TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ ፤ መስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር እንደሚያከናወን ተገልጿል፡፡

ይህን መርሐ-ግብር ተከትሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

በዚህም ፡-

ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ እሑድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

@tikvahethiopia
“ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራሉ ” - ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኀበር

ኦቲዝምና ዳውንሲንድረም ያለባቸው ልጆች የትምህርት እና ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን የሚሰጡ አምስት ማኀበራት ፣ ማህበረሰቡ እንዲህ አይነት የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ልጆች ያለው አመለካከት በፍረጃ የተሸበበ መሆኑን ፤ መንግሥትም የሚገባውን ትኩረት እንዳልሰጠ ገልጸዋል።

ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-16

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አልደረሰብኝም " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲኤም (ATM) አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ። ባንኩ ፤ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን  ገልጾ በቀጣም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ እናስጀምራለን ብሏል። በሌላ በኩል ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት በጊዜያዊነት የተከሰተውን…
#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ገለጸ።

ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት ፦
- በቅርንጫፎች፥
- በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር አስውሷል።

በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ገልጾ አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion #Gojjam

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላና ኧሌ ዞኖች ተነስተው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እያመሩ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን አካባቢ በ " ፋኖ ታጣቂዎች " የተያዙ የቀን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምልመላና የቅጥር ሂደቱን የፈፀመው " ኒኮቲካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አሳውቋል።

የታገቱት ሰራተኞች ብዛታ 272 እንደሆነ ተነግሯል።

የድርጅቱ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ አለነ ምን አሉ ?

" በአጠቃላይ 4 ሺህ ሰራተኛ ነው ያስፈቀድነው። 272 ሰራተኛ ከጋርዱላና አሌ ዞን ወስደን መንገድ ላይ ችግር ገጥሞናል። ችግሩን በአካል እኔው እራሴ ሄጄ በሽማግሌም፣ በምንም እንዲፈታ እየሞከርን ነው " ብለዋል።

ቁጥርን በተመለከተ ፤ " ከጋርዱላ 246 እና ከአሌ 38 በድምሩ 282 ሰራተኞች ነው የሄዱት " የሚባለው እጅግ በጣም ስህተት ነው ብለዋል። " ዶክመንት አለን እያንዳንዱ ዶክመንት ስላለን በዛ ነው የምናወራው ፤ የሰው ልጅ ነው የወስድነው ማንም እየተነሳ ይሄ ነው ማለት አይችልም። ስንወስዳቸውም በህጋዊ መንገድ ተፈራርመን ነው። ቁጥራቸው 272 ነው " ብለዋል።

ይሄን ያህል ብዙ ኪ/ሜ ርቀት ሄዶ ለህዳሴ ግድብ ሰራተኛ መመልመሉን ምን አመጣው ? ለሚለው ጥያቄ ፤ " ጠንካራ ሰራተኞች ስለሆኑን ነው " ሲሉ መልሰዋል። ባለፈው ዓመት ድርጅቱ በተመሳሳይ ከየክልሉ ከአማራ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከደቡብ፣ ከሁሉም ሰራተኛ ወስዶ እንደነበር አስታውሰው በተደረገው ግምገማ በስራቸው ውጤታማ ስለሆኑ ነው ደብዳቤ ተፅፎ ሰራተኞቹ የተወሰዱት የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በአማራ ክልል ውስጥ ጦርነት እንዳለና መረጋጋት እንደሌለ እየታወቀ ለምን በዚህ መንገድ እንዲሄዱ ተደረገ ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እኛ የያዝነው የሀገር ፕሮጀክት ነው። ውል ገብተናል በውሉ መሰረት መስራት አለብን። መንገዱም ሌላ መንገድ የለውም አምናም (በ2015 ዓ/ም) ከ2 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ከኮንሶ ስንወስድ በዚሁ በራሱ መንገድ ነው። አሁንም ህዳር ላይ ነበር የምንገባው ባለው ሁኔታ ሳንገባ ቀረን ሲረጋጋ ተረጋግቷል ግቡ ተባልን ገባን " ሲሉ መልሰዋል።

' ከፋኖ ታጣቂዎች ለታጋቾች #ገንዘብ ተጠይቋል ፣ ድርጅቱ ገንዘብም ሰጥቷል '' እየተባለ ስለሚነገረው ጉዳይ በተመለከተ ፤ " እኛ ሙሉ መረጃ በሁለት ቀን እንሰጣለን ከዚህ በላይ ማለት ያለብኝ የለም " ብለዋል።

የሰራተኞቹ ደህንነትን በተመለከተ " ደህንነታቸው በጣም ሰላም ነው " ብለዋል። ይህን ያረጋገጡት እዛው ቅርብ ስለሆነ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን በአካል እዛው አካባቢ በቅርብ ሆነው እየተከታተሉ እና #በሽምግልና ልጆችን ከእገታ ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ የተመዘገበ ከመላው ሀገሪቱ ሰራተኞችን ለስራ እየመለመለ የሚቀጥር እንደሆነ አሳውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በ 'ፋኖ ታጣቂ ኃይሎች' የተያዙ ሰራተኞች ቤተሰቦች ሰራተኞቹ ፦
* አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳሉ፣
* ጫካ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ፣
* ምግብም እያገኙ እንዳለሆነ፣
* ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱና ወደ ውጊያ ውስጥ እንዲገቡ የማስገደድ ሁኔታ እንዳለ፣
* የግድያ / ርሸና ዛቻም እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ታግተው ከተወሰዱ 4ኛው ሳምንት እየጀመረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ የሰጣቸው አካል እንደሌለ ቤተሰቦች ገልጸዋል። የፌዴራልም የክልል መንግሥትም ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፤ " ... ከተቻለ በ72 ሰዓታት ውስጥ ወጣቶቹን ለቀይ መስቀል እናስረክባቸዋልን " ብለዋል።

ስለ ጉዳዩ በዝርዝር ምን አሉ ?

➢ " እኛ ያረጋገጥነው እነዚህ ልጆች አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ ነው ያገኘናቸው " ብለዋል።

➢ የታገቱ ወጣቶች ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እየተወሰዱ ስለመሆኑን ምን ማስረጃ አላችሁ ? ለሚለው ጥያቄ ፤ " ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ አለን። በወታደራዊ ቋንቋ ጠርናፊ የሚባል ቃል አለ ይህ ማለት አንድን የሚንቀሳቀስ ወታደራዊ ኃይል፣ ምልምል / የታጠቀ ኃይል የሚመራ ማለት ነው። የነዚያ ተጓዦች ተርናፊዎች የአስር አለቃ ማዕረግ ሳይቀርብያላቸው አክቲቭ ወታደሮች መሆናቸውን ከራሰቸው መታወቂያ ዕዛቸውን፣ ኮራቸው፣ ክ/ጦራቸውም ፣ ሻለቃቸውን የሚጠቅስ መታወቂያ ይዘዋል። የመከላከያ አርማ ያለው መታወቂያና አክቲቭ መሆናቸውን አረጋግጠናል " ብለዋል።

➢ "ከያዝናቸው ውስጥ ያነጋገርናቸው ወደ መሰረታዊ ውትድርና እንደሚገቡ እንደሚያውቁ ፣ በዛ ያሉት ግን ግንዛቤው እንደሌላቸው ግን ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፈላቸው ነው ያረጋገጥነው" ሲሉ አክለዋል።

➢ ሌላው ከተለያየ ኢትዮጵያ ክፍል ወደህዳሴ ግድብ የሚሄዱ ሰራተኞችም ሆነ ጎብኝዎች አዲስ አበባን ረግጠው ፣ በአምቦ አድርገው በነቀምት ፣ አሶሳ ነው ወደ ጉባ የሚገቡት በአማራ ክልል አቋርጠው የሚሄዱበት ታሪክ አልነበረም ሲሉ ተደምጠዋል። " አሁን ላይ በአማራ ክልል ውጊያ እንዳለ እየታወቀ በአ/አ አማራ ክልል አድርገው ወደ ጉባ የሚሄዱበት ምክንያት የለም " ሲሉ አክለዋል።

➢ የወጣቶቹን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ በተመለከተ እኚሁ ቃል አቀባይ ፤ " ስለ ፋኖ ዓላማ ፣ ስለ አማራ ትግል አስፈላጊውን ትምህርት ሰጥተናቸው ለቀይ መስቀል ልናስረክባቸው በዝግጅት ላይ ነን " ብለዋል። " ቀይ መስቀል ወደኛ እየመጣ ስለሆነ ከተቻለ በ72 ሰዓት ካልሆነም በ100 ሰዓት ውስጥ ለማስረከብ ዝግጁ ነን። ሁኔታውን አጥንተው ስለሚገቡ በደረሱበት ሰዓት እናስረክባለን። " ብለዋል።

➢ በታጋቾች ላይ እየተፈፀመነው ስለሚባለው የግድያ ዛቻ፣ በግዳጅ ወደ ውጊያ እንዲገቡ የማድረግ ጉዳይ ተጠይቀው ፤ " ከያዝናቸው 240 ሰዎች ፦
• አንድም ሰው የአካል ድብደባ ደርሶበት ከሆነ፣
• በግድ ፋኖ እንዲሆን ጠብመንጃ እንዲሸከም ተገዶ ከሆነ ፣
• አንድም ሰው ያለ ፍላጎቱ እኛ የፈለግነውን ፕሮፖጋንዳ እንዲናገር ተገዶ ከሆነ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፣ ሂውማን ራይትስዎች አስፈላጊው አጣሪ ኮሚቴ ልከው ማጣራት ይችላሉ " ብለዋል።

የጋርዱላ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ኩናሎ ምን አሉ ?

° የፌዴራል መንግሥት ፤ የአማራ ክልልም መንግሥት ከዞኑ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ነገር ግን እስካሁን ውጤት እንዳልመጣ ተናግረዋል።

° ታጋቾች #በነፍስ_ወከፍ_300_ሺ_ብር እንዲከፍሉ መጠየቁን ነገር ግን ለማስቀለቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ያገኘው ከቪኦኤ ሬድዮ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት " ቲክቶክ " የተሰኘውን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ። አዋጁ የቻይናው #ባይትዳንስ_ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " በስድስት (6) ወራት ውስጥ አክሲዮኖችን #ለአሜሪካውያን ካልሸጠ በመላው አሜሪካ ይታገዳል ብሏል። ይህ አዋጅ በሴኔቱ ጸድቆ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ካልተፈረመበት ህግ ሆኖ ተፈጻሚ አይሆንም ተብሏል። ፕሬዝዳንት…
#ቲክቶክ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ትልቅ ተፅእኖ የፈጠረው በቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ የሚተዳደረው " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ በአሉታዊም ይሁን አውንታዊ መንገድ ስሙ ይነሳል።

በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ልዩነት አለው የሚሉም ብዙ ናቸው።

አንዳንድ ሀገራት ልጆች እና ወጣቶችን ከአጉል ባህል ለመጠበቅ በሚል በሙሉ ሲያግዱት ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከመንግሥት ቁሳቁሶች ፣ ከመ/ቤቶች አግደዋል።

ለመሆኑ ቲክቶክ በቻይና እና በተቀረው ዓለም ይለያያል ?

ትሪስታን ሃሪስ ፤ የቀድሞው የጉግል ሰራተኛ እና ለማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ሲሆኑ ፤ በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ይዘት ልዩነት አለው ባይ ናቸው።

ዶዪን የቻይናው ቲክቶክ ልጆችን / ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

" የመተግበሪያው ባለቤቶች ቴክኖሎጅ በልጆች እድገት ላይ ያለው ተጽዕኖ በደንብ አድርገው የተገነዘቡ ናቸው " የሚሉት እኚሁ የማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ፤ " በቲክቶክ የሀገር ውስጥ (ቻይና) ስሪታቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ፦
* በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸው የሳይንስ ሙከራዎችን፣
* የሳይንስ እና ሌሉች ሙዚየም ኤግዚቢቶችን
* የሀገር ፍቅር ቪዲዮዎችን፣
* ትምህርታዊ የሆኑ ቪዲዮዎችን ያሳያሉ " ብለዋል።

እንዲህም ሆኖ እራሱ በሀገሪቱ ያሉት ታዳጊዎች / ልጆች በቀን ውስጥ በቲክቶክ ላይ የሚያጠፉት ሰዓታቸው የተገደበ መሆኑንም አንስተዋል።

በዩኤስ እና ቻይና በታዳጊዎች ላይ አንድ የተደረገ ጥናት እንደነበር የሚያነሱት ተሟጋቹ ይኸውም " ወደፊት የምትፈልጉት የምኞት ስራ ምንድን ነው ? " የሚል እንደሆነ በዚህም ውጤቱ ፦
- በዩኤስ ውስጥ ቁጥር 1 የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ፤
- በቻይና ደግሞ ቁጥር 1 #የጠፈር_ተመራማሪ የሚል እንደነበር ገልጸዋል።

ከዚህ ወራት በፊት የቲክቶክ ዋናው ስራ አፈፃሚ በአሜሪካ ኮንግረስ ቀርበ ጠንካራ ጥያቄ በቀረበባቸው ወቅት አንዱ የተነሳው ፤ በቻይና ያለው ቲክቶክ ለልጆች የሚያስተዋውቀው ፦
° ሳይንስ
° የሒሳብ / ሌሎች የትምህርት ቪድዮዎችን ነው ፤ የሚያዩበት / የሚቆዩበት ሰዓትም ገደብ አለው ዩኤስ ውስጥ ግን የሚገፉት ቪድዮዎች ልጆች ራሳቸውን እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው ይህ ለምን ? የሚል ነበር።

ቲክቶክ ሱስ የማስያዝ አሰራር እንዳለው የሚያነሱ ሌሎች ባለሞያዎች የሰዎችን ስሜት በማንበበ ረጅም ጊዜ እዛ ላይ እንዲያሳልፉ ያደርጋል ባይ ናቸው።

ለታዳጊዎ/ልጆች ተብሎ የተለየ ስሪት ስለሌለው ይተቹታል።

በቲክቶክ ላይ የመቆያ ጊዜ እንደ #ፍላጎት እና ያልተገደበ መሆኑም በተለይ ለወላጆች ፈተና እንደሆነ ያነሳሉ።

ምንም እንኳን በተለይ #አሜሪካውያኑ እያደረሰ ነው የሚሉት የማህበራዊ ተፅዕኖው እንዳለ ሆኖ ከደህንነትና ከቻይና ጋር ባላቸው ሁኔታ እንዲታገድ ወይም ድርሻ #እንዲሸጥላቸው በይበልጥ ቢፈልጉም በርካቶች በትውልድ ላይ ቀውስ እየፈጠረ ነው ፣ ቁጥጥርም የለው በሚል እንዲታገድ / የይዘት ቁጥጥር እንዲደረግበት ይፈልጋሉ።

ከዚህ በተቃራኒው ቲክቶክ በዩኤስ ሆነ በሌላው ዓለም የበርካታ ወጣቶችን ህይወት በገንዘብ ቀይሯል።

በርካቶችን ለብዙሃን አስተዋውቋል። ብዙ ገንዘብ እንዲሰሩም አድርጓል። አልጎሪዝሙ በትንሽ ድካምና ስራ ሚሊዮኖች ጋር ማድረስ መቻሉ ሰዎች በአንድ ሌሊት ብቻ የዝና ማማ ላይ ቁጭ እንዲሉ አድርጓል።

ከደህንነት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ሰፊ ጉዳዮች አስተዳዳሪዎቹ የተጠቃሚዎችን ምንም መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፈው እንደማይሰጡ ደጋግመው ተናግረዋል። ሌሎች ወቀሳዎችንም አጥብቀው ይሞግታሉ።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

ደማቁ የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ቀጥለዋል💥

🔥 ወደ ግማሽ ፍፃሜ ሚደርሱትን ቡድኖች ይገምቱ!

🔥 የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች ይከታተሉ!

👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ደንበኝነትዎን ሲያሳድጉ... እኛም ቀጣዩን ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

ለሚሰጡን አስተያየት በቅድሚያ እያመሰገንን፣ ስለ አገልግሎታችን ጥራት የሚደርስዎትን የፅሁፍ መልዕክት ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#FACupAllOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል ” - የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ትላንት ረቡዕ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህም ላይ ከተገኙት ባለድርሻ አካላት መካከል የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር አንዱ ነው። በአማራ ክልል በ “ፋኖ”…
#Amhara

“ ' 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ' በሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል ” - ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ፤ ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ እንደነበርና ቲክቫህ ኢትዮጵያም መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

በወቅቱ የአማራ ሴቶች ማኀበርን የወከሉት ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ስለሴቶች በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ ለተሳታፊዎችና ኃላፊዎች ገለጻ ሲያደርጉ፣ “ አማራ ክልል ራሱ የበፊቱን እንኳን ትተነው አሁን በሚስተዋለው ግጭት ብቻ ከ4,000 በላይ ሴቶች #ተደፍረዋል ” ሲሉ ገልጻ አድርገው ነበር።

ይህንንም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቦት እንደነበር ይታወሳል።

ሆኖም የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ፣ ዘገባው ከተሰራ በኋላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ የወ/ሮ በላይነሽን ገለጻ መሠረት በማድረግ የተዘገበውን ዜና ጠቅሰው፣ “ የእናንተ ስህተት አይደለም በእርግጥ የልጆቷ ስህተት ነው ” ብለው ዘገባው #ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።

ወ/ሮ በላይነሽ በስብሰባው ላይ ያደረጉት ገለጻ የድምጽ ቅጅ እንደገና ሲረጋገጥ፣ “ 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ” የሚል ሆኖ እያለ፣ መረጃውን የት እንዳገኙት እንዲገልጹ የአማራ ሴቶች ማኀበር ሲጠይቃቸው፣ “ ‘4 ሺህ የተባለው እንደ ኢትዮጵያ የቀረበ እንጂ እኔ አላልኩም፣ 400 ነው ያልኩት " ሲሉ ለመካድ እንደሞከሩ ያስረዱት ም/ዳይሬክተሯ፣ “ 400 ከየት አመጣሽ ? ሲባል ‘ከሴቶች ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ሲባል ሰምቼ ነው’ የሚል ሀሳብ ነው ያመጣች ግን 400ም የእኛ መረጃ አይደለም ” ብለዋል።

አክለው “ የ6 ወራት ሪፓርታችንም ‘ፆታዊ ጥቃት ደረሰብን’ ብለው ተቋማችን ድረስ የመጡ 4 ሴቶች ናቸው። እነዚያን ሴቶችም ሁለቱን ሰጥተናል። ሁለቱን ከፓሊስ ጋ ሁነን ገና በሂደት ላይ ያለ ጉዳይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ አንድ ሰው ከአንድ ተቋም ሲላክ ታምኖበት፣ ዘርፉን ያውቀዋል ተብሎ ነውና የሚላከው ባለሙያዋ የተናገረችው ስህተት መሆኑን እንዴት ነው የምታረጋግጡልኝ ? የሚል ጥያቄ ለም/ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሁሉአየሽ አቅርቧል።

“ እውነት የምነግርህ እኔ ምክትል ዳይሬክተር ነኝ ፤ ልጅቷ ፕላንድ የሚባል ፕሮጀክት አለ የእርሱ አስተባባሪ ነች ” ያሉት ም/ ዳይሬክተሯ፣ “ ዙሮ ዙሮ ግን እርግጠኛ ሆኘ የምነግርህ ክልሉ ያለበት ሁኔታ ይታወቃል። ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊሆንም ይችላል፣ ሊያንስም ይችላል፣ ስትሰበስበው ነው የምታገኘው ” ሲሉ አስረድተዋል።

ተቋማቸው መልዕክቱን በሰነድ መልኩ እንዲልክ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጠይቀው ምክትል ዳይሬኮተሯ ፈርመው የላኩት ደብዳቤ ፦

- " ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ' በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት 4,000 ሴቶች ተደፍረዋል ' የሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል " ይላል።

- ክልሉ በዚህ ወቅት በግጭት ላይ በመሆኑ በሴቶች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ ቢገመትም ተቋሙ ግን ታች ድረስ ወርዶ መረጃ ለመሰብሰብ ባለው ግጭት ምክንያት ምቹ ሁኔታ ስለሌለና ኢንተርኔት በመዘጋቱ ምክንያት መረጃዎችን ሰብስቦ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ይገልጻል።

* የተባለው መረጃው በተቋሙ ውስጥ እንደሌለ፤ ምቹ ሁኔታን ሲገኝ ታች ወርዶ ያረጋገጥነውን መረጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደሚያሳውቅ ያመለክታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረጉት ገለጻ ስህተት እንደሆነ የተነገረላቸው ወ/ሮ በላይነሽን በድጋሚ ማብራሪያ እንዲሰጡ ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#AATikvahFamily

@tikvahethiopia
" ዳሽን ባንክ ላይ የሲስተም ችግር አጋጥሟል  " የሚለው መረጃ ሐሰተኛ ነው ሲል ባንኩ ገለጸ።

ትላንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጋጥሞኛል ባለው ሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቱ ዳግም መስተካከሉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ዳሽን ባንክም ተመሳሳይ አይነት የሲስተም ችግር ማለትም ሰዎች፦
- ያለገደብ ገንዘብ ከኤቲኤም የማውጣት
- በሞባይል ባንኪንግ ገደብ የሌለው ገንዘብ የማስተላለፍ ችግሮች ገጥሞታል በሚል እየተሳራጨ ይገኛል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም ሰዎች ወደ ዳሽን ኤቲኤሞች በመሄድ ያለ ገደብ ገንዘብ ማውጣት እንደሚችሉ የሚገልጹ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ነው።

ባንኩ ግን "  ይህ ፍፁም #ሐሰተኛ መረጃ ነው " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

የባንኩ ኤትኤሞች እና የዲጂታል አውታሮች ሁሉ ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ የተጠበቀ እንደሆነ ገልጾ ደንበኞቹ ምንም አይነት ስጋት ላይ እንዳይወድቁ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት ነገ በአዲስ አበባ ፤ መስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር እንደሚያከናወን ተገልጿል፡፡ ይህን መርሐ-ግብር ተከትሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። በዚህም ፡- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች…
#Update

ዛሬ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ ያዘጋጀው ፦
- የንስሀ ፤
- የምልጃ
- የምስጋና በዓል መርሐ-ግብር መካሄድ ጀምሯል።

ለዚሁ መንፈሳዊ መርሐ-ግብር እጅግ ከፍተኛ ምዕመን በመስቀል አደባባይ መሰባሰቡን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያሳያል።

መርሐ-ግብሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (etv)  ፣ በአዲስ ቴሌቪዥን ፣ በፋና ቴሌቪዥን ፣ በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ፣ በEvangelical Media የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

Video Credit - Generation Eng.
Photo Credit - Evangelical TV

@tikvahethiopia