TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባይቶና

በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው  "ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የተባለ የፓለቲካ ድርጅት ሙሉ እውቅና ማግኘቱ አስታውቋል።

በእነ ዶ/ር ፀጋዛኣብ ካሕሱ ከሚመራው " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ደርጅት ተነጥሎ የወጣው ባይቶና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና ማግኘቱን ገልጿል።

በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው  " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ፓርቲ ጥር 22/2016 ዓ.ም ባሰራጨው መረጃ እንዳመለከተው ፤ ከጥቅምት 17 - 18 / 2016 ዓ.ም መስራች ጉባኤ ማካሄዱ አስታውሶ " ከብዙ ውጣ ውረድ ሁሉም መስፈርቶች በሟሟላት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና አግኝቻለሁ " ብሏል።

ድርጅቱ ለሁሉም አመራሮቹ ፣ ለአባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ለመላው የትግራይ ህዝብና የትግል አጋሮቼ ላላቸው የአንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ማስተላለፉ የዘገበው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                          
@tikvahethiopia            
#DrDessalegnChane

በ2013 ዓ/ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) መታሰራቸውን ቤተሰባቸውን ዋቢ በማድረግ አል አይን አማርኛው አገልግሎት ዘግቧል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ቤተሰብ አባል ፤ " ትናንት ጥር 22 ቀን 2016 ዓ .ም ምሽት 3:30 ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት የጸጥታ ሀይሎች መጥተው ደሳለኝ ጫኔን ለጥያቄ እንፈልግሀለን ብለው ወስደውታል " ብለዋል።

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ ተናግረውም ፤ " የፌደራል ፖሊሶቹ ለጥያቄ እንፈልግሀለን " ከማለት ውጪ ምንም ያሉት ነገር የለም ሲሉም ተናግረዋል።

ዛሬ ጠዋት ጀምሮም ተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መኖሪያ ቤቱ መጥተው ፍተሻ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ ጉዳዩን በተመለከተ ተጠይቀው ፤ " አሁን ላይ ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም " ሲሉ መናገራቸውን አል አይን አማርኛው ክፍል በዘገባው ገልጿል።

@tikvahethiopia
ሀይሌ ሆቴል ወላይታ ተመረቀ።

በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ 1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ ባለ 4 ኮከብ ሆቴል ተመረቀ።

ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ በዚሁ መርሀ ግብር ባደረጉት ገለጻ፣ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ፦
- በጅማ፣
- በደብረ ብርሃን
- በሻሸመኔ ከተሞች ሦስት ሆቴሎችን ለማጠናቀቅ ማቀዳቸውን ጠቁመዋል።

ሻለቃ ሀይሌ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ዞን አዲስ የተመረቀው ሆቴል 1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት፣ ፕሮጀክቱ እንደዘገየ፣ ለዚህም የግንባታ ዕቃዎች መወደድ፣ ከውጪ የሚመጡ ዕቃዎች የምንዛሪ ዕጥረት ፈታኝነት ምክንያቱ እንደነበር አውስተዋል።

ሆቴሉ “107 ሩሞች አሉት” ያሉት ሻለቃ ሀይሌ፣ ላለፉት 4 ዓመታት መሬቱን ከመቀበል ጀምሮ የዞኑና የክልሉ ባለሥልጣናት ላደረጉላቸው ቀና ትብብር አመስግነው፣ “ሆቴሉ የህብረተሰቡ ሀብት ነው” ብለዋል።

ለአካል ጉዳተኞች አካታችነት በምን ደረጃ ነው? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሻለቃ ሀይሌ፣ “ዋናው ሊሰራ የታሰበው እሱ ነው። ዋናው ኮከብ ለማግኘት ያለ አካል ጉዳተኞች እኮ አይሆንም” ብለዋል።  

በመርሀ ግብሩ የተገኙት የሻለቃ ሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ በበኩላቸው፣ የሻለቃ ሀይሌ ሆቴልና ሪዞርት ግንባታዎችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ወደ አህጉሪቱ ይዞ የመውጣት (ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ይዞ የመንቀሳቀስ) ዕቅድና ዓላማ መያዙን አመላክተዋል።

የሻለቃ ሀይሌ ሆቴልና ሪዞርት ወላይታ ሶዶ ጀነራል ማናጀር አቶ ጌትነት ታሪኩ በበኩላቸው፣ ሆቴሉ በውስጡ ምን ምን ይዟል ? ለሚሉት ጉዳዮች በሰጡት ማብራሪያ ፦
107 የዕንግዳ መቀበያ ክፍሎች፣
በየፊናቸው እንደዬ አቅማቸው ከ15 - 600 ሰዎች የመያዝ አቅም ያላቸው 7 ቅንጡ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ 
የወላይታ ባህላዊና የውጪውን ጨምሮ ሦስት የምግብ አዳራሽ / ሬስቶራንቶች፣
የለስላሳና የአልኮል መሸጫ 2 ባሮች
የጤናና የውበት ሳሎኖች
ጂምናዜም፣
ማሳጅ፣
ስቲም ባዝ ሩሞች መካተታቸውን ገልጸዋል።

አዲሱ ሆቴል የፈጠረውንና ለመፍጠር ያቀደውን የሥራ ዕድል በተመለከተም፣ በአሁኑ ወቅት 160 ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ፣ ሆቴሉ ሙሉ ለሙሉ ሥራውን ሲጀምር እስከ 300 ሰዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን አስረድተዋል።

መርሀ ግብሩ ሻለቃ ሀይሌ፣ ባለቤታቸው፣ የክልልሉ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላና የተለያዩ የመንግሥት አካላት ተገኝተዋል።

መረጃውን ያደረሰን በመርሀ ግብሩ የተገኘው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DStv

ቀላል እና ፈጣን መላ ለዲኤስቲቪ ደንበኞች በሙሉ!

ወደ ዲኤስቲቪ የጥሪ ማዕከል ሳይደውሉ በማንኛውም ሰዓት በሞባይልዎ *9299# በመደወል እና My DStv App ስምዎንና የስማርት ካርድ ቁጥርዎን አስገብተው የዲኤስቲቪ ክፍያ መጠንዎንና ቀኑን በቀላሉ ለማወቅ ፓኬጅ ለመቀየር ብሎም በቴሌብር ፣ በሲቢኢ ብር እና በአዋሽ ብር መክፈል ይችላሉ።

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk

የፕሌይ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/3qJ95Us 

የአፕ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/45hIwEU

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#AddisAbaba

ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሸዋ ሱፐርማርኬት አካባቢ በመገንባት ላይ ያለ ህንጻ የአፈር  ክምር ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

ህይወቱ ያለፈዉና ጉዳት የደረሰበት ሰዉ  በዚሁ የህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ናቸዉ።

አደጋው የተከሰተበት የህንጻ ግንባታ ስራ  አሁንም ለአደጋ ስጋት በመሆኑ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የሚመለከታቸዉ አካላት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።

በዚሁ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ከ3 ቀናት በፊት በህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ 2 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፎ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#FederalGovernment

የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚፈልግ የፌዴራል መንግሥት ገለጸ።

የፌዴራል መንግሥት ፤ ሕወሓት ትላንትና ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን #በአንክሮ እንደተመለከተው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሔ የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን የኢፌድሪ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል።

ይሄንንም በተመለከተ የፌዴራሉ መንግሥት ከመነሻው እስካሁን ያለው አቋም ወጥ እና የማይናወጥ መሆኑን በመግለጫው አረጋግጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

" ህወሓት " ትላንትና ያወጣው መግለጫ በዚህ ተያይዟል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/84794?single

@tikvahethiopia