#update በአዲስ አበባ ከተማ ህገ ወጥ ቤት ገንብተው የሚኖሩ ዜጎች በ2 ሳምንት ውስጥ ግንባታቸውን እንዲያፈርሱ የከተማ አስተዳደሩ አሳሰበ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከክፍለ ከተማ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ዛሬ መክረዋል፡፡
በዚህም ህገወጥ ግንባታ የፈፀሙ አካላት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አፍርሰው ንብረታቸውን እንዲያነሱ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል፡፡
ይህ የማይሆን ከሆነ የከተማ አስተዳደሩ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እርምጃ እንዲሚወስድ ተናግረዋል፡፡
የህገ ወጥ ግንባታ በስፋት ይገኙባቸዋል የተባሉትና እንዲያፈርሱ የተጠየቀባቸው ክፍለ ከተሞች ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ጉለሌና የካ ክፍለ ከተሞች ናቸው፡፡
Via #አሀዱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia