TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TPLF

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ በራሳቸው ፍቃድ ከሃላፊነት መልቀቃቸው እየተነገረ ይገኛል።

ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ ጥር 21 /2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፅፍውታል በተባለና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ የመልቀቂያ ደብዳቤ ፤ " ከጥር 21 /2016 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንደለቀቅኩ አስታውቃለሁ " ብለዋል።

ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በፌደራል ደረጃ ታጣቂዎች በማቋቋም ወደ ቀድሞ ህይወታቸው እንዲሰማሩ በሚሰራው መንግስታዊ መስሪያ ቤት ተሹመው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል ሲል የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ህወሓት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር የለም ፤ ከማዕከላይ ኮሚቴ አባልነት ስለመልቃቸውንም ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ በይፋ አልሰጠም።

Via @tikvahethiopiaTigrigna                             
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በህዝብ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ፦ * እንዳይቸገሩ ፣ * መንገድ ላይ ሰልፍ ተሰልፈውም ጊዜያቸው እንዳይጠፋ ፣ * ባሰቡበት ሰዓት በህዝብ ትራንስፖርት ያሰቡበት ቦታ እንዲደርሱ በተለየ ሁኔታ ለተወሰነ ሰዓት የግል ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ #ለመገደብ እየተሰራ ይገኛል። ይህ በቅርብ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል። የትራንስፖርት…
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ፦

- በነዳጅ የሚሰራ #አዲስ ሆነ #አሮጌ የግል አውቶሞቢል መኪና ወደ ሀገር ማስገባት አይቻልም። ሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ኤሌክትሪክ ብቻ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።

- የነዳጅ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ከአምና ጀምሮ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ታግዷል። ግን እስከ ቅርብ ጊዜ በተለያየ መልኩ የሚገቡ ነበሩ። ለምሳሌ ፦ ከውጭ #ተመላሽ ዳይስፖራ ተብሎ እነሱ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም ነበር፤ እነሱ የነዳጅ ሲያስገቡ አይከለከሉም ነበር። ይህ ግን አሁን ላይ አይሰራም። የግል አውቶሞቢል በማንኛውም ምክንያት በዳይስፖራ ሰበብም ይሁን በምንም ሁኔታ እንዲገባ አይፈቀድም።

- የመኪና አስመጪዎች የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ብቻ ነው ማስገባት የሚችሉት።

- በጣም ያረጁ መኪናዎች ከአገልግሎት እንዲወጡ አዋጅ ወጥቷል። ህግም ወጥቶ መኪናዎች መስጠት የሚችሉት አገልግሎት በእድሜያቸው ልክ እንዲሆንና እድሜያቸው ከአገልግሎት ዘመናቸው ውጭ የሆነ ከገበያ ውና ከአገልግሎት እንዲወጡ የሚሄዱበት ሁኔታ እየተሰራ ነው።

- በተለይ አዲስ አበባ ትንንሽ ሰዎችን ከሚጭኑ ታክሲዎች ይልቅ በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎችን የሚጭኑ ብዝሃ ትራንስፖርት እየተበረታቱ ነው። በሂደት አዲስ አበባ ውስጥ እንደሌሎች ያደጉ ከተሞች 10 እና 12 ሰዎች የሚጭኑ ሚኒባስ ታክሲዎች ከአገልግሎት እየወጡ እንዲሄዱ ይደረጋል። ይህ መጨናነቁንም ፣ ብክለቱን ከከተማ ያስወጣል።

- የብዝሃ ትራንስፖርትን በማሳደግ የተሽከርካሪ ቁጥር ለመቀነስም ታስቧል። የብዝሃ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እንዲሆንም እየተደረገ ነው። አዲስ አበባ በቅርብ የሚገዛቸው ባሶች የኤሌክትሪህ ይሆናሉ።

- ከዚህ በኋላ የመኪና ሰሌዳ ዝም ብሎ አይሰራጭም። አስመጪዎች ሰሌዳ እየወሰዱ / በብዛት እየገዙ ድንበር አካባቢ ሄደው አዲስ / አሮጌ መኪና ላይ በመግጠም እንደነባር ህጋዊ መኪና እያሽከረከሩ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። የተራጋ አሰጣቱን ለመቆጣጠር ይሰራል።

- በአዲስ አበባ የፓርኪንግ ቦታ በቅርብ ኖሮ መንገድ ላይ መኪና እንዳይቆም ለማድረግ እየተሰራ ነው። በከተማው በ2 ኪሎ ሜትር አቅራቢያ ፓርኪንግ ካለ ባልተፈቀደ ቦታ ማቆም እንዳይቻል አስገዳጅ ስራ እየተሰራ ነው።

- የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት እንዳይቸጉሩና ባሰቡት ሰዓት ያሰቡበት እንዲደርሱ፣ ሰልፍ ተሰልፈው መንገድ ላይ እንዳይቆሙ ለማድረግና የህዝብ ትራንስፖርት በፍጥነት እንዲመላለስ የግል መኪና ተጠቃሚዎች እንቅስቃሴ እንዲገደቡ ይደረጋል። ይህ የሚሆንበት ሰዓቶችም ተለይተው ተመርጠዋል። በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ " በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይቻል ይታወቅ " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቢከለከልም " ይሄን አልሰማንም " ያሉ ሰዎች የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ገዝተው ወደ ሀገር እያመጡ ይገኛሉ ተብሏል። ይህ የተሰማው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች…
#ኢትዮጵያ

ገንዘብ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ #አለመከልከሉን ገለጸ።

ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢል እንዳይገቡ #መከልከሉን ማሳወቁ አይዘነጋም።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህግ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ ምን አሉ ?

- በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በመከልከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ የሚፈቅድ ምንም አይነት መመሪያም ሆነ ውሳኔ የለም።

- ገንዘብ ሚኒስቴር እያከናወነ ያለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማበረታታት እና በነዳጅ የሚሰሩ በብዛት እንዳይገቡ ተስፋ ለማስቆረጥ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ የተደነገገበት ሁኔታ አለ።

- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማገድ በዓለም የንግድ ድርጅት ህግ መሰረት የማይቻል በመሆኑ የሀገሪቱን የቀረጥ ስርዓት በመጠቀም ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቀሙትን ማበረታታት ጎጂ የሆኑትን እንዳይስፋፉ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው።

- በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ለፓርላማ ስለቀረበው ጉዳይ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።

- ገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንዲገቡ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ተደርጓል። አዋጁ፦
* ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው ለሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች 5% ኤክሳይዝ ታክስ
* ተበታትነው ገብተው ሀገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚያስችል ነው።
* በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንደሚጠቀሙት የነዳጅ መጠን 10% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተደርጓል።

- የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ነጋዴዎች ተግባራዊ ማድረግ የሚጀምሩት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት 38 የተለያዩ ምርቶች ከባንክ ፍቃድ /letter of credit/ እንዳይከፈትላቸው የሚከለክለው እገዳ ከተነሳ በኃላ ነው።

- በአሁን ወቅት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ያሉት ተሽከርካሪዎች ክልከላው ከመደረጉ በፊት ተከፍቶ በነበረ LC እንጂ በልዩ ሁኔታ ተፈቅዶላቸው የሚያስገቡ ነጋዴዎች የሉም።

- የLC እገዳው ካልተነሳ በስተቀር ለንግድ ወይም ለመንግሥት መስሪያ ቤት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች በገንዘብ ሚኒስቴር እውቅና ብቻ አይገቡም። ክልከላው የማይመለከታቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ቢሆኑም በነዳጅ የሚሰራ ተሽከርካሪ በሚያስገቡበት ጊዜ በኤክሳይዝ ታክስ ተስተናግደው ነው።

ይህ የገንዘብ ሚኒስቴር አስተያየት በተመለከተ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ኃላፊ እገዳው በመመሪያ / በውሳኔ የተገለፀ አይደለም ብለዋል።

ግን ሁሉም የሚመለከታቸው መ/ቤቶች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በ100 ቀናት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በተደረገ ግምገማ በተሰጠው አቅጣጫ በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎች እንዳይገቡ መከልከሉን ገልጸዋል።

አንድ የጉምሩክ ኮሚሽን ኃላፊ ደግሞ በአሁን ወቅት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው በብሄራዊ ባንክ የወጣው ውሳኔ ላይ በመሆኑ ውሳኔው በተዘዋዋሪ በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ የተከለከለው አሁን አዲስ በተሰጠ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ብቻ አይደለም ብለዋል።

ብሄራዊ ባንክ ጥቅምት 4/2015 ይፋ እንዳደረገው ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ የተደረገባቸው 38 ምርቶች ውስጥ ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል። ከሞተር ነክ ምርቶች የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የተካተቱ ሲሆን እገዳው በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን እንደማያካት ይታወቃል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/reporter-01-31

ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የዑለማ ጉባዔ የ2ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ጉባኤው በመግለጫው ፦

- በየሳምንቱ የሚደረገው የጁምዓ ኹጥባ አርካኑን በጠበቀ መልኩ በአረብኛ ቋንቋ መሆኑ የተመረጠ ቢሆንም እንደ አስፈላጊነቱ ማህበረሰቡ እንዲረዳው በተለያዩ ቋንቋዎች ቢደርግ ችግር እንደሌለው ጉባኤው መስማማቱ ተገልጿል። በተጨማሪም የቁርአንናና የሐዲስ ጥቅሶች ባሉበት በአረብኛ ቋንቋ ተነበው መተርጎም አለባቸው ብሏል።

- በሸሪአ የተፈቀደው የጋብቻ አይነት በተቃራኒ ጾታዎች ማሃከል የሚደረግ ጋብቻ ብቻ ሲሆን የተፈጥሮ ህግንና ሸሪአን በተፃረረ መልኩ የሚደረገውን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግንኙነት በሸሪዓ በጥብቅ የተከለከለና የአላህን ቁጣ የሚያስከትል ተግባር በመሆኑ ጉባኤው #በጥብቅ_እንደሚያወግዝ አሳውቋል።

- የኢትዮጵያ ዑላማዎች ለሰላም ዘብ እንደሚቆሙ ፤ ህዝበ ሙስሊሙም ለአገር ሠላም ዘብ እንዲቆም ፤ በአገራችን የሚታዩት አለመግባባትና ግጭቶች በሰላማዊ መልኩ በውይይት እንዲፈቱ ለመንግስትና ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ሁሉ ጥሪውን አስተላልፏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF #ህወሓት

ክልላዊ ፣ አገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ባካተቱ 6 ነጥቦች ላለፉት ከ41 ቀናት በላይ ስብሰባ መቀመጡን የገለፀው ህወሓት ዛሬ ባለ 6 ገፅ መግለጫ አውጥቷል።

ጥር 22/2016 ዓ.ም ባወጣው መገለጫ እንዳስታወቀው ረጅም ጊዚያት ወስዶ ያካሄደው የድርጅቱ የፓሊትና የማእከላይ ኮሚቴ  የግምገማ ፣ የሂስና የግለሂስ መድረክ ወደ ቀጣዩ ጉባኤ የሚያሸጋግሩ ወሳኔዎች የተወሰኑበት ነው ብሏል።

ህወሓት በመግለጫው  ፦
- ለትግራይ ህዝብ
- ለድርጅቱ አመራርና አባላት
- ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች
- ለኤርትራ ህዝብ
- ለዓለም ማህበረሰብና ለትግሉ ደጋፊዎች እንዲሁም ሌሎችም አካላት መልእክት አስተላልፈዋል። 

ህወሓት በተለይ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች ባስተላለፈው መልእክት ፤ " ህወሓት ለትግራይ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች የሰላም ስትራቴጂክ አማራጭ ከመሆን በዘለለ በማንም ህዝብ ላይ ጥላቻ አንደሌለው አረጋግጣለሁ " ብሏል።

" ከኤርትራ ህዝብ የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረግ የትግል አጋርነት ነበረን አጋርነቱና የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ መደጋገፉ ይቀጥላል " ያለው ህወሓት " የኤርትራ ህዝብ የኤርትራ ሰራዊት በሃይል ከያዛቸው የትግራይ ግዛቶች ለቆ እንዲወጣ ጫና እንዲያሳድር የሚያስታውስ ጥሪ አስተላልፈዋል። 

ህወሓት " ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብና ከትግላችን ደጋፊዎች " በሚል ባስተላለፈው መልእክት " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ፣ ስምምነቱ መሰረት ያደረገ ውይይት እንዲካሄድ ፣ የትግራይ የግዛት አንድነት እንዲረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፣ የትግራይ መልሶ ግንባታ እንዲፋጠን ፣ ሰብአዊ ወንጀል የፈፀሙ በዓለም አቀፍ ህግ እንዲዳኙ እንዲደረግ የበኩላችሁ እንድትወጡ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል " ማለቱ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።    
                                       
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመውጫ ፈተና ተራዘመ።

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ መራዘሙን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ማረጋገጥ ችሏል።

የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።

Via @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
Jasiri Talent Investor Programme is now welcoming bold and brave aspiring women Ethiopian entrepreneurs ready to lead and innovate. It's more than a program—it's your opportunity to rise as a future leader. Apply for Cohort 6 today at jasiri.org/application and join a network committed to empowering women in business. #FutureFemaleLeaders #JASIRITalentInvestor #WomenEntrepreneurs #Ethiopia #Innovation #Leadership
#CBE

በቲክቶክ ያግኙን!
*********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ትክክለኛ የቲክቶክ ገጽ (https://www.tiktok.com/@combankethiopia) በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ!
********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
" ለ ' ህወሓት' የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ

በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ለ "ህወሓት" እውቅና ስለ መሰጠቱ የሚሰያጨው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተለይም በፌስቡክ ለ " ህወሓት " እውቅና ስለመሰጠቱ #ሀሰተኛ_መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን በተደረገ ቅኝት ማየት መቻሉን የገለፀ ሲሆን ለ " ህወሓት " የተሰጠ እውቅና #እንደሌለ ቢሮው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው እለት ፦
- ለወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
- ለኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ
- ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ለተባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አሳውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለ "ህወሓት" እውቅና ተሰጠ ተብሎ የሚሰራጨው #ሀሰተኛ_መረጃ ፥ መረጃውን የእውነት ለማስመሰል እየተደረገ ያለ ሙከራ መሆኑን የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያስረዳ ሲሆን " ለህወሓት የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " ብሏል። 

ማንኛውም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን የተመለከተ መረጃ በቦርዱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እስካልወጣ ድረስ መረጃዎቹ ሀሰተኛ መሆናቸውንና ቦርዱን የማይወክሉ መሆኑን እንዲታወቅልኝ ሲል ቦርዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia