TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara

በአማራ ክልል ከመንግሥት የፀጥታ ኃይል ጋር የትጥቅ ትግል እያደረጉ የሚገኙት እና ታጥቀው የሚንቀሳቀሱት እነ ምሬ ወዳጆን ጨምሮ 27 ተከሳሾች #የጋዜጣ_ጥሪ እንዲደረግላቸው እና እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰማ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የህገ መንግስትና በህገ መንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ፤ በሽብር ወንጀል በተከሰሱት እነ ዶክተር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ ተካተው ያልቀረቡ ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸውና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ማዘዙን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የጋዜጣ ጥሪ ይደረግላቸውና ይምጡ የተባሉት በአሁን ሰዓት ነፍጥ አንግበው በአማራ ክልል እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ምሬ ወዳጆን ጨምሮ 27 ተከሳሾች ናቸው።

እነ ዶክተር ወንደሰን አሰፋ እና መስከረም አበራን ጨምሮ 23 ተከሳሾች በአማራ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ታስረውና " በሽብር ወንጀል " ተከሰው የፍርድ ሂደታቸው እየታየ እንደሆነ ይወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በእነ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘውና በእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መዝገቦች ቀርበው የነበሩ ክሶች እንዲቋረጡ ተወሰነ። የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና በእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መዝገቦች ቀርበው የነበሩ ክሶች እንዲቋረጡ መወሰኑን አሳውቋል። ክሶቹ እንዲቋረጡ የተወሰነው " ለህዝብ ጥቅም " ነው ብሏል። በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ…
ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ከእስር ተለቀቁ።

የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው፤ ከ5 ዓመት ከ4 ወራት እስር በኋላ ዛሬ ከሰዓት ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለ" ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ጠበቃቸው አቶ ሓፍቶም ከሰተ የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ የተለቀቁት ፤ አብዛኛውን የእስር ጊዜያቸውን ካሳለፉበት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት መሆኑን አስረድተዋል።

ከእስር ሲለቀቁ በቤተሰቦቻቸው አቀባበል እንደተደረገላቸው ጠበቃቸው ተናግረዋል።

ሜጀር ጄነራል ክንፈ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ህዳር 3/2011 ዓ.ም. ነበር።

ከእስር የተፈቱት በእርሳቸው ላይ ቀርበው የነበሩ ተደራራቢ ክሶች በፍትህ ሚኒስቴር መቋረጣቸውን ተከትሎ ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር ክስ የተቋረጠው " ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም " ሲባል ነው ማለቱ ይታወሳል።

በትላንትናው ዕለት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ ከእስር መፈታታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ወንጂ🕯

ለ2 ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ 5 የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የፋብሪካው ኃላፊ ተናገሩ።

እኚሁ ኃላፊ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል።

" አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው " ብለዋል።

ከተገደሉት መካከል 3ቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ዛሬ ተፈፅሟል።

ሁለቱ ሠራተኞች አንደኛው ከአዳማ የመጣው ቀብሩ ዛሬ የተፈፀመ ሲሆን ሌላኛው ከደሴ የመጣው ግለሰብ አስከሬን ወደ ስፍራው ተልኳል ተብሏል።

4ቱ ሠራተኞች በፋብሪካው ውስጥ በትራክተር ኦፕሬተርነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እንደሆኑም ተገልጿል።

ሌላኛው የኤሌክትሪክ ሠራተኛ (ፎርማን) ወጣት ሲሆን በቅርብ የተቀጠረ እና ለአንድ ዓመት ያህል በፋብሪካው አገልግሏል።

አንደ ኃላፊው ገለጻ ከሆነ ግለሰቦቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት የአዳር ስር ላይ ምሽቱን አሳልፈው ጥዋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን " ዶዶታ " ከሚባለው ፋብሪካው ከሚገኝበት ስፍራ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል።

ሠራተኞቹን ያገቷቸው ሰዎች ገንዘብ ጠይቀው እንደነበር ? ወይም የጠየቋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ዝርዝሩን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ነገር ግን ፋብሪካው ከአጋቾቹ በኩል ምንም ነገር እንዳልተጠየቀ ገልጸው፣ ወዲያውኑ ለመንግሥት አካል ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

ፓሊስም ሠራተኞቹን ለማስለቀቅ እየተከታታለ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው ነገር ግን አስከሬናቸው ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት አካባቢ ተገኝቷል ብለዋል።

ስለ ግድያው እንዴት ? እና ስንት ሰዓት ? ተፈጸመ የሚለውን ባያውቁም ምናልባትም ትናንት ምሽት ተገድለዋል ብለው እንደሚጠረጥሩ የተናገሩት ኃላፊው ሰራተኞቹ መገደላቸውን ሰምተው ወደ አካበቢው ሲሄዱ አስከሬናቸውን አግኝተናል ብለዋል።

በፋብሪካው እንዲህ እገታ ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑን እና እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበርም አስረድተዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወንጂ🕯 ለ2 ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ 5 የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የፋብሪካው ኃላፊ ተናገሩ። እኚሁ ኃላፊ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል። " አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው " ብለዋል። ከተገደሉት…
#ወንጂ🕯

ለስራ በወጡበት #በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኃላ ተገድለው ከተገኙት ዜጎች መካከል አንዱ አቶ ግርማ በላቸው እንደሚባሉና የኢትዮ ስኳር ፋብሪካ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አ/ማ የስራ ባልደረባ እንደነበሩ ተነግሯል።

ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው በታጣቂዎች ታግተው ፤ በግፍ ተገድለው የተገኙት ለወንጂ ስኳር ፋብሪካ ድጋፍ ለመስጠት በወጡበት ነው።

በኦሮሚያ ክልል ፤ በቅርቡ የጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 አባቶች ታግተው በግፍ መገደላቸው የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ?

ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱና የክልሉ አስተዳደራዊ ወሰን እንዲከበር ጠይቀዋል።

በጥቅሉ ያነሷቸው ጥያቄዎች  ምንድናቸው ?

- የመከላከያ አባላት የነበሩት ጨምሮ ሌሎች የፓለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤
- የትግራይ ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት የወሰዱት የብድር ወለድና ቅጣት ይነሳ፤
- የመንግስት ሰራተኞችና የጡረተኞች ውዙፍ ደመወዝና አበል ይከፈል፤
- ከትግራይ ሰራዊት (TDF) ለተሰናበቱ ታጣቃዊች ማቋቋምያ ይከፈል፤
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር፤
- ከረሃብ ጋር በተያያዘ እርዳታ ይደረግ ፤
- የህወሓት የህጋዊነት ጥያቄ ለምን ዘገየ ?
የሚሉና ሌሎች ይገኙባቸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምን መለሱ ?

ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ ብዙ ስኬቶች እንዳሉ አሁንም ግን የሚቀር ብዙ እንዳለ ገልጸዋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በጥይት ሰው እንዳልሞተ ተናግረዋል። በትግራይ መረጋጋት ፤ መንግሥት መመስረት ፣ ህወሓት (TPLF) ከሽብርተኝነት መፋቅ የስምምነቱ ውጤት ነው ብለዋል።

ከስምምነቱ በኃላ በርካታ ቢሊዮን ብሮች በካሽም በቁሳቁስም ወደ ትግራይ ክልል መላኩን ገልጸዋል።

እስረኞችን መፍታት በተመለከተ ፦

" ስብሃትን ፈትቼው የለም እንዴ ? ፣ አልፈልግም እንዲታሰሩ።

የመከላከያን በተመለከተ እራሱ ይነግራችኋል (ዶ/ር አብርሃምን ማለታቸው ነው) አላውቅም በእኔ እውቀት #አንድም_የታሰረ_ሰው_የለም።  ከስራ ያቆምናቸው ታጋዮች ነበሩ እርቁ ሲፈፀም መፍታት እኮ አይደለም ወደቦታቸው ነው የመለስናቸው። አሃዱ አለቃ ናቸው ሁሉም በየቦታው በየደረጃው ኃላፊዎች ናቸው መከላከያ ውስጥ ...

እስረኛ በሌብነት ምክንያት ካለ አላውቅም ፤ እስረኛ ሰው ገድሎ የታሰረ ወንጀለኛ ካለ አላውቅም። ከግጭቱ ጋር የሚያያዝ ግን በመከላከያ ወጥተው የነበሩት ተመልሰው መከላከያ ውስጥ ገብተዋል።

እኛ እንደዚህ አይነት ፍላጎት የለንም። የምናውቀውም የለም። እኛ እስረኛ ፈተን ስራ አስፈፃሚ ፈተን ጌታቸው ጋር የቀሩ እስረኞች ነበሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያልፈታቸው ። "

ትግራዋይ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ፤ ተፈናቃዮች በስምምነቱ መሰረት ቤታቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የአማራ ክልሉ አቶ አረጋ ፣ ዶ/ር አብርሃም ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰሞኑን ንግግር ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ የተፈናቀሉ ሰዎች በሙሉ ቤታቸው እንዲመለሱ ነው ያሉ ሲሆን " በማንኛውም ሰዓት ነገ ሁመራ ያለው ቤቴ መመለስ እፈልጋለሁ የሚል ካለ እኛ ለመመለስ ዝግጁ ነን " ብለዋል።

#መከላከያ በአካባቢው የትግራይም ይሁን የአማራ ፀጥታ ኃይል እንዳይኖር ኃላፊነት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

ሁሉም ሰዎች ወደ ቤታቸው #ከተመለሱ_በኃላ እራሱ ህዝቡ አስተዳዳሪውን እንዲመርጥ እንደሚደረግና ከተረጋጋ በኃላ ህዝቡ ሪፈረንደም በማድረግ " እኔ አማራ ነኝ ፤ እኔ ትግራይ ነኝ " የሚለውን እንደሚወስን ተናግረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ተፈናቃዮች መቐለ ፣ ሽረ መቀመጥ እንደማያስፈልጋቸውና ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ረገድ ፌዴራል መንግሥት የሚጠበቅበትን እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በነበረው ሁኔታ ውጭ ሀገር የሄደ ባለሃብት ካለ መመለስ ይችላል ፣ ከባላሃብቶች ጋር በተያያዘ ችግር ካለም ይፈታል ብለዋል።

#ረሃብን በተመለከተ ጉዳዩን ፖለቲካዊ ማድረግ እንደማይገባና ትግራይ ተርባ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በልቶ ጠግቦ እንደማያድርግ ገልጸዋል። " ጌታቸውንም ወቅሼዋለሁ ረሃብ ካለ መደወል ነው እኔ ጋር ያለ አምጡ አግዙ ማለት ነው ቀላል ነው በትዊተር ከሆነ ግን እኛ በትዊተር አንነጋገርም ብሄዋለሁ ለሌሎች ነው የነገርከው እንጂ እኔ አልሰማሁም " ሲሉ ገልጸዋል። " ረሃብ ረሃብ ችግር ችግር አለ የሚል ፖለቲካ " ማድረግ ተገቢ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሚቴ ተቋቁሟል ሄዶ ጥናት አድርጎ መደረግ ያለበት ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/TPLF እውቅናን በተመለከተ ጉዳዩ የምርጫ ቦርድ ቢሆንም " በእኛ በኩል መሰጠት አለበት ብለን እናምናል ፤ በቅርብም #አነጋግረናቸዋል የሚፈታ ይመስለኛል ፤ ብዙም ከባድ አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#ከባንክ ጋር በተያየዝ ጉዳዩ ውስብስብ መሆኑን በማስረዳት መናገር ያልፈለጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢሯቸው አማካሪዎች እና ጉዳዩን በቀጥታ የሚያዩ የሚመለከታቸው አካላት ተነጋገረው የሚቻል ነገር ካመጡ ለማገዝ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ከባንክ ብድር ጋር በተያያዘ " ብድር ተከለከልን " የሚሉ ባላሃብቶች ካሉ ከዶ/ር አብርሃም እና ከሌሎች የሚመደቡ ሰዎች ጋር እንዲነጋገሩ አቅጣጫ ሰጥተው አልፈዋል። በመንግሥት ፖሊሲ ሊፈታ የሚችል ካለ ግን እንደሚታይ ገልጸዋል።

በኤርታራ መንግሥት (በሻዕብያ ኃይል) ስለተያዙ መሬቶች በተመለከተ ፤  የፌዴራል እና ከትግራይ የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙን በዚህም የሀገር መከላከያ ከትግራይ ጓዶች ጋር በመሆን ቦታዎችን እንዲያዩ እንደሚደረግ ገልጸዋል። " #ከአልጀርስ_ስምምነት ውጭ የሆነ ካለ ሪፖርቱ ሲመጣ እናያለን ፤ ማንም የማንንም ቦታ በኃይል ይዞ ለዘላለም መኖር አይችልም እንዳንዋጋ፣ ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር ትርፍ ነገር የተካሄደ ካለ አይተን ቦታውን ለይተን ኦፊሻሊ እነዚህ ነገሮች ይስተካከሉ ብለን በንግግር መልክ ልናበጅ እንችላለልን " ብለዋል። ውጤቱ ታይቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተግረዋል።

➡️ የጡረተኞችን ውዝፍ ክፍያን በተመለከተ ምንም ሳይሉ አልፈው በአቶ ጌታቸው በኩል ያለውን ነገር እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ሌሎችም አንዳንድ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ በቀጥታ አስተያየት ባይሰጡም በጥቅሉ በክልሉ ካሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በውይይት በምክክር እንደሚፈቱ ቃል ገብተዋል።

#TikvahFamilyMekelle
#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
*SafaricomEthiopia

የመጨረሻው ዙር ተረክ አድራጊዎች ታውቀዋል! እንኳን ደስ ያላችሁ !
ደንበኛ ከአርሲ ፤ ነጋዴ ከጅግጅጋ መኪናዋን ተረክ አድርገዋታል!
ከዲላ ፣ከሐረር አራተኛ ፣እንዲሁም ከእንጅባራ ባጃጇን ተረክ አድርገዋታል!

M-PESA ላይ እንመዝገብ ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ እንሸለም!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
ንግድ ባንክ አገልግሎት መቋረጡን ገለጸ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦
- በቅርንጫፎች፥
- በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው አሳውቋል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በርብርብ እየተሰራ ነው ያለው ባንኩ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

ለተፈጠረው መጉላላትም #ይቅርታ ጠይቋል።

ከአንድ ወር ገደማ በፊት በፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት ሁሉም አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደነበር እና በሰዓታት ውስጥ ችግሩ መፈታቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ንግድ ባንክ አገልግሎት መቋረጡን ገለጸ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦ - በቅርንጫፎች፥ - በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ - በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው አሳውቋል። አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በርብርብ እየተሰራ ነው ያለው ባንኩ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል። ለተፈጠረው መጉላላትም #ይቅርታ…
#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ምክንያት ተቋርጦ የነበረው #የቅርንጫፎች_አገልግሎት መጀመሩን አሳውቋል።

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም አሳውቋል።

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ፦
- ኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- ሞባይል ባንኪንግ፥
- ሲቢኢ ብር ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን ገልጾ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ ጠይቋል።

ባንኩ በምን ምክንያት የሲስተም ችግር እንደተፈጠረ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

@tikvahethiopia
#ግሎባል_ባንክ
መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ! የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል፦
1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.iss.one/global_bank_referral_bot?start=476862805
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡

ሽልማቱ በየሳምንቱ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡
ለተጨማሪ ጥያቄዎች በነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥር 8118 ይጠቀሙ!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ምክንያት ተቋርጦ የነበረው #የቅርንጫፎች_አገልግሎት መጀመሩን አሳውቋል። የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም አሳውቋል። በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ፦ - ኢንተርኔት ባንኪንግ፥ - ሞባይል ባንኪንግ፥ - ሲቢኢ ብር ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን ገልጾ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ ጠይቋል።…
#Update

" የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አልደረሰብኝም " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኤቲኤም (ATM) አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ፤ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን  ገልጾ በቀጣም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ እናስጀምራለን ብሏል።

በሌላ በኩል ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት በጊዜያዊነት የተከሰተውን የአገልግሎት መስተጓጎልን ምክንያት በማድረግ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ትስሥር ገፆች በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

" የተከሰተው የአገልግሎት መቋረጥ በባንኩ የውስጥ የሲስተም ችግር ነው " ያለው ባንኩ   ፤ ከባንኩ ውጭ በደረሰ የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት የለም የሚሰራጨው መረጃም ሀሰት ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ እንዳለው ገልጾ ከዚህ ጋር በተያያዘ ደንበኞቹ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው አሳስቧል።

ሌሎች ያልተጀመሩ አገልግሎቶች በሰዓታት ልዩነት ሙሉ በሙሉ በማስተካከል እንዲጀምሩ እየተሰራ መሆን አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከባንኩ ደንበኞች ባገኘው መረጃ ከባንኩ አገልግሎት መስተጓጎል ጋር በተያያዘ የኤቲኤም ማሽን የታዘዘውን ገንዘብ ሲሰጥ እንደነበር (በአካውንታቸው ገንዘብ ለሌላቸው) ፣ በሞባይል ባንኪግም ገንዘብ በአካውንታቸው የሌላቸው ሰዎችም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተረድቷል።

በተለይ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገንዘብ ሲያወጡ ነው።

ይህ ተከትሎ ተቋማት በትላንትናው ዕለት መጋቢት 6 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ኤቲ ኤም ላይ በትርፍ የሌላቸውን ገንዘብ በማወቅም ባለማወቅም ያወጡ በፍጥነት እንዲመልሱ እያሳሳቡ ይገኛሉ።

ተማሪዎቹ ያወጡትን ገንዘብ ቅርንጫፍ ቀርበው እንዲመልሱ ነው ማሳሰቢያ የተሰጣቸው።

የማይመልስ ተማሪ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድበትና በህግ እንደሚጠየቅ ገልጸዋል። የሌላቸውን ገንዝብ ያወጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝርም እንደተላከላቸው አመላክተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አልደረሰብኝም " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲኤም (ATM) አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ። ባንኩ ፤ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን  ገልጾ በቀጣም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ እናስጀምራለን ብሏል። በሌላ በኩል ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት በጊዜያዊነት የተከሰተውን…
#Update

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው እና ሌሎችም የተቋሙ አካላት በካሽ የወሰዱትን እና ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያስተላለፉትን ገንዘብ እንዲመልሱ አስጠነቀቁ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲስተም ላይ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ በርካቶች ገንዘብ ያለገደብ ሲያወጡና ሲያስተላልፉ ነበር።

በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላት ትላንት ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወጭ ሲያደርጉና ወደ ሌላም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ ያወጡና ያስተላለፉ እንዲመልሱ ተቋሞቻቸው እያሳሰቡ ይገኛሉ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ባንኩ የተፈጠረዉን ችግር በተመለከተ ፦
* ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤
* የመረጃ እና ደህንነት እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በባንኩ የተፈጠረዉን የሲስተም መቋረጥ ምክንያት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ፦
➡️ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ #በካሽ ወጭ ያደረጉና በማንኛዉም የባንኩ የድጅታል አማራጮች የተቀበሉ
➡️ ወደ 3ኛ ወገን ያስተላለፉ ተማሪዎች እና የዩንቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የወሰዱትን እና የተላለፈላቸውም አካላት ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አስጠንቅቀዋል።

ገንዘቡ ተመላሽ የሚደረገው በአቅራቢያ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ መሆኑን አሳውቀዋል።

ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑ ጉዳዩ የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑንም እየገለጹ ናቸው። ገንዘብ ያወጡ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ስም ዝርዝር እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia