ እያለፋቸው እንደሆነ በድጋሚ የገለጽንላቸው እኝሁ አካል፣ በድጋሚም “ የለም ” የሚል ማስተባበያ ነው የሰጡት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የጌዴኦ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን ተማሪዎች ደረሰብን የሚሉት ክልከላ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲው “ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” ብሏልና እናንተ ጉዳዩን አይታችሁት ነበር ? ሲል ማረጋገጫ ጠይቋል።
ምክር ቤቱ ምን መለሰ ?
“ ጉዳዩ ከወር በፊት ደርሶን ነበር። እየቆየ ከፍ እያለ መጥቶ ተማሪዎች ግቢ ለመግባት ሲከለከሉ እኛም ደብዳቤ ፅፈን ነበር ችግሩ እንዲፈታ።
ዩኒቨርሲቲው እርከን ያልጠበቀ ጉዳይ ተደርጎ ታይቶ ነው፤ ተማሪዎቹን እናገኛቸዋለን የሚል ጥሩ ስሜት ነበረው።
የእስልምና አለባበስ ከጥንት ጀምሮ ራሱን የቻለ ሊቃውንቶች ያስቀመጡት ነው። ይሄ የተሻለውና ተመራጭ የሆነው አለባበስ ነው ” ብሏል።
(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#Update 🔴 “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” - ሙስሊም ተማሪዎች 🔵 “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” - ዲላ ዩኒቨርሲቲ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው…
#Update
🔴 " ዩኒቨርሲቲያችን እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
➡️ " ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " - ሙስሊም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት የእስልምና እምነት ተከታይ / ሙስሊም ተማሪዎች " በሃይማኖታዊ አለባበሳችን ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን አድርሰዋል።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ተማሪዎቹ መካከል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ እና ሰመራ ካምፓስ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " አትግቡ መባል ከጀመርን አንድ ወር ገደማ ሆኗል " ያሉን ሲሆን " በሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኮሚቴ አማካኝነት በፅሑፍ ቅሬታ አቅርበን ስንጠባበቅ ከሰኞ ጥር 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ ' ንቃብ ማድረግ አትችሉም ' ተብለን ግቢ እንዳንገባ በመከልከላችን በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለን እንገኛለን " ብለዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኑሬዲን አብደላህ ፤ " ችግሩ ከተማሪዎች ባሻገር አንዲት የዩኒቨርስቲው መምህርትም ጭምር ያካተተ ስለነበር ለዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮች ቅሬታ በፅሑፍ አቅርበን በቂ ምላሽ ስላልተሰጠን ተማሪዎች በዚህ የፈተና ወቅት በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለዉ ይገኛሉ " ብሏል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ከማል ሀሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ በደቡብ ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኩል 150 ተማሪዎች ከእስላማዊ አለባበሱ ጋር በተያያዘ ክልከላ እንደተደረገባቸውና አብዛኞቹ የፈተና ወቅት በመሆኑ ኒቃብ አዉልቀዉ ማስክ እየተጠቀሙ ወደ ግቢ እንደገቡ ገልጸዋል።
ስራ አስኪያጁ ፥ 22 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች አሁንም በመስጊዶች ተጠልለው እንደሚገኙ መረጃዉ በጽሑፍ እንደደረሳቸው ገልፀዉ ጉዳዩን ለትምህርት ሚንስትር በፅሑፍ ማቅረባቸውንና " ባለድርሻ አካላት የቆዩ መመሪያዎችን ዳግም ማየት ይጠበቅባቸዋል " ብለዋል።
" ከሁለት ዓመታት በፊት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ችግር ተነስቶ እንዲረግብ ተደርጎ የነበረ ሲሆን አሁንም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ችግሩ ላለመነሳቱ ዋስተና የሌለ በመሆኑ እነዚህን አጋጣሚዎች ለሌሎች ፍላጎቶች በሚጠቀሙ አካላት ጉዳዩ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ዘላቂ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል " ብለዋል።
ቲክቫህ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)ን ስለ ጉዳዩ አነጋግሯቸዋል።
ዶክተር ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፥ " የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " ብለዋል።
" በዩኒቨርሲቲው ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ አልተከለከለም ኒቃብ ደግሞ አስቀድሞም በዩኒቨርሲቲ አይደረግም ነበር " ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለዉም " በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ዩኒቨርሲቲዉ ' ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ሂጃብ መልበስ ከልክሏል ' በሚል የሚሰራጨዉ መረጃ ትክክል ያልሆነ ሀሰተኛ መረጃ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
በዚህ ምክንያት ወጪ አሉ ስለተባሉ ተማሪዎች እና ስላመለጣቸዉ ፈተናዎች እንዲሁም ስለዩኒቨርስቲው ቀጣይ አቋም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበዉ ጥያቄ የተለየ ዉሳኔ አለመኖሩን ዩኒቨርስቲው አስታዉቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa