TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ግብር

የግብር ግዴታቸውን ለመወጣት የሄዱ ጠበቆች ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም በሚል መጉላላት እየደረሰባቸዉ ነው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማሕበር የበጀት ዓመቱን የግብር ግዴታቸውን ለመወጣት የሄዱ ጠበቆች " ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ አይነት ከተመዘገበ ካፒታል ጋር ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም " በሚል መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።

ቅሬታዉን ለፍትህ ሚኒስትር ያቀረበዉ ማህበሩ  ከጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ እና ከግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ሲያጋጥም የቆየውን ችግር በዘላቂነት እንደሚቀርፍ የታመነበት ዝርዝር መመሪያ ሳይወጣና በሥራ ላይ እንዲውል ሳይደረግ የ2016 በጀት ዓመት የግብር መክፈያ ወቅት ተጀምሯል ብሏል።

ይህን ተከትሎ ፍትህ ሚኒስትር ለገንዘብ ሚኒስትር እና ለአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ደብዳቤዉ ጽፏል።

በዚህም የጠበቆችን ታክስ አከፋፈል በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ ወጥቶ ችግሩ ወጥ በሆነ መልኩ በዘላቂነት እስከሚፈታ ድረስ ከዚህ ቀደም በነበሩ ዓመታት ሲስተናገዱበት በቆየው ነባር አሰራር የ2016 በጀት ዓመት የግብር ግዴታቸውን እንዲወጡ እንዲደረግ ጠይቋል።

በዚህ ምላሽ ሊያገኙ እንደሚችል በተገለፀበት ደብዳቤ  ጠበቆች " ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ አይነት ከተመዘገበ ካፒታል ጋር ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም " በሚል የሚደርስባቸዉን መጉላላት ሊቀርፍ ይችላል የሚል እምነት ተጥሎበታል።

#CapitalNewspaper #Ethiopia

@tikvahethiopia
#CentralEthiopia

" እባካችሁ የሰራንበትን ፤ የላባችንን ክፍያ ስጡን " እያሉ ቀን በቀን የሚጮሁ ዜጎች ባሉባት ሀገር እዚህ ጋር ደግሞ ጭራሽ የመንግሥት ሰራተኛ ላልሆኑ ሰዎች በመቶ ሺዎች ብር ወጥቶ ተከፍሏል።

የመንግስት ሰራተኛ ላልሆኑ 19 ሰዎች  ደመወዝ ሲከፍሉ ተደርሶባቸው በሙስና ወንጀል የተከሰሱ 3 ግለሰቦች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸው ተሰምቷል።

በተፈፀመው ወንጀል ተሳታፊ በመሆን ሳይቀጠሩ ደመወዝ ይከፈላቸው የነበሩ ተከሳሾችም በ3 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

የሙስና ወንጀሉ የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ነው።

የሀድያ ዞን ዐቃቤ ህግ ህዳር 30/2016 ዓ.ም ለሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፅፎ ባቀረበው ክስ ምን ይላል ?

1ኛ. ተከሳሽ አቶ ናትናኤል አምቢኮ በሻሾጎ ወረዳ የፋይናንስ ጽ/ቤት የክፍያ ኦፊሰር፤
2ኛ. ተከሳሽ ወ/ሮ አዳነች ጡምደሎ በሻሾጎ ወረዳ የፋይናንስ ጽ/ቤት የክፍያ ቡድን መሪ፤
3ኛ. ተከሳሽ አቶ ታምራት ኒኔ የሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ (በሌለበት የታየ)፤
4ኛ. ተከሳሽ አቶ ሲሳይ ቢያድጌ በወረዳው በመንግስት ሰራተኛነት ሳይቀጠር ደመወዝ ሲከፈለው የነበረ፤
5ኛ. አቶ ሰላሙ አበጀ በወረዳው በመንግስት ሰራተኛነት ሳይቀጠር ደመወዝ ሲከፈለው የነበረ ሲሆን፤

በሻሾጎ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ላልተቀጠሩ  መምህራን ሰራተኞች በቁጥር 19 ሰዎች ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 2016 ዓ/ም ድረስ ከ5 ወር እስከ 11 ወራት ደወመዝ እንዲከፈላቸው አድርገዋል።

በዚህም በድምሩ 7 መቶ 30 ሺህ 2 መቶ 39 ብር በመንግስት እና ሕዝብ  ሀብት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ፤ ያላግባብ ስልጣንን በመገልገል ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ተከታትሏል።

ተከሳሾች የቀረቧቸው የመከላከያ ምስክሮች የዐቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃ አስተባብለው ባለመገኘታቸው ፍ/ቤቱ በሙሉ ድምፅ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቶባቸዋል።

በዚሁም መሰረት ፦ 

1ኛ. ተከሳሽ አቶ ናትናኤል አምቢኮ በሻሾጎ ወረዳ የፋይናንስ ጽ/ቤት ፔሮል አዘጋጅ የክፍያ ኦፊሰር በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር እንዲቀጣ።

2ኛ. ተከሳሽ ወ/ሮ አዳነች ጡምደሎ ኩሪሶ  በሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የክፍያ ሂሳብ ቡድን መሪ በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራትና በ 5 ሺህ ብር እንድትቀጣ።

3ኛ. ተከሳሽ አቶ ታምራት ኒኔ የሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ የነበረ እጁን ለህግ አካላት ያልሰጠና በፖሊስ ታድኖ ሲያዝ የእስራት ጊዜውን የሚያጠናቅቅ ሆኖ (በሌለበት የተወሰነ) በ11 ዓመት ፅኑ እስራትና በ 10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ።

4ኛ. ተከሳሽ አቶ ሲሳይ ቢያድጌ በትምህርት ጽ/ቤት ሳይቀጠርና መምህር ሳይሆን ለ9 ወራት ደመወዝ ሲከፈለው የነበረ በ3 ዓመት ፅኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ።

5ኛ. ተከሳሽ አቶ ሰላሙ አበጀ ተባበል በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ሳይቀጠርና መምህር ሳይሆን ለ 9 ወራት ደመወዝ ሲከፈለው የነበረ በ3 ዓመት ፅኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

መረጃ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው የተገኘው።

#CentralEthiopia #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray : " ... ከጦርነቱ በኋላ የተቋቋመው መንግስት ስራውን ለመስራት አቅም ያጣበት ወቅት ላይ እንገኛለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ ሀምሌ 25 እና 26/2016 ዓ.ም " የትግራይ ፓለቲካዊ አስተዳደር " በሚል ርእሰ አንድ መድረክ መቐለ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተውም ንግግር አድርገው ነበር። ምን አሉ ? - በትግራይ የሃሳብ ጠቅላይነት ሊኖር አይችልም።…
#Tigray : በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በተደራጀ ገለልተኛ በተባለ አንድ አጥኚ ቡድን የክልሉን ሁኔታ በተመለከተ ጥናት ተደርጎ ነበር።

በዚህም ፦

በክልሉ ሕገወጥነት መስፈኑ እና ይህም ወደ ስርዓት አልበኝነት የሚሄድበት ዕድል ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።

የመንግሰት መዋቅር በአንድ ፓርቲ መጠለፉን ያመለክታል።

የክልሉ ህዝብ እና መንግስት ሀብት በግለሰቦች ፣ የውጭ ዜጎች ጭምር እየተዘረፈ እንደሆነ ያሳያል።

የፍትህ ስርዓቱ ተአማኒነት ማጣቱን ያመለክታል።

በህዝቡ ዘንድን ተስፋ ማጣትና ስደት መንሰራፋቱ ይኸው ጥናት አሳይቷል።

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ መንግስት ስራው እንዳይሰራ መቸገሩን ገልፀዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ ፤ " የክልሉ አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ከመስራት ይልቅ፥ ችግሮች በመዘርዘር ተጠምዷል " ብለዋል።

" እኔ እኮ በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር በትግራይ ችግሮቹ ተዘርዝረው እየተነገሩ ያሉት፣ ችግሮቹን ሊፈቱ ስልጣን በያዙ ሰዎች ነው። ኃላፊነታችሁ ልትወጡ ይገባል " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ተናግረዋል።
#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መምህራን " የአማራ ክልል ከማንም ጋር የሚወዳደር አይደለም ፤ መምህራን ጥይት በላያቸው ላይ እያፏጨ ነው ያስተማሩት " - ማኀበሩ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር / ኢመማ / በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ከባድ የሚባል ፈተና ለመጋፈጥ እየተገደዱ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። ቃሉን ለቲክቫህ የሰጠው ማኀበሩ፣ መምህራኑ በከፋ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆነው እየሰሩ ባለበት እንኳ ደመወዛቸው እየተቆረጠባቸው…
🔈#መምህራን

" ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም !! " - የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር

በተለያየ ጊዜ በብሔራቸው አማካኝነትያ ከተለያዩ ክልሎች የተፈናቀሉ መምህራን በሥራ አጥነት ሳቢያ የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር (ኢመማ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለልጿል።

የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " ትግራይ ክልል ዝግ ሆኖ የቆዬ አካባቢ ነው፡፡ ከዚያ አንጻር የተፈናቀሉ መምህራን አሉ " ብለዋል፡፡

" የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሥራ ፈትተው የተቀመጡ መምህራን አሉ። የትግራይ ክልል መምህራን ሆነው ከአማራ ክልል የተፈናቀሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ያሉም አሉ " ሲሉ ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

" ኮይሃ የሚባል አካባቢም የትግራይ ክልል ተወላጆች ሆነው ግን አፋር ክልል ይሰሩ የነበሩ ተፈናቅለው ሥራ ፈትተው የተቀመጡ መምህራን አሉ " ሲሉ አክለዋል።

" በትግራይ ክልል ይሰሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጅ መምህራንም ቢሆኑ ተፈናቅለው ጎንደር የተቀመጡ አሉ " ያሉት አቶ ሽመልስ፣ መምህራን የትም አካባቢ ሂደው መስራት እንዳለባቸው ቢታመንም ችግሮች ግን ጎልተው እየተስተዋሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም እንዲሁ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ለመውጣት የተገደዱ መምህራን እንደነበሩ አስታውሰው፣ " ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም " ብለዋል፡፡

" በተለያዩ ጊዜያት ችግራቸው እንዲፈታ፣ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳውቀናል" ሲሉ ማኅበሩ ያደረገውን ጥረት አስረድተዋል፡፡

" ለትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቀናል፡፡ ትግራይ ክልልም የሰው ኃይል እጥረት አለና ቀጥራችሁ አሰሯቸው የሚል ሃሳብ ነው እያነሳን ያለነው " ብለዋል፡፡

መምህራን ያለምንም ፈቃዳቸው በተለያየ መንገድ ደመወዝ እንደሚቆረጥባቸው ፣ የደረጃ እድገት እየተሰራላቸው እንዳልሆነ ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Mesirat

ቢዝነስዎን ለማሳደግ እሄ ወርቃማ እድል እንዳያመልጥዎ! https://mesirat.acceleratorapp.co/application/new?program=mesirat-entrepreneurs-application-form-sixth-cohort ላይ ተመዝግበው
- በፋይናንስ፣
- በማርኬቲንግ፣
- በቴክኖሎጂ፣
- በኔትወርኪንግ፣
- የባለሙያ አማካሪዎችን በማግኘት፣
- በአገልግሎት ሰጪነት እና
- በአማካሪነት ድጋፍ ያግኙ።

የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም አካል ይሁኑና ቢዝነስዎ እንዲያድግ አጠቃላይ ድጋፍን ያግኙ።
ፕሮግራማችን የባለሙያ ምክር ማግኘት፣ ጠቃሚ ግብአቶች እና ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ስራ ፈጣሪዎች ጋር ንቁ እድገትን ለማፋጠን የተነደፈ ነው።

#መስራት #ስራፈጠራ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ከጸደቀው ገንዘብ ውስጥ ፦ ➡️ 451,307,221,052 ለመደበኛ ወጪዎች ➡️ 283,199,335,412 ለካፒታል ወጪዎች ➡️ 222,694,109,445 ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ➡️ 14,000,000,000 ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው፡፡ @tikvahethiopia
#Ethiopia

ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል።

የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል።

ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡

ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

ከነዚህም ውስጥ #ድጎማ እና #የደመወዝ_ጭማሪ የሚጠቀሱ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች ወጪዎች በአመቱ ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

IMF ሰንድ ትንበያ ምን ያሳያል ?

- የመንግስት ወጪ ቀደም ሲል ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።

- ይህንን ወጪ ለመሸፈን ከአገር ውስጥ ገቢ 1.3 ትሪሊየን ብር (1.15 ትሪሊየን ብር ከታክስ) 214 ቢሊየን ብር ከውጭ የበጀት ድጋፍ በጥቅሉ 1.52 ትሪሊየን ብር የሚገኝ ይሆናል።

- ከውጭ ከሚገኘው 214 ቢሊየን ብር ብድር እና እርዳታ አምና (2016) ከተገኘው 43 ቢሊየን ብር አንፃር በአምስት እጥፍ (500 በመቶ) ጭማሪ ይኖረዋል።

- ከውጭ ከሚገኘው የበጀት ድጋፍ በተጨማሪም ደግሞ በእርዳታ ተቋማት አማካኝነት የሚፈሰው ሃብት ሲካተትበት በጠቅላላ ወደ 304 ቢሊየን ብር ይደርሳል።

- ወጪ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው 1.8 ትሪሊየን ብር ሲሆን የበጀት ጉድለቱ 270 ቢሊየን ብር ይሆናል።

- ከጠቅላላው የመንግስት ወጪ 1.24 ትሪሊየን ብር የመደበኛ ወጪ ይሆናል። ቀሪው 557 ቢሊየን ብር የካፒታል ወጪ ይሆናል፡፡

ሰኔ መጨረሻ ለ2017 በጀት አመት ፀድቆ ከነበረው 971 ቢሊየን ብር በጀት ውስጥ 358.5 ቢሊየን ብር ወይም ከጠቅላላው በጀት 37 በመቶ የሚሆነው የበጀት ጉድለት ነበር፡፡

ሆኖም በIMF ትንበያ ወጪ ይደረጋል ከተባለው 1.8 ትሪሊየን ብር ውስጥ የበጀት ጉድለቱ ከወር በፊት ተቀምጦ ከነበረው መጠን የሚያንስ ነው፡፡

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

#Capitalnewspaper #Ethiopia #IMF

@tikvahethiopia
#HawassaUniversity

በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለጠፈው ማስታወቂያ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲውስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲልኩ ነበር።

ለዚህ ቅሬታ መነሻቸውም አንድ ተለጥፎ ያዩት ማስታወቂያ ነው።

ማስተወቂያው ፦

° በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት ተማሪዎች ወደቤት መሄዳቸውን ይጠቁማል።

° የገበያው አለመረጋጋት አቅራቢዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ ጫና እና በቀን ለ1 ተማሪ የተወሰነው 22 ብር ዕለታዊ ወጪ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ የመግቢያ ቀን መራዘሙን ያሳያል።

° ኢንተርን ሽፕ ላይ ያሉ እና ካፌ ተጠቃሚ የነበሩ እጩ ዶክተሮች በምግብ ምትክ የሚሰጠውን የነን ካፌ ፎግም ሞልተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይላል።

° የተማሪዎች መግቢያ እስኪገለጽ ከቀን 29 /11/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ በመቋረጡ በተለያዩ ምክንያቶች ግቢ ያሉ ተማሪዎች በ4 ቀን ለቀው እንዲወጡ ይላል።

የተማሪዎች ቅሬታስ ምንድነው ?

መልክዕታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ትልቅ ቅሬታ እንዳላቸው ይገልጻሉ።

ቅሬታቸው ፦

- ላለፉት ስምንት ዓመታት ትምህርት ላይ ብንሆንም አሁንም በተለያየ መልኩ ጊዜያችን እየተቃጠለ ነው።
- የመመረቂያ ጊዜያችን አሳሳቢ ሆኗል።
- መግቢያችን ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ትክክል አይደለም።
- በኮቪድ-19 ለአስር ወራት እንዲሁም በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት የትምህርት ጊዚያችን ተቃጥሏል። ወሁን የመመረቂያ ጊዚያችን ተራዝሟል።
- በዚህ ዓመት ለ12ኛ ክፍል ፈተና እንድንወጣ ተደርገን ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ነው የተጠራነው። በኋላም ወደ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም ተገፋ። አሁን ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰማን። ይህ ትክክል አይደለም።
- የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይስጠን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች ቅሬታን እንዲሁም የተለጠፈውን ማስታወቂያ ይዞ ዩኒቨርሲቲው አለኝ የሚለውን ማብራሪያ ለተማሪ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ  ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ ምን አሉ ?

የቀረበዉ መረጃ ትክክል አይደለም።

ኢንተርን ሀኪሞች ከግቢ አይወጡም። ዶርማቸውንም አይለቁም። ይልቁንም ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርስቲው የምግብ አገልግሎት በመቋረጡ በጀታቸዉን እንዲጠቀሙ ነው የተገለጸው።

ይህ የሆነው አሁን ላይ ለ3 አመት ውል የገቡ ነጋዴዎች በእቃ መወደድ ምክኒያት ምንም አይነት የምግብ ግብአት ሊያቀርቡልን ባለመቻላቸዉና ይህን ችግር  ተወያይተን መፍትሄ እስክንሰጠዉ ነው።

ሌሎች ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በቅርቡ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ። ትክክለኛ ቀኑንም  ለተማሪዎች በይፋ ይነገራቸዋል።

ተማሪዎችን አሁን ላይ መቀበል ያልተቻለው ከምግብ አቅርቦትና አንዳንድ ማስተካከያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ስላሉ ነው።

በየጊዜዉ ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲባል ከግቢ መውጣታቸውን ሆነ አሁን ላይ በቶሎ አለመግባታቸው የሚወስድባቸውን ጊዜ  ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው መፍትሄዎችን አስቀምጧል። በዛ ይሄዳል።

ተማሪውን የሚያደናግር ማስታወቂያ ያወጣዉ አካል ከኛ እውቅና ዉጭ በመሆኑ ማንነቱን አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንቱ ተማሪ ደረጀ መንገሻ ምን አለ ?

👉 ኢንተርን ዶክተሮች ከግቢ ባለመውጣታቸዉ እስካሁን መጉላላት አልደረሰባቸውም። ማስታወቂያውም ያለኛ እውቅና ነው የተለጠፈው።

👉 ተማሪውን ሳይፈልግ ወደነን ካፌ መቀየር አግባብ ስላልሆነ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ውሳኔዉ ልክ አለመሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስገብተን ምላሽ እየጠበቅን ነው።

👉 ተማሪዎች ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ያልገቡበት ምክኒያት ዩኒቨርሲቲዉ ከበጀት ማስተካከያና ካምፓስ ውስጥ ከሚያስተካክላቸው አንዳንድ ነገሮች ጋር በተያያዘ ምክኒያት ነው።

👉 ተማሪዎች በጊዜ ወደ ግቢ ባለመግባታቸው በቀጣይ ተማሪዎች ላይ የሚከሰተዉን ጫና በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲያስብበት ተነጋግረናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

More - @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ያንብቡ የኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ ምን አሉ ? - የማይጠበቅ ነው ብዬ መናገር አልችልም። ግን በዚህ ፍጥነት መሆኑ ለእኔ አስደጋጭ ነው። - በእርግጥ አሁን የተደረገው devaluate /ገንዘብ ማዳከም/  አይደለም። devaluation ማድረግ እና floating ይለያያል። - devaluate የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተወሰነ መልኩ በመንግስት ውሳኔ ማዳከም ማለት ነው። አሁን ግን እንደዛ…
#የሐሳብ_መድረክ

IMF ዓለማው ምንድነው ? ቢሊዮን ዶላሮች ደግፎ / አበድሮ ምን ይጠቀማል ?

(በኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ)

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፥ 190 አባል ሀገራት ያሉት የጋራ ድርጅት ነው። ትልልቅ ሼር ያላቸው ሀገራት አሉ። የድርጅቱ ገንዘብ በነዚህ ሼር ካላቸው ሀገራት የሚገኝ ነው።
- አሜሪካ 17.43%
- ጃፓን 6.47%
- ቻይና 6.4%
- ጀርመን 5.59%
- ፈረንሳይ 4.23%
- እንግሊዝ 4.23% ...አላቸው። ሌሎችም ሁሉም ገንዘብ አላቸው በድርጅቱ።

ኢትዮጵያም የIMF አባል ናት።

IMF የተቋቋመው በዓለም ላይ የተረጋጋ የፋይናንስ ስርዓትን ለመገንባት ነው። ለዚህም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ድጋፍ ለማድረግ ነው የተመሰረተው።

በዚህ ምክንያት በየሀገሩ ሪፎርም እያዘጋጀ ይቀርባል ' ይሄን ይሄን አድርጉ ' እያለ ወይም የቀረበለትን እየገመገመ ' ይሄን አድርጉ ይህ እንዲሆን ' ይላል። ትክክል ሲመስለው ያጸድቃል ካልሆነ ውድቅ ያደርጋል።

ኢትዮጵያም ወደ IMF የሪፎርም አጀንዳ ሰንድ ይዛ ቀርባለች። 3 ዓመታት ያህል ሰነዱን ሲገመግም ቆይቶ አሁን አጽድቋል። ሲያጸድቅ ግን የራሱንም መስፈርቶች አስቀምጦ ነው ወደ ተግባር የገባው።

የIMF ስም ከ ' floating exchange rate ' ጋር የሚነሳውም ለዚህ ነው።

እውነት ግን IMF ለሀገራት ስለሚያስብ ነው ? ወይስ በእጅ አዙር ሌላ አላማ አለው ? ይህ ነው ትልቁ መከራረከሪያ ነጥብ።

ይህ መከራከሪያ ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ነው።

IMF ስለ እራሱ የሚለው ምንድነው ? ስራዎቹን በመልካም ጎኑ የሚያዩት አካላት የሚሉት ምንድነው ?

- ዓለም ላይ ባሉ ሀገራት ተወዳዳሪነት ያለበት የኢኮኖሚ ስርዓት እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ የንግድ ስርዓት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- የዓለም ኢንቨስትመንት ያለምንም እንቅፋት እንዲንቀሳቀስ ነው የምፈልገው።
- ገንዘብ በመላው ዓለም በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ እፈልጋለሁ። ... ይላል።

በዚህም ፤ " ምቹ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ያለበትን ሀገር መፍጠር ነው የምፈልገው በየሀገራችሁ ይህን ፈጥርላችኋለሁ " ነው የሚለው።

ስለዚህ መንግሥት ፦
ቁጥጥር ይቀንስ
የገበያው ቁጥጥር ይቀንስ
ጣልቃ እየገባ መቆጣጠሩን ያቁም
የግል ሴክተሩን መቆጣጠር ያቁም
ኢምፖርት ላይ የሚወጣው ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ይቀንስ
ኤክስፖርት ላይ ያለ ቁጥጥር ይቀንስ
ታሪፍ፣ ኮታ አጠቃላይ ቁጥጥር ስርዓት ይቀንስ
አሳሪ ህጎችን አላሉ
ንግድን ፣ ኢንቨስትመንትን የማያበረታታ ህጎችን አላሉ
ፉክክር የማያበረታት ህግ አላሉ
ፕራቬታይዤሽን እንዲኖር አድርጉ
መንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ ተቋማት ወደ ግል ይዙሩ
ሊበራይዜሽን ይጠናከር / በሞኖፖል የተያዙትን ዘርፎች ክፍት አድርጉ (ለምሳሌ ፦ ቴሌ ሊሆን ይችላል)
ማንም ከውጭ አይገባም የሚለውን ቀንሱ ፤ ፉክክር ይኑር
የችርቻሮ ገበያ ይከፈት ፣ የውጭ ባለሃብቶች ይግቡ ፣ ይፎካከሩ
ዋጋ መተመን ገበያ ውስጥ እየገባ እራሱ መሸጥ ሚናዎችን መቀነስ አለበት
ገበያው ለገበያው ይሰጥ
የዋጋ ንረት መቆጠር አለባችሁ
የበጀት ጉድለት አስተካክሉ
መልካም አስተዳደር እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ተቋማት ይገንባ

IMF የጠበቀ የቁጥጥር ስርዓት ቀላል የሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ስለሚያደርግ የኢኮኖሚ እድገት አይፈጥርም ባይ ነው።

ስለዚህ ለናተው ሲባል " በኢኮኖሚ እንድታድጉ፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲኖራችሁ " ነው ይህን ማድረግ ያለባችሁ የሚለው።

በኢኮኖሚ መርህ ተመሩና ሀገራችሁ እዲያድግ እፈልጋለሁ ነው የሚለው።

የሀገራት የእድገት አቅጣጫ እንዲስተካከል ይፈልጋል።

በዚህም ከድህነት የወጣ ሀገር ይመሰረታል ፣ ሁሌ የማይበደር ሀገር ይፈጠራል፣ ኢንቨስትመንት ጤነኛ የሆነበት፣ ምቹ ሀገር መፍጠር ይቻላል የሚል ሐሳብ አለው።

በመሆኑም የማክሮ ኢኮኖሚያ የመምራት አቅማችሁ ደካማ ከሆነ የምትመሩበትን ሁኔታ ይዤ መጣለሁ፣ የገንዘብ ፖሊሲው ጤነኛ ካልሆነ እኔ አግዛለሁ፦
• በቴክኒክ
• ፈንድ በማድረግ
• ብድር በመስጠት
• ብድር በማራዘም አግዛለሁ ይላል።

ስለዚህ " ራሳችሁን ችላችሁ ትቆማላችሁ ፣ ከመለመን ትወጣላችሁ ፣ ሁሌ አትበደሩም ፣ ዓለም አቀፍ እዳችሁ ይቀንስላችኋል፣ ለንግድ ለኢንቨስትመንት የምትመቹ ሀገር ትሆናላችሁ ያን ማድረግ ነው የምፈልገው ነው " የሚለው።

ሙስና እንዲቀንስ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲኖር ይፈልጋል።

IMF ይሄን ያደርጋል ብሎ የሚከራከሩለት አሉ።

IMF የሪፎርም ሰነዶቹን ለተለያዩ ሀገራት ነው የሚያቀርበው።

                                   ---

"IMF በእጅ አዙር ሌላ ዓላማ ነው ያለው" የሚሉ አካላት ምን ይላሉ ?

IMF ያደጉ ሀገራት ያሉበት ሼር ነው። ስለዚህ ያደጉ ሀገራት ድሃ ሀገራት ላይ ፍላጎታቸውን መጫን ይፈልጋሉ።

ብዙ ብድር በመስጠት የሚፈልጓትን ሀገር ተቆጣጥረው መያዝ ይፈልጋሉ።

እዳ ውስጥ እንድትቆይ በማድረግ መያዝ። በብድር ሰብሰብ መያዝ።

ብድር እና ድጋፍ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም ይፈልጋል።

በየሀገሩ እየሄደ " ልርዳችሁ " የሚለው በብድር ሰበብ ረጅም አመት በእዳ መያዝ ይፈልጋል።

ለአንድ ሀገር ብዙ ብድር ያውም ከእፎታ ዘመን ጋር ፣ ከዛም ምንም ወለድ የሌለበት ብድር ሲሰጥ ረጅም ዓመት ሀገሪቱ በእዳ ውስጥ እንድትቆይና በዛ ሀገር የፈለገውን ነገር ለመጫን እድል እንዲሰጠው ነው።

በእዳ የሚይዘው ያደጉት ሀገራት የድሃ ሀገራትን ማዕድን፣ ገበያውን ለምዕራባውያን መስጠት ስለሚፈልግ ነው።

ፊት ለፊት ከሚያደርጉት ስምምነት በተጨማሪ ከጀርባ የሚያደርጉት ስምምነት አለ። ያደጉ ሀገራት ድርጅቶቻቸው ያላደጉ ሀገራት ሄደው፦
° ማዕድን እንዲያገኙ
° ገበያ በቀላሉ እንዲያገኙ እድል እና ጫና የመፍጠር አዝማሚያ አለው።

እዳ ውስጥ የተዘፈቀ ሀገር በፖለቲካ በኩል የሚመጣለትን ፦
° ተጽኖ
° ጫና
° መከራከሪያ ሁሉ እንዲቀበል የማድረግ መሳሪያ ነው። አንዳንድ ሀገራት ግጭት ውስጥ ሲገቡ (ህልውናቸውን ለማስጠበቅም ቢሆን እንኳ)፣ ሰላምና መረጋጋት ሲርቃቸው እርዳታ እና ብድር ይይዛል። አይሰጣቸውም።

ዓላማው እድገት ብቻ አይደለም።

ተመሳሳይ ሪፎርም ለበርካታ ሀገራት ይሰጣል። ይህ የሀገራቱን ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ለግብጽም፣ ለናይጄሪያም፣ ለኢትዮጵያም የሚመክረው ተመሳሳይ ነው። ብዙ ድሃ ላለበት ሀገር እና ትንሽ ድሃ ላለበት ሀገር ተመሳሳይ ምክር ይሰጣል።

ምሳሌ ፦ ድጎማ #እንዲቀንስ_ያበረታታል። በደካማ ኢኮኖሚ ያለው ሀገር ሳይቀር መንግስት ከድጎማ ወጥቶ ገበያው በራሱ እንዲንቀሳቀስ ይመክራል። ይሄ ደግሞ በርካታ ሰዎች ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ውጭ ይሆናሉ።

ነጻ ገበያ እያለ ያውጃል ግን ያላደጉ ሀገራት እሱን ሲሞክሩ ብዙ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ የሚገቡ ማህበረሰቦች ይፈጠራሉ።

የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመጠበቅ እንኳን መንገድ እንዳይኖር ልቀቁት ይላል። በዚህም ትንንሽ አማራቾች ከውጭ በሚመጣ ምርት እና አምራች ጋር መፎካከር አቅቷቸው ከንግድ ውጭ ይሆናሉ።

ምክሮቹ ድህነትን የሚያበረታቱ የመሆን እድል አላቸው።

በሚል የሚከራከሩ አሉ።

IMF ግን አንዳንድ ሪፎርሞች ሁሉ ወዲያው ለውጥ እንደማያመጡ በማመን የራሱ መከራከሪያዎች አሉት።

ያንብቡ: https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-04

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ከኦሎምፒክ ውድድር ጋር በተያያዘ ገና ከጅምሩ አንስቶ ጭቅጭቅ ፣ ቅሬታ ፣ ንትርክ ፣ በሚዲያ በኩል የኃይል ምልልስ የነበረበት ነው።

የስፖርት ቤተሰቡ ሆነ ዜጋው የነበረውን ነገር በአንክሮ ሲከታተል ነበር።

" እስቲ እዛው ፓሪስ ላይ ሲደርሱ ነገሮችን ጸጥ ይላሉ፣ ለሀገር ክብር ሲሉ ሁሉም በስምምነት ያለ ጭቅጭቅና ቅሬታ ይሰራሉ " ቢባልም ዛሬም ድረስ ቅሬታዎች እንደ ጉድ እየተሰሙ ነው።

ኢትዮጵያ ስሟ በገነነበት በዚህ ስፖርት ዘርፍ እንዲሁም ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብንና ባንዲራን ወክሎ ሄዶ በአንድነት አለመስራት፣ ቅሬታዎችና ስሞታዎች መብዛት እጅግ አሳዛኝ ነው።

ሀገርም ህዝብም መዋረድ የለበትም ፤ እውነት ለህዝብ ከሆነ የሚሰራው ህዝቡን አክብሩት።

በዚህ ጭቅጭቅ እና የሚዲያ ንትርክ ውጤት ቢጠፋ ማነው የሚጠየቀው ? ሁሌ ውድድር በመጣ ቁጥር ጭቅጭቅ እና ቅሬታ መስማት አያሳፍርም ? እውነት ለሀገር ነው የሚሰራው ?

አሁንም ገና ውድድሩ ብዙ ይቀረዋልና ህዝብን አክብሮ ለአንዲት ሀገር ሲባል በጋራ መስራት ይገባል። ሀገሪቱን እና ባንዲራውን አክብሩና አስከብሩ።

ችግር ከተፈጠረና ውጤትም ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ምንም ተቀባይነት አይኖረውም።

የኦሎምፒክ መረጃዎችን በቲክቫህ ስፖርት ይከታተሉ - https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

#Ethiopia

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች ለሁላችንም በታላቅ ቅናሽ ከዲኤስቲቪ !

ዛሬውኑ የዲኤስቲቪ ዲኮደርዎን ከ800 ብር ቅናሽ ጋር በመግዛት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፣ ቻምፒዮንስ ሊግ ፣ ላሊጋ ፣ ሴሪ አን ጨምሮ የሚወዱትን ክለብ በሚመርጡት ፓኬጅ ላይ እንደየምርጫዎ በዲኤስቲቪ ይዝናኑ!

ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች፣ ሁሉንም የቡድን ወኔ፣ ሁሉንም ትንታኔዎች ... ሁሉም በዲኤስቲቪ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#DStvEthiopia
#ሁሉምያለውእኛጋርነው
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture


የውበት እና የጥራት ዳር ድንበር!


አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282

👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture

#yonatanbtfurniture #furniture #modernfurniture #kitchen #kitchencabinet
" 75 ሺህ ታጣቂዎች ወደ ህብረተሰቡ ለመቀላቀል ያለመ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

ትላንትና በትግራይ ታዋጊዎች ወደ ህብረተሰብ ለመመለስ ያለመ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።

መድረኩን አዘጋጅተው የነበረው የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን እና USAID ኢትዮጵያ በትብብር ነበር።

በዚህም መድረክ የተገኙት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ፤ " በ2015 ዓ.ም ወደ ህብረተሰብ ይቀላቀላሉ የተባሉ 50 ሺህ ታጣቂዎች ነበር በድጋፍና የማቋቋምያ እጦት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ " ብለዋል።

" ባለፈው እጅግ ደም አፋሳሽና አሰቃቂ ጦርነት ብዙ ነገሮች ወድመዋል ተመሳቅለዋል የተሰዋ አካሉ የጎደለ ፣ ንብረቱ ወድሞበት ከሃብት ወደ ደህነት የወረደ ብዙ ነው " ብለዋል።

ጀነራል ታደሰ " ወደ ህብረተሰቡ የሚቀላቀሉ ታጣቂዎች ከባባድ ችግሮች ያለባቸው ስለሆኑ የቀናጀ ሁለንተናዊ ማቋቋምያ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።

" ታጣቂው ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅሎ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ አስተሳሰብ ርቆ የሰላምና  ፀጥታ ጠባቂ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ እድገት የሚጠበቅበት ሃላፊነት እንዲወጣ ከተፈለገ ድጋፍ ፣ ክብርና እውቅና ያሻዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ታሳቢ ያደረገ 75 ሺህ ታጣቂዎች ወደ ህብረተሰቡ ለመቀላቀል ያለመ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

#Tigray

@tikvahethiopia
#Ethiopia

° " በርካታ መሰረታዊ ሸቀጥ የያዙ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ጣቢያዎች ተንቀሳቅሰዋል " - መንግሥት

° " የዋጋ ጭማሪ ቁጥጥር የአንድ ሰሞን ወሬና ወከና ሆኖ በዛው ጨምሮ እንዳይቀር ተከታተሉልን ፤ከዚህ ቀደም በዘይት የሆነውን አይተናል። ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም " - የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ
(ከአ/አ)

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደረገ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ መሰረታዊ በሚባሉ ሸቀጦች ላይ ጭማሪ፣ እንዲሁም " የለም " የማለት ነገር እያጋጠማቸው እንደሆነ ዜጎች ተናግረዋል።

ይህም ሁኔታ እያማረራቸው እንደሆነ ያመለክታሉ።

በተለይም አንዳንድ ምርቶችን ለመግዛት ሲሄዱ ከፍ ያለ ብር ተጨምሮ እንደሚነገራቸው ፤ ከዚህ ባልፈ ደግሞ " አሁን ምርት የለም " እየተባሉ እንደሚጉላሉ በምሬት ይናገራሉ።

መንግሥት በበኩሉ ገበያው እንዳይናጋ የቁጥጥር ስራ እየሰራ እንደሆነ እየገለጸ ነው።

ዋጋ ጨምረው የተገኙ በርካታ ሱቆችን ከማሸግ በተጨማሪ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠረ ሸቀጥ በገፍ እንዲገባ እየሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ እያሳወቀ ይገኛል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በማሻሻያው ምክንያት የገበያ መናጋት እንዳይፈጠር እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ገልጿል።

ለአብነት በጉምሩክ ጣቢያዎች መሰረታዊ ሸቀጥ ጭነው የቆሙ ተሽከርካሪዎች እንዲወጡ መፍትሄ እየተሰጠ እንደሆነ አመልክቷል።

በተለይ ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ባወጣው የቫት ክፍያ ምክንያት ቆመው የሚገኙትን እንዲንቀሳቀሱ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት ፦
➡️ 101 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 44,000 ሌትር ዘይት የያዙ ፤
➡️ 80 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 32,000 ኩንታል ስኳር የጫኑ
➡️ 23 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 9,200 ኩንታል ሩዝ የጫኑ
➡️ 69 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 27,600 ኩንታል የስንዴ ዱቄት የጫኑ በጥቅሉ 273 ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው የጉምሩክ ስነስርዓት ጨርሰው ወደ መዳረሻቸው እንደተንቀሳቀሱ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በነገው እለትም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሰረታዊ ሸቀጥ ከጉምሩክ ጣቢያዎች ወደ መላው ሀገሪቱ አከባቢዎች እንደሚጓጓዝም አሳውቀዋል።

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች " ዶላር ጨምሯል " በሚል በተለይ መሰረታዊ ምርቶች ላይ የሚታየው ጭማሪ ዜጎችን እያማረረ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

በተለይ እንደ ዘይት፣ ስኳር፣ ያሉት ምርቶችን አንዳንድ ቦታ ማግኘት እንደማይቻል ሲገኝ ደግሞ ዋጋው ጨምሮ ነው ለሸማች የሚነገረው።

ቃላቸውን የሰጡን የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ ፥ " እኔ ደመወዜ አንድም ጊዜ ሳይጨምር ይኸው ዘይት ጨምሮ ጨምሮ በሺህ ቤት ገብቷል። እንዴት መኖር እንዳለብኝ አልገባኝም። ደመወዘኔ ምኑን ከምኑ እንደማደረገውም ጠፍቶብኛል " ሲሉ በሀዘን ተናግረዋል።

" የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር የሚጨምረው ዋጋ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ወሬና ወከባ ይሆንና ዋጋው በዛው ጨምሮ ጣራ ነክቶ ይቀራል ፤ ይህ ከዚህ በፊት በዘይት አይተነዋል " ብለዋል።

" ነጋዴው አያዝንልን፣ የመንግስት ሰዎች ተገቢና ዘላቂ ቁጥጥር አያደርጉልን፣ መፍትሄ አይሰጡን፣ የሚመጣው ሁሉ ግን እኛ ላይ ያርፋል። እንደ ከዚህ ቀደሙ ዋጋ ጨመረ ተብሎ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ግርግር ሆኖ በዛው ዋጋው ተሰቅሎ እንዳይቀር መደረግ ያለበት ይደረግ፤ ኑሮው በጣም ከብዶናል። " ሲሉ አክለዋል።

#Tikvahethiopia

@tikvahethiopia
#DireDawa : ዶክተር ጌታቸው ጫካቤኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዶ/ር ጌታቸው ጫካቤኛ በድሬዳዋ የመጀመሪያው የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ነበሩ።

ከአርባ ዓመታት በላይ በድሬዳዋ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በህጻናት ህክምና ስፔሻሊስትነት ፣ በህክምና ዘርፍ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበው ወገናቸውን አገልግለዋል።

በስራ ልምዳቸውም በርካቶችን አብቅተዋል።

ድሬዳዋ " ባለውለታዬን አጣኋቸው " ብላለች።

ከንቲባ ከድር ጁሀር  " ለረጅም ዓመታት በከተማው የህፃናት አለኝታ በመሆን ጡረታ እስኪወጡ የድሬዳዋን ህዝብ በፍቅር ነው ያገለገሉት " ሲሉ በህልፈታቸው የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

በዶ/ር ጌታቸው የህክምና ጥበብ ከህመማቸው የተፈወሱ በርካታ ህፃናት እና ወላጆች እንደሆኑ ገልጸው ሀዘኑ የመላው ከተማ እንደሆነ በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።

#DireDawa #ድሬ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ° " በርካታ መሰረታዊ ሸቀጥ የያዙ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ጣቢያዎች ተንቀሳቅሰዋል " - መንግሥት ° " የዋጋ ጭማሪ ቁጥጥር የአንድ ሰሞን ወሬና ወከና ሆኖ በዛው ጨምሮ እንዳይቀር ተከታተሉልን ፤ከዚህ ቀደም በዘይት የሆነውን አይተናል። ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም " - የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ (ከአ/አ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደረገ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ መሰረታዊ በሚባሉ…
🔈 #የዜጎችድምጽ

የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ ፦

" እኔ ደመወዜ አንድም ጊዜ ሳይጨምር ይኸው ዘይት ጨምሮ ጨምሮ በሺህ ቤት ገብቷል። እንዴት መኖር እንዳለብኝ አልገባኝም።

ደመወዘኔን ምኑን ከምኑ እንደማደረገው ጠፍቶብኛል።

የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር የሚጨምረው ዋጋ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ወሬና ወከባ ይሆንና ዋጋው በዛው ጨምሮ ጣራ ነክቶ ይቀራል ፤ ይህ ከዚህ በፊት በዘይት አይተነዋል።

ነጋዴው አያዝንልን፣ የመንግስትም ሰዎች ተገቢና ዘላቂ ቁጥጥር አያደርጉልን ፣ የሚመጣው ሁሉ ግን እኛ ላይ ያርፋል።

እንደ ከዚህ ቀደሙ ' ዋጋ ጨመረ. ' ተብሎ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ግርግር ሆኖ በዛው ዋጋ ሁሉ ተሰቅሎ እንዳይቀር መደረግ ያለበት ሁሉ ይደረግ ፤ ኑሮው በጣም ከብዶናል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM