TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቿን ከነገ ጀምሮ በተቀናጀ መንገድ የመመለስ ሥራ እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግሥት ልዑክ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና የጂዳ ቆንስላ ጀነራል ሰራተኞች እና የኮሙኒቲ አስተባባሪዎች ጋር በመወያየት በተመላሾች መለየት እና መመለስ ላይ…
#Update

“ ከሳዑዲ ተመላሾች በመደበኛው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተካተዋል ” - ሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ ዜጎቿ እየመለሰች እንደምትገኝ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር መካላከልና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍና ክትትል ሂደት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ተግይበሉ በሰጡት ቃል ፣ " በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ስራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

ዛሬ እና ትላንት ብቻ 1913 ሰዎች ተመልሰዋል።

ምን ያህል ወገኖችን ለመመለስ ታስቧል ? ሲል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ያቀረበላቸው አቶ ደረጃ “ በአጠቃላይ ለመመለስ የታቀደው ወደ 70 ሺሕ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ነው። በሚቀጥሉት 3 እና 4 ወራት ውስጥ በስምንት 3 ወይም 4 ቀናት በሚደረግ በረራ የማስመለስ ዕቅድ ተይዟል ” ሲሉ መልሰዋል።

70 ሺሕ ወገኖችን ከመመለስ ባሻገር ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት ለማቋቋም ምን ታቅዷል ? በሚል ላነሳነው ጥያቄ ፥ “ በተለይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ የሳዑዲ ተመላሾች በመደበኛው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተካተዋል ” ብለዋል።
 
በዚህ ወቅት በመደበኛው ሆነ በኢመደበኛው የሄዱ በአጠቃላይ በሳዑዲ አረቢያ ምን ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ አብዛኛዎቹ መደበኛ ባልሆነ ስርዓት ስለሆነ የሚሄዱት ይህን ይህል ናቸው ተብለው በመንግሥት አይታወቅም ” ብለዋል።

በሳዑዲ በጣም በርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንዳሉ፣ ነገር ግን ሁሉም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት የሄዱ ናቸው ተብሎ ስለማይጠበቅ ከሳዑዲ መንግሥት ጋር በተደረገ ድርድር እየተመለሱ ያሉት በኢመደበኛ ፍልሰት የሄዱትንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ሚገኙትን እንደሆነ አስረድተዋል።

በኢመደበኛ መንገድ የሚሄዱ ዜጎች፦
- የሞት አደጋ፣
- ሴቶች ለፆታዊ ጥቃት፣
- በደላላ ገንዘባቸውን የመበዝዘብ ችግር እንደሚደርስባቸው የገለጹት አቶ ደረጀ፣ “ መደበኛውን የፍልሰት ስርዓት ተከትለው የሚሄዱባቸውን ሁኔታዎች ከመንግሥት አካላት መረጃ ወስደው እንዲጠቀሙ አደራ እንላለን
” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia