TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት መካከል ፦ " ... ዋናው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሥራ አጥነት ነው። አብዛኛው ሰው cause ኖሮት አይደለም። ሥራ ፍለጋ ይሄዳል ያግታል ብር ይጠይቃል። ዓላማ መር ትግል ሳይሆን እገታ መር ትግል ነው ያለው። ይሄን ደግሞ በርከት አድርጎ ሥራ በመፍጠር ወጣቱ ወደ ሥራ እንዲሄድ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ተግባሩ…
#Update

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሀገራዊ ሰላምና ፀጥታ ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ " መንግሥት በቀጣይነት ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል " ብለዋል።

" ሕግ ማስከበር አጠናክረን እንቀጥላለን " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጡ የሚለውን ጉዳይ አንስማማም አንቀበልም አናደርግም። መንግሥት ነን አቅም በፈቀደ መጠን ሕግ ለማስከበር እንሰራለን " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ሕግ ለማስከበር ስንሰራ በየአንዳንዷ ሰከንድ ለሠላም ዝግጁ የሆነ ኃይል ካለ በራችን ክፍት ነው " ያሉ ሲሆን " ለውይይት ለሠላም፣ ለንግግር ክፍት ነን። ሕግ የማስከበሩን ሥራ ከንግግር እና ከውይይት ውጭ እንዲሆን አንፈልግም " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ እና ትግራይ ድርቅ ባስከተለው #ረሃብ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ምን ያህል ሰዎች ድርቅ ባስተከተለው ረሃብ ሞቱ ? በትግራይ ክልል ፤ በማዕከላዊ ዞን 334 ሰው ከድርቁ ጋር በተያያዘ የሞተ ሲሆን ከዚህ ዞን ውስጥ የተቋሙ ቁጥጥር ቡድን ካየው የአበርገሌ ወረዳ 91 ሰው መሞቱን እና ከደቡብ ምስራቅ…
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህ/ተ/ም/ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ፤ " እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

" በትግራይ የተወሰነ አካባቢ ፣ በአማራ የተወሰነ አካባቢ ፣ በኦሮሚያ ፣ ምስራቁ ክፍልም እንዲሁ ድርቅ አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህ ምንም ጥያቄ የለውም ፤ ይህን ግን ማየት ያለብን እንደ ፖለቲካ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ድርቅን መንግሥት አላመጣውም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " environmental crisis አለ ችግኝ እንትከል ሲባል ችግኝ ምን ያደርጋል ብለን ፤ ድርቅ እና ረሃብ አለ ስንዴ እናምርት ስንል ስንዴ ምን ያደርጋል ብለን ድርቅ መጣ ብለን ብንጮህ ትርጉም የለውም ትርጉሙ ተባብሮ ሰው እንዳይሞትብን ማድረግ ነው " ብለዋል።

በቦረና በተደረገ ርብርብ ምንም እንኳን ከብቶች ቢሞቱም ሰው አልሞተም ፤ በሶማሌ ክልልም እንዲሁ በርብርብ ሰው እንዳይሞት ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁንም ትግራይ ፣ አማራ ፣ ኦሮሚያ ተርቦ እዚህ በልተን ማደር አንችልም ተባብረን ሰው እንዳይሞትብን ማድረግ አለብን ፤ ግን ድርቅን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ የምንጠቀም ከሆነ ጥፋት ነው " ብለዋል።

" ባለፉት 4 ወራት ወደ ትግራይ 500 ሺህ ኩንታል እህል በዋነኝነት በመንግሥት እና በተወሰኑ ደጋፊዎች ተልኳል ይህ ሶስት አራት ወር ሰው በምግብ እጥረት እንዳይሞት ያደርጋል። የትግራይ መንግስትም ያለውን resource / እህል ውስንም ቢሆን የከፋ ችግር ያለበት ቦታ ማድረስ አለበት፤ ያለው እህል በትክክል ካልተሰራጨ ችግር ሊያመጣ ይችላል " ብለዋል።

" ያለው resource በቂ ካልሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አቅም እያለውና የኢትዮጵያ ህዝብ በልቶ እያደረ አንድም ቦታ በረሃብ የሚሞት ሰው አይተን ዝም አንልም፤ ባለን አቅም ህዝባችንን አግዘን ይህችን ጊዜ እንዲሻገር እናደርጋለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

" መንግሥት ለድርቅ ትኩረት አልሰጣም " የሚባለውን አስተያየትም አጣጥለውታል ሰው እንዳይሞት በዋነኝነት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያወጣ ነው ብለዋል።

" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት ሚሞት ሰው የለም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ያለው ችግር ረሃብ እና አብሮ የሚመጣ በሽታ አለ በትግራይ ብቻ ሳይሆን ደቡብ ምዕራብ አካባቢ ብትወስዱ አዲስ የወባ ባህሪ አለ ያ የወባ ባህሪ በጥቂት ቀናት ሰው ይገድላል ከዚህ ቀደም የሚሰጡ መድሃኒቶችም ፈውስ አላመጡለትም ወባ ሲጨመር ፣ ተቅማጥ ሲጨመር በምግብ እጥረት እላዩ ላይ በሽታ ሲጨመር ሰው መቋቋም አቅቶት ሊሞት ይችላል " ብለዋል።

" ይሄ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ የሚሆን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምንም ጊዜ በላይ በታሪክ ተምርቶ የማያውቅ ምርት አለ " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ይህ ሁሉ እያለ ምርት አምራች አርሶ አደሮች " ወንድምህ ተርቦ እየሞተ ነው " ሲባሉ ዝም ይላሉ ብላችሁ አትጠብቁ ፤ መንግሥት እንኳን ባያደርግ ህዝቡ ተረባርቦ ሰው እንዳይሞት ጥረት ያደርጋል ብለዋል።

፣ መንግስት የሚራብበት ዜጋ ካለ ፕሮጀክት አጥፎ ህዝቡ በረሃብ እንዳይሞት ከህዝቡ ጋር የሚችለውን ሁሉ ይሰራል " ሲሉ ተናግረዋል።

በቅርቡ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ይፋ ባደረገው ሪፖርት በትግራይ እና በአማራ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ምክንያት 372 ሰዎች መሞታቸውን ፤
23 ህፃናት በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት ተገቢዉን ዕድገት ባለማግኘታቸዉ ሞተው መወለዳቸውን ማረጋገጡ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህ/ተ/ም/ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ፤ " እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ሲሉ ተናግረዋል። " በትግራይ የተወሰነ አካባቢ ፣ በአማራ የተወሰነ አካባቢ ፣ በኦሮሚያ ፣ ምስራቁ ክፍልም እንዲሁ ድርቅ አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህ ምንም ጥያቄ…
#ድርቅ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርቅን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ " አሁን የተከሰተው ከ77ም ያልተናነሰ ነው " በሚል ከዚህ ቀደም የተሰጡ አስተያየቶችን ኮነኑ።

" የሚታረስ መሬት እያለን የሰው ጉልበት እያለን ድህነንት እና ልመናን ጌጥ አናድርገው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ተቸግረዋል ሊያልቁ ነው ሲሉን እንደ ሽልማት አንውሰደው ኮሮና መጣ ሊረግፉ ነው አሉ ረገፍን እንዴ ? አልረገፍንም ሟርት ነው። ጦርነት ስንጀምር ታስታውሳላችሁ ረሃብ ረሃብ ረሃብ አሉ እውነት ነው እንዴ ? " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአንድ በኩል መዘናጋት የለብንም ችግር ሲመጣ ተረባርባን እንፍታው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " 6 ወር ያልፍና የታለ የሞተ ሰው ፣ የተባለው የታለ ሲባል ማፍር ያመጣል " ብለዋል።

" አንዳንዱ ከ77 ያልተናነሰ ድርቅ አለ ይላል ማለትም 1 ሚሊዮን ገደማ ሰው ይሞታል ማለት ነው ፤ አንድ ሚሊዮን ካልሞተ እየዋሸ ነው ሰውየው እኛ ደግሞ 1 ሚሊዮን ሳይሆን አንድም እንዳይሞት አቅማችን በፈቀደ እንፍጨረጨራለን ከአቅም በላይ ከሆነስ ? እሱ ምን ይደረጋል " ብለዋል

አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ከተረባረበች ቢያንስ ሰው እንዳይሞት የማድረግ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።

ከወራት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) ፤ በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 እንደነበርና አሁን ያጋጠመው ከዚህም በላይ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ፤ " በትግራይ ረሃብ እና ሞት እያንዣበበ ነው "  ያሉ ሲሆን ከ1977 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ ድርቅ ነው የተከሰተው ሲሉ ተናግረው ነበር።

በእድሜ የገፉ አዛውንቶችም በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው መሬት እህል አላበቅል እንዳላቸውና ሁኔታው ከ1977 የከፋ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት መካከል ፦ " ... ዋናው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሥራ አጥነት ነው። አብዛኛው ሰው cause ኖሮት አይደለም። ሥራ ፍለጋ ይሄዳል ያግታል ብር ይጠይቃል። ዓላማ መር ትግል ሳይሆን እገታ መር ትግል ነው ያለው። ይሄን ደግሞ በርከት አድርጎ ሥራ በመፍጠር ወጣቱ ወደ ሥራ እንዲሄድ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ተግባሩ…
" በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ የዜጎች #እስር ጉዳይ ነው።

" እስር በዝቷል " በሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው መልስ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እውነቱን ለመናገር አሁን እንዳለው anarchy ፣ ስድብ ፣ጥፋት እስር ቢበዛ ኖሮ ፓርክ ሳይሆን እስር ቤት ነበር የምንገነባው " ያሉ ሲሆን " በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ " ብለዋል።

ምሳሌ ብለውም ፤ ሸራተን ጀርባ ብዙ ተለፍቶበት ተሰርቷል ያሉትና ስራ ከጀመረ 15 ቀን ገደማ በሆነው መንገድ ላይ ቆመው ሽንት የሚሸኑ ሰዎች ጠቅሰዋል።

" እነዚህ ሰዎች ቢታሰሩ አገባብ አይደለም ወይ ? " ሲሉ ጠይቀው " ለማጥፋት ነው የሚመስለው እንጂ ካልጠፋ ቦታ እንደዛ አይነት ቦታ ላይ ሄዶ እንደዛ አይደረግም " ብለዋል።

" እኛ እስር ቤት ሳይሆን ፓርክ ነው እየገነባን ያለነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ከሆነ የእስር ጉዳይ የተነሳው ... ከተያዘው አብዛኛው ሰው ተምሮ ወጥቷል። " ብለዋል።

በሺህ የሚቆጠር ሰው ከእስር እንደወጣ የገለፁት ዶ/ር ዐቢይ " አሁን በጣም በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው እስር ቤት ያሉት። እነሱም እየተጣሩ፣ እየተማሩ ሊፈቱ ይገባል ፤ ሰው እስር ቤት አቆይቶ መቀለብ ለድሃ መንግሥት አያዋጣም። አስተምሮ መመለስ ያስፈልጋል " ብለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " የታሰሩ ሰዎች እዚህም እዚያም አሉ " ያሉ ሲሆን " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚመራው ኃይል እየመረመረ እያወያየ እያሰለጠነ አብዛኛዎችን ይፈታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ መሆንም ያለበት እንደዛ ነው። " ብለዋል።

" ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ከዚያ ጋር አብሮ የሚጨፈለቅ ፣አብሮ የሚታይ ነገር ካለ መፈተሽ ጥሩ ነው " ብለዋል።

" እንደው እንከን የለውም የመንግስት አሰራር ብሎ መሄድ ጥሩ አይደለም። የምንፈጥረው ስህተት ካለ እየመረመርን ማስተካከል አለብን። ካጠፋን ይቅርታ መጠየቅ አለብን። " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ሀገር ሲፈርስ ዝም ብለን አናይም፤ ስራችን መጠበቅ ስለሆነ ሀገር ጠባቂ ነን ብለን ደግሞ ጥፋት የምናመጣ ከሆነ መጠየቅ አለብን። በጣም በርካታ ሰዎች እኛ ውስጥ ሆነው የሚሰርቁ የሚያጠፉ አሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" #መለዮ ለብሰው ሰላም ማስከበር ሲገባቸው ጥፋት ላይ የሚሳተፉ ሰዎች አሉ " በማለት የተናገሩት ጠ/ሚኒስትሩ " ብዙዎቹ ይያዛሉ እነሱም ይጠየቃሉ። 100% የተሟላ ባይሆንም በውስጥ የእርማት ስራዎች በስፋት ይሰራሉ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ የዜጎች #እስር ጉዳይ ነው። " እስር በዝቷል " በሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው መልስ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እውነቱን ለመናገር አሁን እንዳለው anarchy ፣ ስድብ ፣ጥፋት እስር ቢበዛ ኖሮ ፓርክ ሳይሆን እስር ቤት ነበር የምንገነባው…
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ላይ የሚመጣ ማንኛውም የውጭ ስጋት ካለ በአግባቡ ለከላከል ዝግጁነት እንዳለ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።

ይህን ጉዳይ ያነሱት ስለ ባህር በር እና ስለ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ባነሱበት አውድ ነው። 

" ሶማሊያ ውስጥ የምንሞተው የእነሱ ሰላም የእኛ ሰላም ስለሆነ ነው " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ለሶማሊያ ሰላም ሶማሊያ ውስጥ እንደ እኛ የሞተ የለም፤ መግለጫ ያወጣ ግን አለ " ብለዋል።

የሶማሊያ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር መጣላት ፍላጎት እንደሌለው የተናገሩት ዶ/ር ዐቢይ ፤ ነገር ግን አንዳንድ አካላት ሁለቱን ሀገራት ለማጋጨት ፍላጎት አላቸው ብለዋል።

እነዚህ ፍላጎት አላቸው ያሏቸውን አካላት በስም ከመጥራት ተቆጥበዋል።

" እኛ የማንንም ሉዐላዊነት መንካት አንፈልግም " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ወደማንም አንሄድም ወደ እኛ የሚመጣ ካለ ግን ስጋት አይግባችሁ በአግባቡ እንከላከላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ባነሱት ሀሳብ " #የግብጾች ስጋት ውሃ ከያዛችሁ አስዋን ግድብ ይቀንሳል " የሚል እንደነበር ገልጸው " ውሃ ይዘን ጨርሰናል፤ የአስዋን ግድብ ውሃ ግን አልቀነሰም " ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ አሁንም ከግብጽ ጋር ለመደራደር ፣ ጥያቄያቸውን ለመስማት ዝግጁ መሆኗን አሳውቀዋል። እነሱም የኢትዮጵያ ጥያቄ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆን አለባቸው ብለዋል።

ተጨማሪ ፦
* የብድር አቅርቦት
* የአገር ውስጥ ገቢ
* የእዳ ጫና
* የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም
* የፕሪቶሪያ ስምምነት ጉዳይ
* የአማራ ክልል ሁኔታ
* የሸኔ ድርድር ... ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ የሰጧቸው ምላሾች በዚህ ይገኛሉ ፦ https://telegra.ph/PMOffice-02-06

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች።

ቤተክርስቲያን ፤ ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና ሰጥተው እንደነበር አስታውሳለች።

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው የሚገኙ መሆኑን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በአየር መንገድ አቀባበል ለማድረግ በተገኘበት ወቅት ማረጋገጡን ቤተክርስቲያን ገልጻለች።

" ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለከተው የመንግስት አካል የቤተክርስቲያናችን ከፍተኛ  የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ  መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ  እንዲፈቀድላቸው እንዲደርግ " ስትል ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አስተላልፋለች።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ስለ አዲሱ የአቢሲንያ የሞባይል ባንኪንግ አፕ ብዙዎች መነጋገር ጀምረዋል።
ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
ይክፈሉ ያሸንፉ!

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሂሳብዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m  በመክፈል ታብሌት፣ የሞባይል ቀፎ እንዲሁም የኢንተርኔት ፓኬጅን ጨምሮ ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ለማሸነፍ የዕጣ ውድድር (Scratch & Win) ይሳተፉ፤

በተጨማሪም የክፍያ ጊዜዎን በየወሩ ማስታወስ ሳይጠበቅብዎ አስቀድመው በማስተካከል (Schedule Payment) ክፍያዎን ይፈጽሙ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በኑሮ መማረራቸውን ተከትሎ “ ራሳቸውን ለማጥፋት ” ከትልቁ የኤሌክትሪክ ታወር ጫፍ ወጥተው በፓሊስና በአባታቸው ልመና ወርደው በሕይወት የተረፉት የሁለት ልጆች እናት ወ/ሮ ሂሩት በቀለ በወላይታ ሶዶ ኦተና ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምናቸው ላይ መሆናቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በሆስፒታሉ ተገኝቶ አረጋግጧል።

በሆስፒታሉ የሚገኙት የወ/ሮ ሂሩት አባት አቶ በቀለ ደኣ ፣ ባለቤታቸው  አቶ ማርቆስ አሳላ ፣ የቅርብ ቤተሰብ አቶ ኢሳያስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

አባት ፦

- ልጄ ትተርፋለች የሚል ተስፋ አልነበረኝም።

- አሁንም ቢሆን በጭንቀት ሳቢያ ያገረሸውን የልጄ የአዕምሮ ህመም የሕክምና ወጪ ለመሸፈን ተቸግርያለሁ።

ባለቤት ፦

* ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት የቀን ሥራ እየሰሩ እንደሆነና ለዚህም ወደ አዲስ አበባ ለሥራ ሂደው እንደነበር ገልጸዋል።

* " እኔ ሰርቼ እስክመጣ ተረጋጊና ጠብቂኝ ብዬ ነግሪያት ሄድኩ። ከዛ ከቤት ወጥታ ቤተሰብ ጋ ነበረች።

* የኑሮ ችግር ነው አዲስ አበባ የወሰደኝ። ሰርቼ ማኖር ብችል ባለቤቴ አትታመምም ነበር።

* እኔ በነበርኩበት ሰዓት ጤንነቷ ደኀና ነበር። እኔ በወጣሁበት ወቅት ነው ሕመሟ የተነሳባት። የምትበላውም፣ የምትጠጣውም ያሳስባታል። በዚያ ምክንያት ነው በሽታው የተነሳባት በጭንቀት። እኔ አቅም የለኝም ለማሳከም። 10,000 ብር ከሰው ተበድሬ ነው የመጣሁት። ሊበቃም ላይበቃም ይችላል። ተሽሏት ከወጣች ከእርሷ ጋር እኖራለሁ።

የቅርብ ቤተሰብ (አቶ ኢሳያስ) ፦

° ቀድሞውንም በኑሮ ውድነቱ ጭምር በባልና ሚስቱ በኩል ጭቅጭቅ ነበር ፤ አቶ ማርቆስ የጫንጮ እንጨት እየቆረጡ ቤተሰብ ያስተዳድሩ ነበር።

° በአሁኑ ደግሞ ለልጆች ምግብ ለማሟላት ወደ አዲስ አበባ ሂደው ለገና በዓል መመለስ የነበረባቸው ቢሆንም የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው አልተመለሱም ፤ ለበዓል ሲቀሩም የልጆችን ጨምሮ ለበዓል መሰናዶ አለመኖር ወ/ሮ ሂሩትን በይበልጥ አማሯቸው ነበር።

° የ6 ወር ህፃን አለች ፤ ባልና ሚስቱ በአጠቃላይ የ6 ወርና የ4 ልጆች አላቸው፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት ከቤተሰብ ጋር ቢሆኑም ችግር ውስጥ ናቸው።

° ለወ/ሮ ሂሩት መድኃኒት ከሆስፒታል ውጪ ስለሚገዛ የገንዘብ እጥረት ፈተና ሆኗል።

3ቱም ቤተሰቦቿ ወ/ሮ ሂሩትን ለማሳከም ፍላጎት ያለው ሁሉ የበኩሉን እንዲወጣ ተማጽነዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba #Update

በማህበር የተደራጁ የጋራ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች  በወሰን ማስከበር  ምክንያት እንቅፋት  ስላጋጠማቸው ግንባታቸው  መጓተቱ ተገለጿል።

ከዚህ ቀደም በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ዛሬ በቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ማወቅ ተችሏል።

በመግለጫው ላይ የተወሰኑ ሳይቶች ላይ ችግሮቹ ቢፈቱም አሁንም ግን አብዛኞቹ ሳይቶች የወሰን ማስከበር ችግር እንዳለባቸው ተነግሯል።

ፍርድ ቤቶችም ለችግሩ አፋጣኝ ውሳኔ በመስጠት የሚታየው መዘግየት ቀርፈው ማህበራቱ ወደ ግንባታ እንዲገቡ ምላሽ መስጠት አለባቸው ተብሏል።

የማህበራቱ ተወካዮችም ፤ በአፋጣኝ ወደስራ ባለመግባታቸው በየጊዜው ለሚታየው  ለግንባታ ዋጋ ንረት መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

መረጃው ከቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች። ቤተክርስቲያን ፤ ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ…
ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው ከደቂቃዎች በፊት ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " አሁን አሳፍረውኝ ተመለስኩ፤ ወደ አሜሪካ ወደመጣሁበት መለሱኝ ፤ ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ። " ብለዋል።

ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃላቸውን በሰጡበት ወቅት አውሮፕላኑ ሊነሳ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ የሚደረግበት ምክንያት ምንድነው ? ተብለው ተጠይቀው ፤ ብፅዕነታቸው ፤ " በቃ ግሪን ካርዱን ብቻ ነው የምንፈልገው እኛ ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም ግሪንካርድ ብቻ ነው የምንፈልገው ብለው ወሰዱ በሩን ዘጉ !! " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ያደረጉት የደህንነት ሰዎች ናቸው ብለዋል።

ብፅዕነታቸው ወደ አውሮፕላን እንዲገቡ ከመደረጋቸው በፊት ውጭ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር ተናግረው አንድ የኢሚግሬሽን ሰው " የማውቀው ነገር የለም ግሪንካርዱ ትክክል አይደለም " እንዳላቸውና እሳቸውን ግሪንካርዱ ገና 3 ዓመት እንደሚቀረው እንደነገሩት አስረድተዋል።

ይህን ሲያስረዱ ከግለሰቡ መልስ እንዳልተሰጣቸውና " ሌሎች ሰዎችንም #ዲፖርት እያደረግን ነው " በማለት እንደነገራቸው ገልጸዋል።

ብፅዕነታቸው የአሜሪካ ፓስፖርት እንዳላቸው ገልጸው ፤ " እሱን ምንም ለማድረግ ስላልቻሉ ግሪንካርድ እንወስዳለን በማለት ወስደዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሳምንታት በፊት ለአገልግሎት ከሀገር ሲወጡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎችም " ሊያስቀሩህ ይችላሉ " የሚል ነገር ሰምተው እንደነገሯቸው ነገር ግን በአሜሪካ የያዙትን አገልግሎት መተው ስላልፈለጉ ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ገልጸዋል።

ብፅዕነታቸው ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት " ኮበለሉ " የሚሉ መረጃዎች ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል። በኃላም ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ ፤ በህጋዊ መንገድ በቤተክርስቲያን እውቅና ከሀገር እንደወጡ ፤ የሚደበቁም ሆነ የሚኮበልሉ የወንጅል ሰው እንዳልሆኑ አሳውቃ ነበር።

@tikvahethiopia