#እንድታውቁት #ሀዋሳ #ክልከላ
በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ ባለ ሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና የሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር #ተከለከለ።
ሰሞኑን በሀዋሳ ከመዝናኛ መልስ እየደረሰ ያለውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሲባል ከምሽቱ 3:00 በኃላ ባለሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪው ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፦
° ምክንያት ?
° ክልከላው ለምን አስፈለገ ?
° በማህበረሰቡ የእለት ተእለት ህይወትስ ላይ የሚያሳድረዉ ጫና አይኖርም ? ወይ ስንል ኢንስፔክተሩን ጠይቋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፤ " ሁሉንም ያደረግነው ለማህበረሰቡ ደህንነት ነው " ብለዋል።
" አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እየተስተዋለ ነው " ሲሉ ገልጸው ከአደጋዎቹ አብዛኛዉ በባለሦሰት እግር ባጃጅና በባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል የሚደርስ እንደሆነ አስረድተዋል።
" በዚህ አመት ብቻ በምሽት በሞተር ሳይክል የደረሰዉ አደጋ የሚያስገርም ቁጥር ያለው ነው " ያሉት ኢስፓክተር ተስፋዬ በቁጥር ስንት ? የሚለውን ወደፊት ዳታውን አጠናቅረዉ ለማህበረሰቡ የማሳየት እቅድ እንዳለቸዉ ጠቁመዋል።
ከአደጋዎቹ ውስጥ በአብዛኛው የሚከሰቱት በምሽት መሆኑን ጠቅሰው ፤ " ጠጥቶ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር ትልቁ ምክኒያት ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም በመንግስት ሞተር ሳይክሎች ሳይቀር ሶስትና ከዚያ በላይ ሆኖ መንቀሳቀስ አደጋ እየፈጠረ ነው ይህን ችግር ለመቀነስ ሲባል #ክልከላው ወጥቷል " ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ፤ " የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የወንጀል መፈጸሚያ እየሆኑ ነው " ያሉት ኢንስፔክተሩ ፤ " ለአብነት ኮንትራት ተብለዉ በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ እና የሌሎችም ወንጀሎች ምንጭ ሆነው ተገኝተዋል " ብለዋል።
" ጥንቃቄ ለራስ በመሆኑ ማህበረሰቡ ለራሱ ሲባል የወጣዉን ክልከላ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ " ሲሉ አሳስበዋል።
" እለት ተእለት የሚከሰተው ዘግናኝ የትራፊክ አደጋ እንዲቆም የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል " ብለዋል።
ክልከላው የሚያበቃበትን ጊዜን በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia

#እንድታውቁት
በበዓሉ ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምንድናቸው ?
- በምግብ ማብሰያ ወይም በማዕድቤት አካባቢ የኤሌክትሪክ ፣ የቡታጋዝ ፣ የከሰል ምድጃዎችን በአግባቡ እና በጥንቃቄ ይጠቀሙ።
- በገበያ ማዕከላት የገበያተኛውን ቀልብ ለመሳብ የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዲኮሬሸኖች ቃጠሎ እንዳያስነሱ ይጠንቀቁ።
- ሻማ እና ጧፍ ሲጠቀሙ ከተቀጣጣይ ነገር ያርቁት።
- ካምፋዬር ሚያዘጋጁ ከሆነ ከአካባቢው ከመራቅዎ በፊት በደንብ መጥፋቱን ያረጋግጡ።
- በፍጹም ጠጥተው አያሸከርክሩ።
ለማናቸውም የእሳት እና የድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎት የሚከተሉትን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልክ ቁጥሮች መዝግበው ይያዙ።
24 ሰዓት መደወል ይችላሉ።
1. ማዕከል - 0111555300/ 0111568601
2. አራዳ - 0111567004/ 0111560249
3. ቂርቆስ - 0114663420/21
4. አዲስ ከተማ - 0112769145/46
5. ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 0114425563/64
6. አቃቂ ቃሊቲ - 0114340096 / 0114343063
7. ቦሌ - 0116630373/74
8. ኮልፌ ቀራንዮ- 0113696085/ 0113696104
9. ጉለሌ - 0112730731/ 0112730653
10. ቦሌ ሰሚት - 0116680846/ 0116680760
11. ልደታ - 0115589043/ 0115589533
(በእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቀረበ)
እንኳን አደረሳችሁ !

#እንድታውቁት #አዲስአበባ
ዛሬ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ' ከፖሊስ ስራ ' ጋር በተያያዘ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮግራም አለ።
ይህ ተከትሎ መንገዶች ተዘግተዋል።
የተዘጉት መንገዶች ፦
- ከልደታ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከጠማማ ፎቅ በንግድ ምክር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከገነት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከሰንጋ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከቡናና ሻይ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ሲሆኑ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ያሳወቀው።
በመሆኑም ፦
° በስራ ላይ ምትገኙ አገልግሎት የምትሰጡ አሽከርካሪዎች ፣
° ወደ ስራ እየገባችሁ ያላችሁ ሰራተኞች
° ከስራ ወጥታችሁ ወደ የቤታችሁ እየሄዳችሁ ያላችሁ ነዋሪዎች ይህን መረጃ ተመልክታችሁ አማራጭ መንገድ ተጠቀሙ።
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት #አዲስአበባ ዛሬ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ' ከፖሊስ ስራ ' ጋር በተያያዘ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮግራም አለ። ይህ ተከትሎ መንገዶች ተዘግተዋል። የተዘጉት መንገዶች ፦ - ከልደታ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ - ከአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ - ከጠማማ ፎቅ በንግድ ምክር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ - ከገነት መብራት…
#እንድታውቁት #አዲስአበባ
' ሜክሲኮ ' በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት በነበረ ፕሮግራም ተዘግተው የነበሩ መንገዶች አሁን ላይ ክፍት ናቸው።
በምሽትና ለሊት የትራንስፖርት አገልግሎት የምትሰጡ የቤተሰብ አባላቶቻችን ይህ መረጃ ይጠቅማችሁ ይሆናል።

#እንድታውቁት #AddisAbaba
በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መዚህ መሰረት ፡-
- ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
እንዲሁም #በውስጥ_ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ #በየዕለቱ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#AddisAbabaPolice

የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት_እንደሚቀጥል አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ - ነጭ ናፍጣ ➡ ብር 79.75 በሊትር - ኬሮሲን ➡ ብር 79.75 በሊትር…
#እንድታውቁት
ከነገ ግንቦት 28 /2016 ዓ/ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።
ስራ ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን ➡️ ብር 78.67 በሊትር
- ነጭ ናፍጣ ➡ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ➡ ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ➡ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 61.16 በሊትር ነው።

#እንድታውቁት🚨
2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ።
1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56
2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127
የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።

" መኪና አቁሞ መሄድ ፍጹም የተከለከለ ነው " - ፖሊስ
የኮሪደር ልማት ስራዎቻቸው ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ከ5ቱ የኮሪደር ልማት ስራዎች ውስጥ ፦
➡️ ከአራት ኪሎ እስከ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያን መታጠፊያ
➡️ ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት እንዲሁም
➡️ ከቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም በደጎል አደባባይ እስከ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን አቅጣጫ መንገዱ ትላንት ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሔድ ፍጹም ክልክል መሆኑን አሳውቋል።