TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ : ንግድ ባንክ ዛሬ ለ4ኛ ተከታታይ ቀን የውጭ ምንዛሬው ላይ ምንም የተለየ ለውጥ ሳያደርግ ቀርቧል።

ዶላር እንደትላንቱ 95.6931 ይገዛል ፣ 101.4347 ይሸጣል።

በአብዛኛዎቹ የግል ባንኮች ላይም ከሰሞኑን የተለየ ጭማሪ የታየበት የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አልወጣም።

በተለያዩ ባንኮች ያለው የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

" ተስፋ ቆርጠናል " - ቆጣቢዎች

በአዲስ አበባ የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት በሚል መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም የኮንዶሚንየም ቤት ምዝገባን በ1997 እና 2005 ያደረገ ሲሆን እጣው የዘገየባቸው ነዋሪዎች " ተስፋ ቆርጠናል " ሲሉ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ቃላቸውን የሰጡት #ለአሃዱ ነው።

ከተመዘገቡ 19 እና 11 ዓመታት እንዳለፋቸው የተናገሩት ተመዝጋቢዎች " ከወደ መንግስትም ምንም አይነት መረጃ እየወጣ አለመሆኑ ጥያቄ ፈጥሮብናል " ብለዋል።

" የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን " የሚሉት ተመዝጋቢዎቹ " በመንግስት በኩል ቅድሚያ እየተሰጣቸው ያሉ ነገሮች ተመዝጋቢዎቹ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያስገባ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋን።

ለአብነትም ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን 3 ሺህ የሚሆኑ ቤቶችን በመግንባት ለሽያጭ ማቅረቡን በማስታወስ " ለምን እንዲህ ይደረጋል ? የሚል ጥያቄ ብናቀርብም ሰሚ አልነበረም " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ምን አለ ?

ኮርፖሬሽኑ " አትቆጥቡ ያለ አካል የለም ከመንግስት በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግንባታዎች እየተካሄዱ ነው " ብሏል።

" ተመዝጋቢዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ " ሲልም ጠይቋል።

ለኮንዶሚኒየም ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎች የት ቦታ ምን እየተሰራ እንደሆነ መግለጽ ከተቻለ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እየተሰራ መሆኑን መግለጽ በቂ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮንዶሚንየም ተመዝጋቢዎች ምን ስራዎችን እየከወነ ይገኛል ? በሚል ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ጽ/ቤቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

ሁለት አስርት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ወራት የቀረው ተመዝጋቢ ለሌሎች ዓመታት በትዕግስት እንዲጠብቅ ተገልጾለታል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሃዱ ነው።

#AddisAbaba #AhaduRadioFM

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ትግራይ

" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ፅ/ቤቱ

በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ወረዳ የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።

የመሬት መደርመስ አደጋው በሰው ህይወት ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም የእህል አዝርእት ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

የመሬት የመደርመስ አደጋ ያጋጠመው ሀምሌ 29/2016 ዓ.ም በዓድዋ ወረዳ በታሪካዊትዋ የይሓ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።

የወረዳው የቁጠባ ዘርፍ ፅ/ ቤት ፤ " በአደጋው የ21 አርሶ አደሮች የተዘራ እህል ሙሉ በሙ ወድሟል " ብሏል። 

' ደምባፍሮም ' በተባለች መንደር የተዘራው ስንዴ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተመላክቷል።

" ከአሁን በፊት በትግራይ ያልተለመደ የመሬት የመደርመስ አደጋ አሁን አሁን መታየት ጀምሯል " ያለው ፅ/ቤቱ " አርሶ አደሩ የክረምቱን ሀያልነት ከግምት ያስገባ ሁሉን አቀፍ ጥንቃቄ እንዲያደርግ " ሲል አሳስቧል።

ዘንድሮ በትግራይ ክልል ያለው ኃይለኛ ክረምት በንብረትና በእንስሳት አደጋ በማደረስ ላይ ይገኛል።

ባለፈው ሳምንት በክልሉ የራያ ጨርጨር ወረዳ ዝናብ ያስከተለው ኃይለኛ ጎርፍ በ106 የቤት እንስሳትና በ11 ሄክታር የእርሻ መሬት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በጎርፉ 91 እንስሳት ሲወሰዱ ፣ 15 ቱ የአካል ጉዳት ደርሷቸዋል። በ11 ሄክታር የተዘራ እህል ከጥቅም ውጭ ሆኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia
#Ethiopia የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነዋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ለ2 ወር በከፊል ዝግ ሆነው ይቆያሉ።

የበጀት ዓመቱ መጠናቀቁን ተከትሎ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዳኞች ለተከታታይ 2 ወራት ማለት ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ እንዲያርፉ በአዋጅ ቁጥር " 1234/2013 አንቀጽ 38 " በመደንገጉ ነው ፍ/ቤቶች በከፊል ዝግ የሆኑት።

ሆኖም ፍ/ቤቶቹ በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያቶች በተረኛ ችሎቶች ለአስተቸኳይ ጉዳዮች ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ/ም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የሚቀጥል ይሆናል።

እነዚህ ጉዳዮችም በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ በዜጎች መብትና በአገር ልማት ላይ አሉታዊ ተጽኖ የሚያሳድሩትን አቤቱታዎች የሚመለከቱ ሲሆን በእነዚህ ተረኛ ችሎቶች ላይ የሚታዩት ፦
° ከእግድ፤
° መፈቻ፤
° ቀለብና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች
° ዋስትና፤
° አካል ነፃ ማውጣት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይነታቸዉ በችሎቱ የሚወሰኑ መሰል ጉዳዮችን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎቶች በመደበኛ ጊዜ የሚሰሯቸዉን አጣርተው ዉሳኔ የመስጠት ስራቸውን ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በመደበኛነት የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይቀጥላሉ፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ እንደሆነ በዛሬው ዕለት አሳውቋል። ይኸው ልዩ ጨረታ የአሜሪካ ዶላር ለሚፈልጉ ባንኮች ነው። ጨረታው ነገ ነው የሚካሄደው። ፍላጎትት ያላቸው ባንኮች እንዲያመለክቱ ጥሪ ቀርቧል። እንደ ገበያው ሁኔታ ደግሞ በመጪዎቹ ሳምንታት ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊወጣ እንደሚችል አሳውቋል። (ዝርዝር…
#NEB : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡

የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ፦

አንድን የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ ተሽጧል።

27 ባንኮች ተሳትፈውበታል።

የዛሬው አማካይ ዋጋም የነገ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ነው ተብሏል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ምን አሉ ?

" ተግባራዊ የተደረገው የባንክ ምንዛሪ ዋጋ ከትይዩ የገበያ ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት መቀራረቡን የሚያሳይ ተጨባጭ ውጤት መገኘቱ አስደሳች ነው። ይህ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሊያሳካ ካሰባቸው ግቦች ነው።

የዉጪ ምንዛሪ ግብይት አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ባንክ ሥርዓት እንዲሸጋገር የሚያደርግ ነው። በዚህም የውጭ ምንዛሪ የሚያመጡትን ላኪዎች እንዲሁም ብዙ ኩባንያዎችን እና የውጭ ምንዛሪ ለሚፈልጉ ሥራ ፈጣሪዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። "

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

💬🎊በSMS ጨዋታችን ፈታ እያልን በየቀኑ በሽልማት እንንበሽበሽ! 🎁

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'START’ ብለን ወደ 34000 ወይም *799# በመላክ እንወዳደር! እናሸንፍ! በአንድ መልስ 1ብር ብቻ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details...
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች

° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው ካሉ አርሶ አደሮች ቅሬታ ሲቀበል ውሏል።

አርሶ አደሮቹ ፥ " ' ያቀረብንላችሁን ምርጥ ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ ብቻዉን መውሰድ አትችሉም ' መባላችንን ተከትሎ የሚችል እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ሲገዛ የማይችል የዘር ወቅት እያለፈበት ነው " ብለዋል።

" ወቅቱ የድንች ተከላ ፣ የአደንጓሬ መዝሪያ ፣ የጎመን መትከያ እና የብዙ የክረምት ግዜ አዝመራ ስራ ነው " የሚሉት የአካባቢው አርሶ አደሮች ስለዚህም የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ቢሆንም ይህን ግን ማግኘት አልቻልነም ብለዋል።

በተለይ " ጃለለ የሚባለው ድንች ሞክረነዉ ከኛ አካባቢ ጋር የማይስማማ መሆኑን ተከትሎ ብንተወውም የወረዳው አመራሮች ግን  እንድንዘራዉ እያስገደዱን ነው " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

የአካባቢውን የአርሶ አደሮች ቅሬታ ይዘን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ፍናን አነጋግረናቸዋል።

ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ? ስንል ጠይቀናል።

እሳቸውም ፤ " ግዳጅ የሚባል ነገር የለም " በማለት አርሶ አደሩ ይሆነኛል የሚለውን ዘር በጁ ካለው ማዳበሪያ ብቻ መውሰድ ይችላል ሲሉ መልሰዋል።

" የማዳበሪያ ስርጭቱን በተመለከተ ነጋዴና ደላላ እጅ እንዳይገባ ጥንቃቄ እያደረግን ቢሆንም የትኛውም መሬቱን ዝግጁ ያደረገ ገበሬ የማዳበሪያ ችግር አይገጥመውም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግር ካለም ለመፍታት ዝግጁ ነን " ብለዋል።

አስተዳዳሪው " ዘመናዊ  የግብርና አሰራሮችን መከተልና ምርጥ ዘሮችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን እናምንበታለን " በማለት ይህንም ከወረዳዉ አርሶ አደር ጋር የጋራ መግባባት ተደርሶ እየተሰራበት ነው ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (No.8) " ባነር አሰርተን ልመና ወጥተናል ገንዘብ ግን እየተገኘ አይደለም " - የታጋች ተማሪ ቤተሰብ ትምህርት አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ የነበሩ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “ ገብረ ጉራቻ ” የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸው አይዘነጋም። ተማሪዎቹ የታገቱት ሰኔ 26/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ ብዛታቸው በትክክል ባይታወቅም…
#Update (No.9)

በታጣቂዎች የታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከምን ደረሱ ?

ሁለት አውቶብስ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት " ገርበ ጉራቻ " ላይ መታገታቸው ይታወሳል።

የታገቱት ሰኔ 26/2016 ዓ/ም ረፋድ 4 ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ ከታገቱ ወር አልፏቸዋል።

ሁለት ታጋቾች 50 ሺህ እና 300 ሺህ ብር ከፍለው ከእገታ መለቀቃቸውን፣ ሆኖም ቢያንስ ከ60 በላይ ተማሪዎች በእገታ ላይ እንደሚገኙ፣ የታጋች ቤተሰብ ማስለቀቂያ ገንዘብ ለመላክ ገንዘብ እያሰባሰቡ መሆኑን አሳውቀችሁ ነበር።

አሁንስ ስለታጋቾቹ ምን አዲስ ነገር አለ ?

ከሰሞኑን ደግሞ የተወሰኑ ታጋች ተማሪዎች ገንዘብ ከፍለው ቢለቀቁም በርካታ ተማሪዎች ግን ከእገታው እንዳልተለቀቁ ለማወቅ ተችሏል።

በእገታው ወቅት በአቅራቢው በነበረ የገለባ ክምር ውስጥ ተብቆ ያመለጠ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው ፣ አምስት (5) ጓደኞቹ ከቀናት በፊት በ100 ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው ከእገታ እንደተለቀቁ ነው።
 
ጓደኞቹ ገንዘብ ከፍለው እንደተለቀቁ፣ ወደ ቤተሰብ ለመቀላቀል በጉዞ ላይ መሆናቸውን፣ አሁንም በርካታ ታጋቾች የመከራ ጊዜ እያሳለፉ መሆኑን እንዳረጋገጡለት ገልጿል።

ልጆቻቸው ከእገታ ያልተለቀቁ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ አጋቾቹ እየጠየቁ ያሉት እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ በመሆኑ ገንዘቡን ባለማግኘታቸው ለልመና እንደወጡ በሀዘን ገልጸዋል።

ጉዳዩን ከመናሻ ጀምሮ እየተከታተለ ያለው በደባርቅ ዩኒቨርሲት የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ኀብረት በበኩሉ፣ በሂደት የሚያሳውቀን ጉዳይ እንዳለ የገለጸልን ሲሆን፣ ቃሉን ሲሰጠን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግዳሮቶቹ ምንድናቸው ? ጠንካራ ጎኑን በሚመለከት በስፋት ከብሔራዊ ባንክ ሰነድ ላይ መረዳት ይቻላል። ስለ ተግዳሮቶቹ ደግሞ የባንክ ጉዳዮች ባለሙያው ሙሴ ሸሙ ተከታዩን ሙያዊ ትንተና አቅርበዋል። ከአስተያየታቸው መካከል ፦ - ገበያ መር (Free Floating) የውጭ ምንዛሪ ስርዓት በተረጋጋ፣ በቂ አቅርቦት እና ምርታማነት እውን በሆነበት ኢኮኖሚ ላይ ተመስርቶ ካልተተገበረ…
#የሐሳብ_መድረክ

(የባንክ ባለሙያ አቶ ሙሼ ሰሙ)

" ፓሊሲው (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ) ተግባራዊ ከሆነ ሳምንት ተቆጥሯል።

ስጋቶች ከየአካባቢው እየተነሱ ነው።

አንዱ የስጋት ምንጭ የሆነው በገቢ እቃዎች ላይ የታየው የዋጋ ንረት ነው።

የችግሩ ምንጭና መፍትሔውን በጋራ እንመልከተው።

ነጋዴው ድሮም እቃ የሚያስመጣው በጥቁር ገበያ ተመን ነበር። እንዲያውም አሁን ላይ ከጥቁር ገበያ ባነሰ የዶላር ተመን የማስመጣት እድል እየተፈጠረለት ነው።

የምንዛሪ ዋጋ ለውጥ ከሌለ የእቃ ዋጋ ለምን ይጨምራል ? የሚል መከራከርያ በስፋት እየተሰማ ነው።

ይህ አቀራረብ ሁለገብ ምልከታ የጎደለው ስለሆነ ወደ ተረጋጋ መፍትሔ የሚወስድ አይመስለኝም።

በመጀመርያ ነጋዴው የሚያስመጣው ቁሳቁስም ሆነ ሸቀጥ 100% ከጥቁር ገበያ በሚገኝ የውጭ ምንዛሪ የሚገዛ አይደለም።

ሁለተኛ ነጋዴው ሚያስመጣው እቃ ዋጋ የሚወሰነው ጉምሩክ ባዘጋጀው የእቃዎች የዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ተመስርቶ ሲሆን ቀረጥ የሚከፍለው ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የእለቱን የውጭ  ምንዛሬ ተመን መሰረት በማድረግ ነው።

ይህ ማለት ነጋዴው ከሳምንት በፊት በ100 ዶላር ለጫነው እቃ ቀረጥ የሚከፍለው በወቅቱ በነበረው የብሔራዊ ባንክ የአንድ ዶላር ተመን ብር 57.5 ተሰልቶ ሲሆን ዛሬ ላይ ቢጭን ደግሞ በባንኮች በሚያወጡት የውጭ ምንዛሪ አማካይ ተመን ላይ ተመስርቶ በሚሰላ ዋጋ 100 ብር ገደማ ነው።

ይህ ማለት የቀረጥ መጣያ ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል ማለት ነው። ' ዋጋ ቀንስ ' ብቻ ሳይሆን ነጋዴው በተመን ለወጥ ምክንያት የተፈጠረበትን  የቀረጥ ጭማሪ እንዴት ይሸፍን የሚለው ጥያቄ መመለስ ይስፈልጋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታሰብበት የሚገባው ፦
° የአውሮፕላን ትኬት፣
° ኢንሹራንስ፣
° የጭነት ዋጋ፣
° የኮንቴይነር ኪራይ በእቃዎች ዋጋ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም።

ቀስ በቀስ በደሞዝና በድጎማ መልክ ወደ ኢኮኖሚው የሚፈሰው ገንዘብም አቅርቦትና ፍላጎትን በማዛባት ግሽበትና የዋጋ ንረት ማስከተሉ የሚጠበቅ ነው።

ሌላው የውጭ ምንዛሪ ግብይት በነጻ የገበያ ውድድር የሚመራ ከሆነ የእቃ ዋጋም ያለማንም ጣልቃ ገብነት ገበያው ውስጥ በሚኖረው አቅርቦት፣ ፍላጎትና የመተኪያ ዋጋን መሰረት አድርጎ መመራት አለበት። ይህ የተሻለው የዋጋ ማረጋጊያ መንገድ ነው።

በተቃራኒው በመመርያና በአስተዳደራዊ እርምጃ የሚተመን ዋጋ የግብይትና የአቅርቦት ስርዓትን በማፋለስ፣ የጥራት ጉድለትና የዋጋ ንረት በአጠቃላይ የገበያ ውጥቅጥን ማባባሱ የሚጠበቅ ነው።

በአስተዳደራዊ ውሳኔ አከፋፋዩም ሆነ ቸርቻሪው ዛሬ እጁ ላይ ያለውን ምርት በውሳኔው ዋጋ አጣርቶ ሊሸጥ ይችላል።

እጁ ላይ ያለው ምርት ካለቀ በኋላ ግን ነጋዴው እንደሚከስር እያወቀ እቃ ለማስመጣትም ሆነ ለማከፋፈል ፍላጎት እንደማይኖረው ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ የእቃ እጥረትና ተጨማሪ የዋጋ ንረት/ግሽበት ፣ እቃ መሰወር፣ ጥራት የጎደለው ምርት ማቅረብና ለኮንትሮባንድ ንግድ  መጋለጥን ሊያስከትል ይችላል።

ጊዜያዊ በሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና በሙስና በተጨማለቁ ደንብ አስከባሪዎች ማዋከብ ነጋዴው ማህበረሰብ ስጋት እንዳያድርበት፣ እንዳይበረግግና ከገበያው እንዳይወጣ፣ በዚህ ምክንያትም ገበያው ይበልጥ እንዳይታወክ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከአቅራቢ፣ ከአከፋፋዩና ከቸርቻሪው ጋር በየደረጃው በመወያየት ነባራዊ ሁኔታውን በማስጨበጥ ስግብግብነት ካለም በእንጭጩ በመግታት የነጋዴውንም ችግር በዛው ልክ በመረዳት ነጋዴውን የችግሩ መንስኤ ሳይሆን የመፍትሔው አካል ማድረግ ዘላቂ ጥቅም አለው። "

#Ethiopia #Economy #MusheSemu

#YeHasabMedrk
@tikvahethiopia
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በመቐለ የተለያዩ ክፍሎች ጨምሮ በሌሎች የትግራይ ከተሞች ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እያጋጠመ ነው።

ይህን ተከትሎ ነዋሪዎች ለከፋ ችግር ተጋልጠለዋል።

የመቐለ የተወሰነ ክፍል የኤሌክትሪክ ሐይል ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ተቆጥረዋል።

ትላልቅ ኢንዳስትሪዎች ጨምሮ በኃይል እጦትና መቋረጥ እየተፈተኑ ነው።

በተለይ በተያዘው የክረምት ወቅት በስፋት እየታየ ያለው እና መቐለ ከተማ ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሚሸፍነው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ሐይል መቋረጥ በነዋሪዎች ዘንድ የከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ፈጥሮ ይገኛል።

በመቐለ በተለምዶ ሰብዓ ካሬ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኤሌክትሪክ ሐይል አገልግሎት ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ሆኗል።

ከመቐለ ውጪም ቢሆን በሀገረሰላም እና ወጀራት አካባቢዎች ከወር በላይ ለሚሆን ግዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተጓጉሎባቸው ቆይቷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ሪጅን የትራንስሚሽንና ሳብስቴሽን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ገብረእግዚአብሔር፥ " የኃይል መቋረጡ ዋነኛ ምክንያት በኃይል ማስተላለፊያ ላይ የደረሰ ጉዳት ነው " ብለዋል።

ችግሩ በግዚያዊነት እስከ መጪው ነሐሴ 5 ቀን 2016 ድረስ ለመፍታት ይሰራል። በዘላቂነት ደግሞ ተጨማሪ ጥረቶች ይደረጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ነው።

#DWAmharic

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM