TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

የአዲስ አበባ ካቢኔ ሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል።

ካቢኔው " በኮሪደር ልማት አካባቢ ያሉ የግል ባለይዞታዎች የቅድሚያ የማልማት ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበት አግባብ፣ የተጀመሩ ግንባታዎች የቦታ ማስፋፊያ ጥያቄዎች፣ ለኃይማኖት ተቋማት እና የባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ የቦታ ጥያቄዎች ላይ በመወያየት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸዉ አኳያ በመመርመር እንዲፈቀድላቸውና ወደ ልማት እንዲገቡ " ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

ሌላው የአዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለማስተዳደርና ለማልማት የወጣው ረቂቅ ደንብን መርምሮ ለማህበረሰቡ ከሚኖራቸው የጎላ አገልግሎት አኳያ በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተባባሪነት እንዲፈፀም መወሰኑን ታውቋል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች ነው።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት እንደሚፈልግ ገልጿል።

በመሆኑም ፦

- የእንግሊዘኛ፣
- የፈረንሳይኛ
- የዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የሚችሉ እና ዕድሚያቸው ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ምዝገባው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ነው የሚከናወነው።

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት ማስረጃቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው እንዲቀርቡ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ " የአገራት መሪዎች፣ የዓለምአቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚሳተፉበት የአህጉራችን ትልቁ ጉባዔ ላይ በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል በመሆን የዚህ ታሪክ አካል ሆናችሁ አገራችሁን ያለ ክፍያ በኩራት እንድታገለግሉ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ #የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።

ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።

የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።

ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።

ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ድረስ ይቆያል።

ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።

ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት እና ለማመልከት 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል። ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ…
የዛሬው የመርካቶ ገበያ  ውሎ ምን ይመስላል ?

በዛሬው እለት በመርካቶ የሚገኙ የተለያዩ የገበያ ማዕከላት ተዘግተው መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባደረገው ቅኝት ማየት ችሏል።

የመርካቶ ገበያም ከዚህ ቀደም ከነበረው የንግድ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ መዋሉን ነጋዴዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተዘግተው ከዋሉት የገበያ ማዕከላት መካከል
ሚሊተሪ ተራ ፤ ዱባይ ተራ ፤ አድማስ እና አመዴ ገበያ አካባቢ የሚገኙ ሱቆች ይገኙበታል።

ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን የዘጉት ከደረሰኝ ጋር በተገናኘ ውዝግብ መሆኑ ታውቋል።

ነጋዴዎቹ ዛሬ ጠዋት በርካታ የንግድ ሱቆች ዝግ እንደነበሩ የተናገሩ ሲሆን በከሰአቱ የገበያ ሁኔታ አንዳንድ ሱቆች እንደተከፈቱ ገልፀዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከሰዓት በኋላ ባደረጉት ቅኝት የጣና ገበያ ፣ ሲዳሞ ተራ እና ቦምብ ተራ አካባቢ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደታዩበት ታዝበዋል።

በተወሰነ መልኩም ወደ ሸማ ተራ እና መሃል መርካቶ አካባቢዎች መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መመልከት ተችሏል።

ሆኖም ግን በሸማ ተራ ፣ ድር ተራ እና ሰሀን ተራ አካባቢዎች የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ የተቀዛቀዘ መሆኑን ነጋዴዎች ነግረውናል።

በዛሬው እለት በሰሀን ተራ አካባቢ በግምት 8 ሰዓት ገደማ ላይ ነጋዴዎች " አነስተኛ ነው " ያሉት እሳት ተነስቶ እንደነበር ጠቁመዋል። ነገር ግን እሳቱ ሳይስፋፋ ወዲያው በነጋዴው ርብርብ እንደጠፋ ጠቅሰዋል።

በሰሀን ተራ አካባቢ የሚገኙት ሱቆች በአክሲዮን የገበያ ማዕከልን ለመገንባት ሱቆቻቸውን ለቀው እየወጡ እንደሆነም ካነጋገርናቸው ነጋዴዎች ተረድተናል።

በዚህ አካባቢ የሚገኙት ነጋዴዎች ሱቃቸውን የለቀቁት በስምምንነት መሆኑንም ተናግረዋል።

የተለቀቁትም ሱቆች ከወረዳው የመሬት የልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበት " ታሽጓል " የሚል ጽሑፍ ተለጥፎባቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የተለያዩ የመርካቶ ነጋዴዎች በሸማ ተራ ከተከሰተው የእሳት አደጋ በኋላ " ስራ የለም " ሲሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ያለ ደረሰኝ ሲነግዱ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ ይጣላል የተባለው ቅጣት የተጋነነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሱቆቹ የተዘጉት " ግብይቶች ሁሉ በደረሰኝ ይካሄዱ " የሚለው ተቃውሞ እንዳልሆነ አንድ ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀ የመረጃ ምንጭ ገልጿል።

የመረጃ ምንጩ " ግብይቶች በደረሰኝ የሚደረጉ ቢሆንም ተቆጣጣሪ አካላት የተሸጡ እቃዎችን የሚያሳይ ደረሰኝ በሚጠይቁበት እና በምናሳያቸው ወቅት ከሚገባው በታች ነው የቆረጣችሁት በማለት በ6 ወር ሰርተነው የማናቀውን 100 ሺህ ቅጣት ጥለውብን ይሄዳሉ " በማለት አማረዋል።

በአንፃሩ አንድ ሌላ ነጋዴ እንደገለፁት ከንግድ ስራ መንግስት ማግኘት የሚገባው ገቢ ቢኖርም ይህ አሰራር የማይመቻቸው እና ደረሰኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና የምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ  " መርካቶ በባህሪው ብዙ የክልል ግብር ከፋዮች የሚያለቅሱበት ቦታ ነው የሌሎች ክፍለ ከተሞች ግብር ከፋዮችም ቅሬታ ያቀርባሉ ደረሰኝ አይሰጡም በሚል ትልቅ ችግር ስላለበት ትኩረት ተደርጎበት ያለ ነው እንጂ አዲስ አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

ዳይሬክተሩ አክለውም " ቦታው በልዩ ሁኔታ (በግብር አሰባሰብ) በመንግስት ትኩረት ተደርጎበት ሊሰራበት የሚፈለግ አካባቢ ነው ነገር ግን ከአሰራር አንጻር በሚፈለገው ልክ ማሳካት አልተቻለም " ማለታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA

የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋን ጨምሮ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ሚኒስትር ስፔራ፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ፀሀፊ ፋሬል እና ሌሎችም የተካተቱበት ልዑክ ከሀገር መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ጋር መክረዋል።

በወቅቱም ኢንጂነር አይሻ ፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ላላት የረዥም ጊዜ ወታደራዊ ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እንደገለጹና ይህንኑ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳለት መናገራቸውን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ገልጿል።

የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለው ከሆነ ደግሞ በምክክሩ ላይ #በአማራ እና #ኦሮሚያ ያለው ግጭት ጉዳይ ተነስቷል።

ሌላው የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም ስለሚደረገው ስራ (DDR) ውይይት ተደርጓል።

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር በማጠናከር ላይም ትኩርት ያደረገ ምክክር መደረጉን ከኤምባሲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

#USA #USEmbassy

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA

" እውነት ነው " - ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን በገፍ በጅምላ ከሀገር ለማባረር ጦሩን (መከላከያውን) ሊጠቀሙ ይችላሉ ተብሏል።

ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፤ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው በገቡት ቃል መሰረት ሰነድ የሌላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደየመጡበት ሀገር ያባርራሉ።

ለዚህም በመላ ሀገሪቱ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ እንደሚችሉ እንዲሁም ስደተኞቹን ለማባረር የአሜሪካን ጦር ሃብት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ተነግሯል።

የጁዲሻል ዋች ፕሬዜዳንት የሆኑት ቶም ፊቶን ፥ ከዛሬ 10 ቀናት በፊት ትሩዝ በተሰኘው የትራንፕ የማህበራዊ ሚዲያው ላይ ቀጣዩ አስታዳደር በገፍ ስደተኞችን ከሀገር ለማባረር ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ ሊያውጅ እና ወታደራዊ ንብረቶችንም ሊጠቀም እንደሚችል ፅፏል።

ትራምፕ ዛሬ " እውነት ነው !!! " ሲሉ የፊቶንን መረጃ አጋርተዋል።

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ እንደገቡ የመጀመሪያ ስራቸው ስድተኞችን ከሀገር ማባረር እንደሆነ እየተነገረ ነው። በዚህም በርካታ ስድተኞች " ከአሜሪካ ልንባበረር ነው " በሚል ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወድቀዋል።

አንዳንድ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች የትራምፕ በጅምላ ስደተኞችን ማባረር የሚያተኩረው በ ' ወንጀለኞች ላይ ብቻ ነው ' የሚል ተስፋ አድርገዋል።

#USA #deportation

@tikvahethiopia
#InfinixEthiopia

የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን የኢንፊኒክስ ሆት 40 ፣ ኖት 40 ፣ ዜሮ 40 ሞባይል ስልኮችን እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ ኩፖን በመውሰድ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽ ታግ በመጠቀም እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፍ ብቻ ከላይ በተጠቀሱት ሽልማቶች ይንበሽበሹ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
#AddisAbaba

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አፈጸሚ አቶ ሰዒድ አሊ ያለመከሰስ መብት ተነሳ።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

በዚህም ጉባኤ የምክር ቤቱ አባል የሆኑትን የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰዒድ ዓሊን ያለመከሰስ መብትን ተነስቷል።

በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት ነው ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው።

ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተደረገው ከሙስና ጋር በተያያዘ ነው።

ምክር ቤቱ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ መወሰኑ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በራስ ገዟ ሶማሌላድ ዛሬ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ህዝቡ ከጥዋት አንስቶ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ ድምጹን እየሰጠ ይገኛል። በምርጫው የአሁን ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ከአብዲራህማን ኢሮ እንዲሁም ከፋይሰል አሊ ዋርቤ ጋር ይፎካከራሉ። ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ተገንጥላ እራሷን እንደ ነጻ ሀገር የምትቆጥር ናት። ላለፉት በርካታ አመታት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ምንም ግንኙነት…
#UPDATE

አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " የሶማሌላድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን አሸነፉ።

የዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንዲሁም ፋይሰል አሊ ዋርቤ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

የኢሮ ፓርቲ ምርጫውን 63.92 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው። የተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ ፤ ኩልሚዬ ፓርቲ 34.81% ነው ያገኘው።

ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ተገንጥላ እራሷን እንደ ነጻ ሀገር የምትቆጥር ናት። ላለፉት በርካታ አመታት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ምንም ግንኙነት የላትም።

የራሷን መሪ / ፕሬዜዳንቶችን በምርጫ ስትመርጥ ኖራለች።

@tikvahethiopia