TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አልነጃሺ
በጦርነቱ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጅድ ጥገና ባለመደረጉ የሶሀባዎች መቃብር በዝናብ እና በፀሀይ እየተደበደበ መሆኑ ተገለፀ።
ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አልፎም የዓለም ሙስሊሞች ታሪክ የሆነው ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጅድ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በውስጡ የነበሩ ቅርሶችም ተዘርፈው መወሰዳቸውን የአል ነጃሺ መስጅድ ኢማም እና አስጎብኚ ተናግረዋል።
በጦርነቱ ምክንያት የንጉስ አል ነጃሺን ጨምሮ የ8 ሶኻባዎች የመቃብር ስፍራ ያለበት ቦታ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ በዝናብ እና ፀሀይ እየተደበደበ ከመሆኑም ባሻገር የመፍረስ አዳጋ እንደተጋረጠበት ኢማሙ ተናግረዋል።
በተጨማሪ የአል ነጃሺ መስጂድ ሚናራ በመሳሪያ የተመታ በመሆኑ በዝናብ ፍሳሽ እንደተቸገሩ ገልጸዋል።
ከቅርብ ሳምንታት በፊት በመንግሥት በኩል " የአል ነጃሺ መስጅድ በቱርክ መንግስት እድሳት እንደሚደረግ ቢገለፅም እስካሁን የመጣ አካል የለም " ሲሉ ኢማሙ ተናግረዋል።
በሌላ ዜና ፤ ሼህ ሙሀመድ አልሀሙዲን ለታሪካዊው የአልነጃሺ መስጂድ ትራንስፎርመር በመቃጠሉ የተቋረጠውን የውሀ እና መብራት አግልግሎት ለማስቀጠል ጥገና ለማድረግ በሚድሮክ ኩባኒያ በኩል ቃል መግባታቸው በመጅሊስ ልዑካን ቡድኑ መስማታቸው እንዳስደሰታቸው የተናገሩት የነጃሺ አካባቢ ነዋሪዎች ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ቶሎ ተፈፃሚ እንዲሆን ጠይቀዋል።
መረጃው የሀሩን ሚዲያ ነው።
@tikvahethiopia

#ድርቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርቅን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ " አሁን የተከሰተው ከ77ም ያልተናነሰ ነው " በሚል ከዚህ ቀደም የተሰጡ አስተያየቶችን ኮነኑ። " የሚታረስ መሬት እያለን የሰው ጉልበት እያለን ድህነንት እና ልመናን ጌጥ አናድርገው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ተቸግረዋል ሊያልቁ ነው ሲሉን እንደ ሽልማት አንውሰደው ኮሮና መጣ ሊረግፉ ነው አሉ ረገፍን እንዴ ? አልረገፍንም ሟርት ነው።…
#OxfamInternational
ኦክስፋም ኢንተርናሽናል በትግራይ ክልል ጦርነትና የዝናብ እጥረት ያስከተለውን የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ጠቅሶ፣ " ሰው ሲራብ ቆሞ መመልከት የሞራልና የፖለቲካ ኪሳራ ነው " ሲል አስታወቀ፡፡
ኦክስፋም ፤ በረሃብ የተጠቁ ቤተሰቦች ችግሩን ለማምለጥና በሕይወት ለመትረፍ ሲሉ የመጨረሻ ተስፋ አስቆራጭ ዕርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
ኦክስፋን አነጋገርኳቸው ያላቸው በአንድ ትምህርት ቤት ከተጠለሉ ቤተሰቦች መካከል ፦
- እናቶች፣ ልጆቻቸው ተርበው ቀኑን በሙሉ የሚያበሏቸው ነገር ማጣታቸውን፣
- እናቶች ልጆቻቸው ረሃቡን ሊቋቋሙ ባለመቻላቸው የረሃብ ሕመምን ለማስታገስ ለረጅም ሰዓታት እንዲተኙ እንደሚያስገድዷቸው
- ሰዎች ለእንስሳት የሚሆኑ ሥራ ሥሮችን ለመመገብ መገደዳቸውን መናገራቸውን ገልጿል፡፡
ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች በረሃብ እየተሰቃዩ መሆናቸውንም አክሏል፡፡
የኦክስፋም የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ፤ " አሁን የሚታየው የችግሩ ጫፍ ነው " ብለዋል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች አስከፊ የሆነ ረሃብ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉና ዜጎች ቀጣዩን ምግባቸውን ማግኘት ከባድ የሆኑ መንገዶችን እያለፉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ አስከፊ ከሆኑ የሰብዓዊ ቀውስ ክስተቶች አንዱ ለሆነው የሰሜን ኢትዮጵያ የዕርዳታ አቅርቦት፣ ይጠበቅ ከነበረው 4 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት የተቻለው 34 በመቶ ብቻ መሆኑን ኦክስፋም ጠቁሟል፡፡
አፋጣኝ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ካልተደረገ የበርካታ ዜጎች ሕይወት አደጋ ውስጥ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ኮንሰርን ወርልድ ዋይድ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ ተከስቷል ያለው ረሃብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡
በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የተከሰተው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ከተሰጣቸው መሰል ክስተቶች እጅግ የላቀ መሆኑን ድርጅቱ በሪፖርቱ አመላክቷል።
የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት በትግራይ እና በአማራ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ምክንያት 372 ሰዎች መሞታቸውን ፤ 23 ህፃናት በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት ተገቢዉን ዕድገት ባለማግኘታቸዉ ሞተው መወለዳቸውን ማረጋገጡ ማሳወቁ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ " ድርቅ ለኢትዮጵያውያን ልክ እንደ ባህላችንና እንደ ዓድዋ ድል ለ100 ዓመታት ሲጎበኘን የቆየ ጉዳይ በመሆኑ፣ እንደ አዲስ ሊወራ የሚችል ነገር አይደለም " ብለው ነበር።
" ድርቁን መንግሥት አላመጣውም " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ " ድርቅን እንደ ፖለቲካ ማየት የለብንም፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ችግር አለ፣ ችግኝ እንትከል ሲባል ችግኝ ምን ያደርጋል ? ድርቅና ረሃብ አለ ስንዴ እናምርት ሲባል ስንዴ ምን ያደርጋል? ካልን በኋላ ድርቅ መጣ ብለን ብንጮኸ ትርጉም የለውም " ሲሉ አስረድተዋል፡፡
" ድርቁን ለፖለቲካ መጠቀም ጥፋት ነው " ብለው፤ ባለፉት 4 ወራት 500 ሺሕ ኩንታል እህል በመንግሥትና በተራድኦ ድርጅቶች ትብብር ለተረጂዎች መላኩን ተናግረዋል፡፡
" ይህ ሀብት በቂ ካልሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አቅም እያለው በረሃብ የሚሞት ሰው ዓይተን ዝም አንልም " ብለዋል፡፡
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " መንግሥት ትናንት እንዳደረገው ዛሬም የሚራብ ሰው ካለ ፕሮጀክት ሁሉ አጥፎ በረሃብ እንዳይሞት ከሕዝቡ፣ ከባለሀብቶችና ከክልል መንግሥት ጋር በመሆን የሚችለውን ሁሉ ይሰራል " ብለዋል።
#ሪፖርተር

" ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው " - የደቡብ ወሎ ዞን
በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "018 አለኋት" ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30/2016 ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከ20 በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
" በአለቱ የተዳፈኑትን ወጣቶች ለማውጣት የቦታው አቀማመጥ ለማሽን የተመቸ ባለመሆኑ በሰው ኃይል በቁፋሮ ህይወታቸውን ለማትረፍ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል " ብሏል።
ዋሻው ከ750 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ሲሆን ለዋሻው መግቢያ ቅርበት ባለው የውስጠኛው ክፍል ላይ ነው የወጣቶቹን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ እየተደረገ የሚገኘው።
መረጃው የደቡብ ወሎ ኮሚኒኬሽን ነው።

ፎቶ፦ 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ነው የሚገኘው የተባለው የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት #ወደመጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል። ፕሮጀክቱ በውስጡ ፦ - በዓድዋ ጦርነት የተሰዉ ጀግኖችን የሚዘክር ሙዚየም፣ - የመዝናኛ ሥራዎች፣ - ካፍቴሪያዎች፣ - ሲኒማ ቤቶችና ሁለገብ አዳራሾችን - የህፃናት መጫወቻ - አንድ ሺህ (1000) መኪና ማቆም የሚያስችል ፖርኪንግ - የንግድ ቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።…
#Update
የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " ዛሬ ይመረቃል።
አጫጭር መረጃዎች ስለ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " ፦
- በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለል እና 8 በሮች አሉት።
- 8ቱ በሮች ፦
* የምሥራቅ ጀግኖች በር፣
* የምዕራብ ጀግኖች በር፣
* የሰሜን ጀግኖች በር፣
* የደቡብ ጀግኖች በር፣
* የፈረሰኞች በር፣
* የአርበኞች በር፣
* የፓንአፍሪካኒዝም በር ተብለው ተሰይመዋል።
- በመታሰቢያው ነጋሪትን ጨምሮ የኢትዮጵያውያን የተለያዩ (ባህላዊዎችን ጨምሮ) የጦር መሳሪያዎች ተቀምጠዋል።
- በዓድዋ ድል መታሰቢያው የአፄ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ፣ የ12ቱን የጦር መሪዎች ሀውልት፤ በጦርነቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ፈረሶች መታሰቢያ የአርት ሥራዎችም ሰፍረዋል።
- አንድ መቶ ሃያ ሺህ ጀግኖችን የሚዘክር ማስታወሻ፣ የዓድዋ ድል ለፓንአፍሪካኒዝም ንቅናቄ ማሳያነቱንም ይዟል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፋውንቴንም ተሰርቶለታል።
- በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 500 ሰዎችን መያዝ የሚችል የፓንአፍሪካኒዝም አዳራሽ አለው።
- በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 300 ሰዎችን መያዝ የሚችል ዘመናዊ ሁለገብ አዳራሽ አለው።
- አራት ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል የቤት ውስጥ የስፖርት ሜዳ እና አዳራሽ አለው።
- የህፃናት መጫወቻ፣ የንግድ ሱቆች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቢሮዎችና የአርት ጋላሪ አለው።
- ከአንድ ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ አለው።
- እያንዳንዳቸው 280 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ 2 ሲኒማ ቤቶች አሉት።
- በቅርቡ ወደ ሀገር የገባችው " ፀሀይ አውሮፕላን " በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንድትቀመጥ ተደርጓል።
- አጠቃላይ ስራው 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
ℹ️ 00 ኪ.ሜ መነሻ ቦታ ፦ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መሐከል ላይ የሚገኘው የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው።
Info ፦ EPA
Photo Credit ፦ Addis Ababa City Communication & Abel Gashaw /

#CBE
እጥፍ ወለድ....
********
ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ፤
አዲሱን የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ!
• ከመደበኛው ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል ፣
• ለውጭ ሀገር ጉዞዎ ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬ አገልግሎት እና
• የሞባይል ካርድ ስጦታም ያገኛሉ ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***********
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial

በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም አሪቦና ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ።
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ " ሳዉዝ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የተሽከርካሪዎች ግጭት በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
የሳይክል ፣ የሞተርና መኪና ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ ሳይክል ሲያሽከረክር የነበረ የ17 አመት እድሜ ያለዉ ታዳጊ ህይወቱ ሲያልፍ ፤ ሞተር ያሽከረክር የነበረዉ ወጣት ላይ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያዊ የሰጡት የአካባቢው የትራፊክ አባል ሳጅን አገኘሁ አቡ ፤ ጉዳቱ በፍጥነት ችግር የተከሰተ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ በህይወት ቢተርፍም ጉዳት ያስተናገደዉን ሞተረኛ ለህክምና ወደ ሪፈራል ሆስፒታል መላኩን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፥ ከአዲስ አበባ ወደ መተሀራ በሚወስደው ዋና መንገድ በምስራቅ ሸዋ ቦሰት ወረዳ ልዩ ስሙ " አሪቦና "በተባለ ሥፍራ በደረሰ የመኪና አደጋ አንድ ሰው ሞቷል።
አደጋው የደረሰው " ኒሳን ፖትሮል " መኪና ከአይሱዚ መኪና ጋር ተጋጭተው ሲሆን አንድ ሰው ሲሞት ሌሎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢፕድ ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ኢፕድ (አሪቦና)

" በወንድሜ አንተነህ ጌታሁን ጉዳይ ፍርድቤት ለሁለተኛ ጊዜ የዋስ መብት ቢፈቅድም ፖሊስ ሊፈታልን አልቻለም " - ዳግም ጌታሁን
" ተጨማሪ ምርመራ በማስፈለጉ ፖሊስ ህጋዊ መንገድ ተጠቅሞ ተጠርጣሪዉን ሊያቆየዉ ችሏል " - ፖሊስ
አንተነህ ጌታሁን የተባለ ወጣት በሀዋሳ ከተማ " በሶሻል ሚዲያ የምትጽፈዉ ጽሁፍ ወጣቱን ለሽብር ያነሳሳል !! " በሚል በቀን 26/05/2016 ከጓደኞቹ ጋር በሚዝናናበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ታስሯል።
ይህ ወጣት አንተነህ ጌታሁን ሁለተኛ ጊዜ ፍ/ቤት ቀርቦ የዋስ መብቱ ቢከበርም ፖሊስ ሊፈታዉ ፈቃደኛ አልሆነም ሲል ወንድሙ ዳግም ጌታሁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
" እሁድ ምሽት ከጓደኞቹ ጋር በመዝናናት ላይ እንዳለ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ለጥያቄ ትፈለጋለህ " በሚል ወሰዱት የሚለዉ ዳግም " የቀረበበት ክስ ተጨባጭ መረጃ የለዉም በሚል ፍ/ቤቱ የዋስ መብቱን ለ2ኛ ጊዜ መፍቀዱን ተከትሎ የታዘዘዉን 50 ሺህ ብር ብናስይዝም ወንድሜ ሊፈታ አልቻለም " ብሏል።
ወንድሙ የታሰረበት ዳግም ጌታሁን ፤ " እየመጡ ነው !! " በሚል የፋኖ ኃይሎችን የሚደግፍ ፅሁፍ በፌስቡክ ፅፈሃል በሚል እንደሆነ ተናግሯል።
በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የመምሪያዉ ፖሊስ አዛዣ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ እንደገለጹት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ በህጋዊ መንገድ ተጨማሪ ጊዜ ተጠይቆበት ተጠርጣሪዉ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዉ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
አቶ አንተነህ ለሶስተኛ ጊዜ ነገ ሰኞ ፍርድቤት ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉዳዩን ተከታትለን የምንዘግብ ይሆናል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።