TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Awash🚨 ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በአፋር ክልል ፣ ' አዋሽ ' አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ። አንድ የአዋሽ ነዋሪ ፤ " የዛሬውስ በጣም ያስፈራ ነበር  " ሲል ሁኔታውን ገልጾታል። ሌላ ነዋሪው ፥ " በጣም ነው ያስደነገጠን ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው አላህ ይጠብቀን " ብሏል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱንም…
#Earthquake

ከለሊቱ 6:04 ላይ አፋር ክልል፣ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድረስ ተሰምቷል።

በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል።

አርብ ምሽት 3:55 ላይ እንዲሁም ለሊት በዚህ ሰዓት የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር።

በአዋሽ የሚገኝ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " አላህ ክፉን ሁሉ ያርቀው ፤ እጅግ በጣም ያስፈራ ነበር " ሲሉ የዛሬ ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ከለሊቱ 6:04 ላይ አፋር ክልል፣ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድረስ ተሰምቷል። በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። አርብ ምሽት 3:55 ላይ እንዲሁም ለሊት በዚህ ሰዓት የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር። በአዋሽ የሚገኝ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " አላህ ክፉን ሁሉ…
#Update #Earthquake

በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።

ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

አዲስ አሰልጣኝ ፣ አዲስ ድራማ ? ማን ዩናይትድ የድል መንገዱን ይቀጥል ይሆን? ድሉ የማን ነው?

Man United vs Chelsea ዛሬ ጥቅምት 24 ከምሽቱ 1፡30

👉 ይህንን ደማቅ ፍልሚያ ለማየት ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Earthquake በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል። ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው። …
" ቅልጥ አለቱ በመሬት ውስጥ ተረጋግቶ ሊቀርም ወይም ወደ መሬት ላይ ሊፈስም ይችላል። ይህንን በሂደት የምናየው ነው " - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር)

በአፋር ክልል፣ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።

አደጋው ትላንት ምሽት ከለሊቱ 6:04 ላይ በዚሁ አካበቢ የተከተሰተ ሲሆን፣ ንዝረቱም አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱ ታውቋል።

ስለትላንቱ ርእደ መሬትና መንስኤው ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑትን ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር)ን ጠይቀናል።

እሳቸውም፣ " የየቀን ተግባራችንን እያከናወንን ክስተቱ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በንቃት ሁኔታወን ቢከታተሉ ጥሩ ነው " ብለዋል።

በዝርዝር ምን አሉ ?

" ይሄ በአሁኑ ወቅት በፈንታሌ አካባቢ እየተከሰተ ያለው ርዕደ መሬት፤ ቅልጥ አለት (ማግማ) መሬት ውስጥ ከሚያደርገው እንቅስቃሴዎችና ተዛማጅ ሁኔታዎች ጋር የተገናኘ እንደሆነ ቀደም ሲልም አስታውቀናል።

ቅልጥ አለቱ መሬት ውስጥ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የቀነሰ ቢመስልም አልተቋረጠም።

እዚህ ሰሞኑን ከሚሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተያይዞ ፤ በወፍ በረር 130 ኪ.ሜ ላይ የሚገኘው ፈንታሌ አካባቢ እየተከሰተ ያለው የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ግን ወዴት እንደሚያመራ አናውቅም።

ይህ ቅልጥ አለት በመሬት ውስጥ ተረጋግቶ ሊቀርም ወይም ወደ መሬት ላይ ሊፈስ ይችላል። ይህንን በሂደት የምናየው ነው።

ተቋማችን ባለው አቅም እንዲሁም በሀገር ውስጥና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ አብረውን ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር ግንኙነቶችን በማድረግ ሳይንስ የደረሰበት የእውቀት ደረጃን በሙሉ ለመተግበር የሚገባውን በማድረግ ላይ እንገኛለን።

የእኛ ተቋም የምርምር ተቋም በመሆኑ የሚያከናውነው ይህ ርዕደ መሬት የት ተከሰተ? መጠኑ ስንት ነው? መንስኤው ምንድነው ? የቅልጥ ዓለቱስ እንቅስቃሴ ወዴት ሊያመራ ይችላል ? እና የመሳሰሉ ሃሳቦች ላይ መመራመር ሲሆን፤ ይህንን የምርምር ውጤትም ግብአት አድርገው  ባለድርሻ አካላት ከዚህ በኋል መሰራት ያለባቸውን ሥራዎች ይሰራሉ። "


ምናልባት የቴክኖሎጂ እጥረት ይኖር ይሆን ? አደጋውን መቆጣጠር የሚቻልበት የተለዬ ሁኔታስ የለም ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ኤልያስ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

" እየተከሰተ ያለውን ርእደ መሬትም ሆነ የቅልጥ አለት እንቅሰቃሴን ሂደት በቅርብ መከታተል የሚቻል ሲሆን፤ ማቆምም ሆነ መቆጣጠር ግን አይቻልም።

እኛ ብቻ አይደለንም በዓለም ላይ ያሉ ማናቸውም ባለሙያዎች መቆጣጠርና ማቆም አይችሉም። በፈንታሌ አካባቢ ያለውን ሁኔታ እኛ ብቻችን ሳይሆን፤ ሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ተባባሪ ባለሙያዎች ጋር በቅርብ ምክክር በማድረግ እየሰራን ነው።

የእኛ ዩኒቨርሲቲም ሆነ ኢንስቲትዩታችን በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችና ለዚህ ተግባር የሚያገለግሉ ዘመናዊ የሆኑ መሳሪያዎች ያሉት ቢሆንም፣ ዓለም የደረሰበት ሁሉም ዓይነት መሰሪያዎች ግን አሉን ማለት አይደለም።

ለምሳሌ የርቀት ዳሰሳ ወይም ሪሞት ሴንሲንግ የሳተላይት መረጃዎችን የሚያሰባስቡ ሳተላይቶች ስለሌሉን ከዓለም ዓቀፍ ማዕላት መረጃ በመቀበል፣ በመተንተንና ከተባባሪዎቻችን ጋር ሆነን በመቀመር እንሰራለን።

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች መረጃ እንዲያሰባስቡ የተከልናቸው የርእደ መሬትና የGNSS መረጃ ማጠናቀሪያ ጣቢያዎች በዓለም ላይ ደረጃቸውን የጠበቁ ሲሆኑ፤ ብዛታቸውን ግን አሁን ካለው በላይ ማስፋፋት ይጠበቃል። 

ይህ ደግሞ መጠነ ሰፊ መዕዋለ ንዋይን ማፍሰስ ይፈልጋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ አሁን ከተጠቀምንበት ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በአሁኑ ወቅት አስቸጋሪ ስለሆነ ባለን ለመስራት እየተጋን ነው።

ምንም እንኳን ተጨማሪ ጣቢያዎች ያስፈልጉናል ቢባልም፣ ፈጣሪ ይመስገንና በዓለም ደረጃ ስመጥር በሆኑ ባለሙያዎቻችን የማያሰልስ ጥረትና ችሎታ ትክክለኛውን መረጃ ከማንም ባላነሰ መልኩ እያቀረብን እንገኛለን።

አሁን የሚጠበቀው ይህንን መረጃ ወስዶ በተቀናጀ መልኩ ምናልባት ሊፈጠር ከሚችል አደጋ ለመከላከል ዝግጁ መሆን ነው። እኛ የአንድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማዕከል ነን። ከዚህ ውጭ ያለው ሥራ ግን የሌላ ብዙ ባለድርሻ አካላትን መቀናጀትን ይጠይቃል። 

አሁን እያደረግን ካለው ውጭ የማድረግ ማንዴቱም የለንም ተልእኳችንም አይደለም። ይህም ሆኖ ግን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የሚቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው " ብለዋል።

አደጋውን በተመለከተ መደረግ ስላበት የጥንቃቄ ሥራ ባስተላለፉት መልዕክት ደግም፣ " እንዳንዘናጋ ! የእለት ከእለት ተግባራችንን እያከናወንን በንቃት ሂደቱን እንከታተል
" ሲሉ አስገንዝበዋል።

" የስምጥ ሸለቆዎች ባሉበት ሀገር ስለሆነ የምንኖረው ክስተቱ በታየበት ሰሞን ብቻ ሳይሆን፣ አኗራራችን፣ ግንባታዎቻችን፣ አስተሳሰባችን፣ የትምህርት ካሪክለሞቻችን ባጠቃላይ ዝግጁነታችን በዚሁ የተቃኘ መሆን አለበት " ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ !

ፋዌ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እድሚያቸው ከ 15 እስክ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴት እና የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ኮርሶች ነው፡፡

ምዝገባው የሚካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን አመልካቾች በ2014፣2015 ወይም 2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ እና የ2017ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ውጤት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

የማመልከቻ ቀናት ከጥቅምት 22-29/2017 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0911330024 / 0902662688
አዳማ በ 0911383055
ባህርዳር በ 0913042043
ሀዋሳ በ 0965679139 በመደወል ወይም በድረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰብን ማስተማር ነው!

ምዝግባዉም ሆነ የመረጣው ሂደተ ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃልን
#ብርሃን_ባንክ

ስለ ብርሃን ስኩልፔይ (school pay) በጥቂቱ፤
#ለወላጆች ወይም #ለተማሪዎች የትኛውም ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ የትምህርት ቤቱን መለያ ኮድ በመጠቀም የትምህርት ክፍያዎችን መክፈል፤ የክፍያ ማረጋገጫዎችን፤ የክፍያ ሪፖርቶችን እና ተያያዥ መረጃዎችን በእጅዎ ባለው ስልክዎ በቀላሉ ማግኘት ያስችልዎታል፡፡

#ለትምህርት_ቤቶች ደግሞ ክፍያ ሲፈጸም ደረሰኝ ይዞ መሄድ ሳያስፈልግ ት/ቤቱ ሁሉንም ክፍያዎች በስኩልፔይ ሲስተም ማየት እና በቀላሉ መቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ሙሉ የሆነ የተማሪዎችን መረጃ በመያዝ ምቹ አሰራርን ይፈጥራል፡፡

ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#SafaricomEthiopia

💫ከዳር እስከ ዳር በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት! እንገናኝ! የተመቸንን ሼር እናድርግ!👍ከወደድነው ጋር እንደልብ እንገናኝ!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት የሚሰጡ ማደያዎችና በመሰራጨት ላይ የሚገኝ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ከላይ ተያዟል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከነዳጅ ጋር በተያያዘ የተገልጋችን እንግልት ለመቀነስ ሲባል በየዕለቱ ነዳጅ ያለባቸውን ማደያዎች ይፋ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ በአንዳንድ ማደያዎች ረዘም ያለ ሰልፍ መኖሩን ተዘዋውረን ለማየት ችለናል።

@tikvahethiopia
" በሽጉጥ አስፈራርተው ነው መኪናውን ይዘው የተሰወሩት " - ቤተሰቦች

ሶስት የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የሜትር ታክሲ አሽርከርካሪን በሽጉጥ አስፈራርተው መኪናውን ይዘው መሰዋራቸውን ቤተሰቦች አሳውቁ።

ድርጊቱ የተፈጸመው እሮብ በቀን 20 /2/2017 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 6:30 አካባቢ ነው።

አዲስ አበባ ከኢምፔሪያል ሆቴል ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ጋር ከአትላስ ሆቴል ሦስት ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን አሳፍሮ ሲጎዝ የነበረው የሜትር ታክሲ ሹፌር ገርጂ ኖክ ማደያ አካባቢ በሽጉጥ አስፈራርተው መኪናውን ይዘው እንደተሰወሩ የአሽከርካሪው ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የመኪናው አይነት yaris compact ከለሩ ነጭ የሆነና ታርጋ ቁጥር code 3 B14395 እንደሆነ ጠቁመዋል።

ስርቆቱ ሲፈፅም የኃላው መስታወት ሙሉ ለሙሉ የተሰበረ እንደሆነም አክለዋል።

ተሽከርካሪውን ያየ ማንኛውም አካል በስልክ ቁጥሮች በ0912274400 ፣ 0913518744 ወይም ደግሞ አካባቢው ላይ ላለ ማንኛውም የፖሊስ አካል ጥቆማ እንዲሰጥላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ እንዳነሳ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

ለጊዜው የተነሳው ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።

የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል ተብሏል።

መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።

የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ፥ የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይመስላል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መታሰቢያ ፋውንዴሽን 4ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ትላንት እሁድ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

ጉባኤው ትኩረቱን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት እና ስራ ከጀመረነት ጌዜ አንስቶ ምን ምን አብይ ጉዳዮችን አከናወነ ? ምን እንቅፋቶች ገጠሙት? ለእንቅፋቶቹስ ምን መፍትሄ ሰጠ የሚለውን ዋና የመወያያ አንጀዳ አድርጎ ነበር።

በዚሁ መድረክ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ  (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።

ዳንኤል (ዶ/ር) ፤ " ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ ? የሚለው ነው " ብለዋል።

መንግስትም ሲጠየቅ " ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ " ይላል።

ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ " እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው " ይላሉ።

ስለዚህ ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሉ ገልጸዋል።

" ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም " ብለዋል።

ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን አንስተዋል።

" ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የተዓማኒነት ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ችግር ባይሆንም በቀላሉ የሚታይ ግን አይደለም ነው " ያሉት።

" አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ነው " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ " ከችግሩ ክብደት አንጻር ላይገርም ይችላል ነገር ግን ብዙ ነገሮች እየመጡ ሲያልፉ አይተናል አሁን ያለውም ችግር ከኢትዮጵያውያኖች አቅም በላይ ነው ብዬ አላስብም " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም : https://t.iss.one/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Customs

በኤርፖርት ጉምሩክ አንዲት የአረብ ሀገር ተመላሽ ባጋጠማት ጉዳይ ቤተሰቦቿ አንድ መልዕክት ልከዋል።

ግለሰቧ አሁን ላይ በእስር ላይ የምትገኝም ሲሆን ከቀናት በፊት የ8 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባት እያተጠባበቀች ነው።

ያንብቡ 👇
https://teletype.in/@tikethiopia/GycVvbDJpme

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 " Ethiopia land of origins " የሚል ስያሜ የተሰጠውን የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ ከኤር ባስ የአውሮፕላን ኩባንያ ተረክቧል።

አውሮፕላኑ ከፈረንሣይ ቱሉስ ተነስቶ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ጥቅምት 26/ 2017 ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚያርፍ ይጠበቃል።

Photo Credit - ENA

@tikvahethiopia