" የማህበሩ ይዞታ አለአግባብ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ ተሰጥቷል " - የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች
በአዲስ አበባ ከተማ የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ቤቶች ባለቤቶች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር የነዋሪዎች ይዞታ (600 ካ/ሜ በላይ) አለአግባብ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ እንደተሰጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳወቀ።
ጉዳዩ ፍርድ ቤት ድረስ የደረሰና ፍርድ ቤትም ውሳኔ ያሳለፈበት ነው።
ጉዳዩ ምንድነው ?
ማህበሩ ይዞታው እንደሆነ የገለጸውና በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበት እንዲሁም በሳይት ፕላን ሳይቀር በግልጽ የማህበሩ ይዞታ መሆኑ የታወቀ መሬት ተወስዶ ለግለሰብ ተሰጥቷል።
ማህበሩ በሳይት ፕላኑ መሰረት የነዋሪዎች ይዞታውን አጥሮ የበለጠ እንዲለማና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርግ ፍቃድ አግኝቶ አልምቶት ነበር።
ልማቱ የሕጻናት ስፖርት ማዘውተሪያ መጫወቻና የመኪና መተላለፊያ እና ፓርኪንግ ውሎ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም ይህ ቦታ የተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች እንደ ደመራ ፣ ሀዘንና ሰርግ ማከናወኛ ቦታ የነበረ ነው።
ለዚህ የልማት ስራ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ከማህበሩ ወጪ ተደርጓል።
ከዚህ ባለፈ ለህበረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የጋራ መጠቀሚያ ፣ የሕጻናት ማቆያና የስፖርት ማዘውተሪያ የእርድ አገልግሎት መፈጸሚያ በከፍተኛ ወጪ አሰርቶ ለፍቃድ ሲጠባበቅ ነበር።
ነገር ግን ያለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ከክፍለ ከተማው (ልደታ) የመሬት ልማት አስተዳደር " ታዘዘ ነው " በሚል አንዳችም ደብዳቤ ሳይዙ በቃል ብቻ በፖሊስ ኃይል በመታገዝ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የማህበሩን ይዞታ ጥሰው በመግባት ልኬት ወስደዋል።
ከዛ በኃላም ያለ ምንም የፅሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ በግልጽ የማህበሩ ይዞታ እንደሆነ እየታወቀ ኮርዲኔት ተቀይሮ ለግለሰብ መሰጠቱን ማህበሩ እንደደረሰበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማህበሩ ፥ በአንድ የጋራ መኖሪያ ክልል ውስጥ የሚገኙ የጋራ መጠቀሚያዎች በተለይም በ' ግሪን ኤርያ ' የተከለሉ ቦታዎችን ህብረተሰቡን ሳያማክሩ እና የከተማ ፕላንና ልማት መመሪያን ጥሶ አረንጋዴ ቦታዎችን ለግለሰብ እያነሱ መስጠት አግባብ አይደለም ሲል ወቅሷል።
ከዚህ ባለፈ ከአካባቢው የግንባታ ስታንዳርድ አንጻር ቦታውን ለግለሰብ ከመስጠት ይልቅ ለህብረተሰቡ ለልጆች መጫወቻ፣ ለእርድ ቦታ፣ ለኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ፣ ለተለያዩ የማህበራዊ ክንዋኔዌች እንዲሁም ለመኪና ማቆምያ ቢውል የተሻለ እንደሆነ አስገንዝቧል።
ይህ የይዞታ ጉዳይ 2014 ዓ/ም ላይ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶም ነበር።
ከሰሽ ደግሞ ይዞታው የራሱ እንዳልሆነ የታወቀው አካል ሲሆን " ቦታውን ለመንጠቅ አጠሩብኝ ፤ ሁከትም ፈጥረዋል " የሚል ክስ ነው ያቀረበው።
ጉዳዩን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲከታተለው ከቆየ በኃላ ክርክር የተነሳበት ይዞታ የከሳሽ አለመሆኑን ወስኗል።
ነገር ግን ጉዳዩ የተረሳሳ አስመስሎ በቅርቡ ቦታው ታጥሯል። ማህበሩም ለሶስተኛ ወገን እንደተሰጠ እንደደረሰበት ጠቁሟል።
መፍትሄ ፍለጋ ብዙ ቢደክምም ሰሚ አላገኘም።
(የፍርድ ቤት ሂደቱን ከታች ይቀርባል)
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ቤቶች ባለቤቶች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር የነዋሪዎች ይዞታ መሆኑ እየታወቀ ለሶስተኛ ወገን ተላልፏል ያለው ይዞታ ጉዳይ ፍርድ ቤት ድረስ የደረሰ ነው።
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው ጉዳዩን የተከታተለው።
ከሳሽ ሆኖ የቀረበው ደግሞ ታሌሮ ኃ/የተ/የግል ማህበር ነው። ክስ ያቀረበው በሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር ላይ ነው።
ከሳሽ ያቀረበው ክስ ፥ ተከሳሾች በኃይል ገብተው የተሰጠኝን ከ600 ካ.ሜ በላይ የሆነ ቦታ ለመንጠቅ የብረት አጥር በማጠር ሁከትም ፈጥረዋል የሚል ነው።
" በሁከቱ ምክንያት ለደረሰብኝ ጉዳትና ኪሳራ ከነወለዱ ተከሳሾች እንዲተኩ ይወስንልኝ " የሚል ነው።
ከዚህ ጋር የሰነድ ማስረጃ አቅርቧል።
የሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር በበኩሉ ፦
- ከሳሽ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ያቀረበበት ይዞታ በእጃ አደርጎ ወይም በይዞታው ስር አድርጎ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሲያዝበት የነበረ ይዞታ አይደለም።
- ከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ይዞታ ይዞት አያውቅም።
- ከሳሽ ባያያዙት ካርታ ላይ ከተረጋገጠው ይዞታ ውጭ የሆነ ይዞታ ነው። ይዞታው በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በክ/ከተማው መሬት ልማት ማኔጅመንት በኩል ካሳ ተከፍሎብት የሰንጋ ተራ የጋራ ህንፃ ነዋሪዎች ማህበር ይዞታነት የተካለለ ነው፡፡
ስለሆነም ከሳሽ በእጁ በማይገኝ ይዞታ የራሱ ባልሆነና በይዞታው ስር ባልነበረ ይዞታ ላይ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጿል።
ሌላው ከሳሽ የፕላን ስምምነት የተሰጠው አሁን ክርክር በተነሳበት ይዞታ ላይ ሳይሆን አስቀድሞ በነበረው ይዞታ ላይ እንደሆነ አመልክተዋል።
በከሳሽ ይዞታ በማስረጃነት ከተያያዘው ካርታ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ባለ 7 ፎቅ ህንጻ የሰራው በ1685 ካ/ሜ ይዞታ ላይ ነው እንጂ በክሱ ላይ እንደተገለጸው በካርታ ከተያያዘው ይዞታ ውጭ ባለው 600 ካ/ሜ በላይ በሆነው ይዞታ ላይ አይደለም ብለዋል።
ክሳሽ የሁከት ይወገድ ክስ ያቀረበው በህጋዊ መንገድ ከያዘው ይዞታ ውጪ በሆነው በ600 ካ/ሜ ይዞታ ላይ ነው ይህም በእጁ አድርጎ የማያዝበት በመሆኑ ክሱ ተገቢነት የለውም ብለው ተከራክረዋል።
የሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር ፦
° በከሳሽ ይዞታ ወስጥ በመግባት የሰራነው አጥር የለም፤
° ይዞታው የከሽ ስለመሆኑም የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃም የለም።
° አጥር የሰራነውም በይዞታችን ስር አድርገን እየተጠቀምንበት ባለው ይዞታ እና ስልጣን ካው አካል የተሰጠንን የግንባታ ቦታ ፕላን እና የአጥር ግንባታ ፈቃድ በመያዝ በህጋዊ መንገድ ነው።
° በከሳሽ በኩል የቀረቡት ሰነዶች ለክርክሩ መነሻ በሆነው ይዞታ በ600 ካ.ሜ በላይ የሆነው ይዞታ ላይ ባለይዞታነቱን የሚያስረዱ ማስረጃዎች አይደሉም።
° ' ማስፋፊያ ጠይቄ ተስጥቶኛል ' ካለም አግባብ ባለው አካል የተሰጠው ለመሆኑ ሊያረጋግጥ የሚችል ማስረጃ ማቅረብ ሲገባው አላቀረበም።
ክሱ ውድቅ ይሁን ፤ በቂ ወጪና ኪሳራ እንዲከፈለን ሲሉ ጠይቀዋል።
የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጣልታ ገብቶ እንዲከራከር ይታዘዝልን በማለትም ለፍርድ ቤት አመልክተው ነበር።
ማህበሩ በማስረጃነት የሰነድ ማስረጃ እና የሰው ምስክር አቅርቧል።
ፍርድቤቱ የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጣልቃ ገብቶ እንዲከራክር በ29/10/13 ዓ.ም ላይ ትእዛዝ የሰጠ ቢሆንም ጣልቃገብ የሰጡት መልስ ባለመኖሩ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎ ክስ በሌሉበት ተሰምቷል።
ፍርድ ቤት በሁለቱም በኩል የቀረቡ ዶክመንቶችን ከተመላከተ በኃላ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል መጣራት አለበት በማለት የአዲስ አበባ የመሬት ይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤት ከልደታ ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ግራ ቀኙ በተገኙበት ይዞታው በከሳሽ ስራ መሆን አለመሆኑን በማጣራት ምላሽ እንዲልክ አዟል።
በኃላም የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፥
" የቅየሳ መሳሪያ ይዘን በቦታው ላይ በአካል ተገኝተን ልኬት ልንወስድ ዝግጅት እያደረግን እያለ ከሳሽ ጥያቄያቸው በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በያዙት 1685 ካ.ሜ ይዞታቸው ላይ ሳይሆን በካርታ ከያዙት ውጭ ተጨማሪ የቦታ ማስፋፋት ጥያቄ መሆኑን በቃል ያስረዱን ሲሆን በዚህም ልኬት ሳናከናውን ተመልሰናል። ጥያቄያቸው አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሻ በመሆኑ ለሚመለከተው አካል አመልክተናል። " የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።
ፍ/ቤቱም በምላሽ የቀረበው የስነድ ማስረጃ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታ ከሳሽ በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በያዙት 1685 ካ.ሜ ይዞታቸው ላይ ሳይሆን በካርታ ከያዙት ውጭ ተጨማሪ የቦታ ማስፋፋት ጥያቄ መሆኑን እና አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሻ መሆኑን ያሳያል ብሏል።
በዚህም ምላሽ የሚያስረዳው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታ የከሳሽ ይዞታ አለመሆኑን እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል።
ከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ይዞታ በእጁ አድርጎ በእዉነት እያዘዘበት መሆኑ እና ይዞታዉን በህግ አግባብ ያገኘዉ መሆኑ በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ የከሳሽን ክስ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም።
ውድቅም በማድረግ ወስኗል፡፡
ይህ ውሳኔ በተሰጠበት ሁኔታ ቆይቶ እና አረሳስቶ በሚመስል ሁኔታ ቦታው በፖሊስ ኃይል ታግዞ ታጥሯል።
የሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር የማጠር ተግባሩና እየተፈጸመ ያለው ከህግ ውጭ የሚደረግ ድርጊት ይቁም በሚል ይመለከታቸው ያላቸው ቢሮችን ለማነጋገር ቢጥርም ሰሚ አላገኘም።
አሁንም ቦታው ታጥሮ ይገኛል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የፍርድ ቤት ውሳኔና ሌሎች ዶክመንቶች ከላይ ተያይዘዋል)
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በንጉስ ማልት ሁልጊዜ ደስስስስስስስስስስስስስስስስስታ! ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/Negus_Malt
#ከአልኮልነፃ #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት #ንጉስማልት
#ከአልኮልነፃ #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት #ንጉስማልት
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በድጋሚ ቢሮ ሂደን ጠየቅናቸው ግን የተስፋ ቃል ከመስጠት ውጪ መሬት ላይ ምንም ተጨባጭ ነገር አይሰሩም " - ቤት ገዢዎች ከ600 በላይ የሚሆኑ የአያት ግሪን ኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች፣ በውላቸው መሠረት ድርጅቱ የመብራት፣ የውሃ፣ የታንከር መሠረተ ልማቶችን ባለሟማላቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው ከገዙት ቤታቸው መግባት እንዳልቻሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡…
#AddisAbaba
“ ከቆጣሪ ጋ የመገጣጠም ሥራው ግፋ ቢል ከዚህ በኋላ አንድ ወር ቢፈጅ ነው ” - ኖህ ሪልስቴት
ኖህ ሪልስቴት ሰሚነት አካባቢ “ ኤርፓርት ድራይቭ ” በተሰኘ ሳይቱ የገነባቸውን ሱቆችና ቤቶች ዛሬ ለገዢዎቹ ማስረከቡን ገልጿል።
የድርጅቱ የሕግ ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ደስታ፣ “ ዛሬ ሰሚት አካባቢ በሚገኘው 'ኤርፓርት ድራይቭ' የተሰኘ ሳይት ቤቶችን ስላጠናቀቅን የምረቃት ሥነ ስርዓት አካሂደናል ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ሱቅን ጨምሮ ወደ 750 ቤቶች እንዳስረከቡ ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባደረጉት ንግግር፣ “ በዛሬው እለት እያስመረቅናቸው ያሉ 750 ቤቶቾና 43 ሱቆች ከተማችንን የሚመጥኑ ሆነው ለምተዋል ” ብለዋል።
እስከዛሬ ባስረክባችኋቸው ቤቶች የመሠረተ ልማት ቅሬታ ይነሳል (ለምሳሌ አያት ግሪን ሰይት ተጠቃሽ ነው) በአሁኑ ሳይትስ ተመሳሳይ ቅሬታ እንዳይኖር መሠረተ ልማቱ ተሟልቷል ? ሲል ቲክቫህ ለአቶ ዮሴፍ ጥያቄ አቅርቧል።
ምን አሉ ?
“ ከአያት ግሪን ፓርክ ልምድ ወስደናል። ሁሉም ፕሮጀክቶቻችን ላይ መዘግዬት የተፈጠረው ከኮቪድ ጀምሮ ባለው ችግር ነው። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ያለውን ነገር እንዴት እንፍታ ? በሚል ግሪን ፓርኩ ላይ ልምድ ወስደናል።
ከወሰድነው ልምድ አንጻር ለዚህኛው ፕሬጀክት አስፈላጊው ጀነሬተር ገብቷል ፤ ትራንስፎርመር ገብቷል። የመብራት ፓሎችም ተተክለዋል። ከህንጻዎቹ ጋር የማገናኘት ሥራ ብቻ ነው የሚቀረን።
ውሃን በተመለከተ ፤ ቦታው ላይ የከርሰ ምድር ውሃ ቆፍረን ለነዋሪው አዘጋጅተናል። ስለዚህ የውሃ ችግር አይኖርም።
መብራትን በተመለከተም ከመንግስት የፓወር ችግር የለም። በኛ በኩል የሚያስፈልገውን ትራንስፎርመር፣ ጀነሬተር፣ ሌሎቹን ኢንፍራስትራክቸሮች በሙሉ አዘጋጅተናል። ስለዚህ እሱን የማገናኘት ሥራ እንሰራለን ” ብለዋል።
በአጠቃላይ በገዢዎች የሚነሱ የመሠረተ ልማት ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ኖህ ምን እየሰራ ነው ? ዛሬ ያስረከባችኋቸው ቤቶች መሠረተ ልማቶች መቼ ይጠናቀቃሉ ? የሚጠናቀቁበትን ጊዜስ ከገዥዎቹ ጋር ተነጋግራችኋል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ማብራሪያቸው ምንድን ነው?
“ ትልቅ እንቅፋት የነበረው የትራንስፎርመር ችግር ነው። ከመንግስት (ከኤሌፓ) ነው የሚገዛ የነበረው። ከዚያ ብቻ በሚገዛበት ጊዜ ወረፋ እንጠብቅ ነበር። አሁን ግን ተፈቅዶልናል ከገበያ እንድንገዛ። ያ እንቅፋት የለም።
ውሃን በተመለከተ ፤ የከተማውን የውሃ እጥረት ስለምናውቅ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው በከርሰ ምድር ላይ ነው። ውሃም ቶሎ የሚገኝበትን መንገድ እንሰራለን።
ህንጻዎቹ ያልቃሉ ከዛ የመሠረተ ልማት ጥያቄ አለ። ይሄ ጥያቄ የኛ ብቻ አይደለም። ዋናው ሆኖ እያለ በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይም የውሃ እጥረት አለ። ለመቅረፍ እየሰራን ነው።
መሠረተ ልማቱ በምን ያክል ጊዜ ውስጥ ያልቃል ? ሁሉም እቃ ቀርቧል። የቀረው ነገር መብራት በሚሰራው ኮንትራክተር መገጣጠም ነው። ከቆጣሪ ጋ የመገጣጠም ሥራው ግፋ ቢል ከዚህ በኋላ አንድ ወር ቢፈጅ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።
የአያት ግሪን ፓርክ የገዢዎች የመሠረተ ልማት ከምን እንደደረሰ ጠይቀናቸው በሰጡን ቃል አቶ ዮሴፍ ፤ “ ተመሳሳይ እምጃዎችን ወስደን የመብራት አገልግሎቱ አሁን በዬቤቱ ቆጣሪ የማስገባት ሥራ ተጀምሯል” ነው ያሉት።
“ ስለዚህ እዛም ያለውን ችግር አቃለናል። ውሃን በተመለከተ ለውሃ የሚያስፉፍገው የታንከር ማስቀመጫ ቦታ ችግር ነበረብን እሱን ፈትተን ውሃውን ግቢ ውስጥ አስቀምጠን ወደ ፊት እየተራመድን ነው ያለነው ” ሲሉ አክለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

መቐለ ? የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል። የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ…
#መቐለ
" የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲሱን የመቐለ ከንቲባ ከስራ አገዱ።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለዶ/ር ረዳኢ በርሀ " በማለት ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ፤ አዲሱ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ህጋዊ ያልሆነ ተግባራቸውን እንዲያቆሙ አሳስበዋል።
" የመቐለ ከተማ ምክር ቤት መጠቀምያ በማድረግ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ የሚፃረር ተግባር መፈፀም አይቻልም " ያለው የፕሬዜዳንቱ ደብዳቤ የአዲሱ ከንቲባ ሹመት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል።
አቶ ጌታቸው " የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩም ከእርስዎ ጋር መሰራት አይችልም " ብለዋል።
በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች " ህጋዊ አይደሉም " የተባሉት ከንቲባ የሚሰጡዋቸው አመራሮች እና ትእዛዞች ተቀብለው እንዳይፈፅሙ ፕሬዜዳንቱ አስጠንቅቀዋል።
አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ፤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት የስራ አስፈፃሚ ሆነው የተመረጡ ናቸው።
በያዝነው ወር መጀመሪያ ሳምንት ደግሞ የቀድሞውን ከንቲባ አቶ ይትባረክ አምሃ በመተካት ከንቲባ ሆነው እንዲመሩ በመቐለ ከተማ ምክር ቤት መሾማቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle