TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CBE

በርካታ አማራጮች...
***
ለጥምቀት በዓል ከውጭ ሀገር በመረጡት
ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ገንዘብ ያስልኩ!

መልካም የጥምቀት በዓል!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***

የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!  
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh  
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ ይሻል " - ኢሰመኮ ኢሰመኮ አሰባሰብኩ ባለው መረጃ እና አነጋገርኳቸው ያላቸው የአስተዳድር መዋቅር ጠያቂዎች እንደገለፁት በጋሞ ዞን ፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ፦ * ኤልጎ * ወዘቃ * ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ…
#ደቡብኢትዮጵያክልል:- ከአስተዳደራዊ መዋቅር ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች ነዋሪዎችን ያሳተፈና አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔ ይሻል ሲል ኢሰመኮ አሳውቋል።

በነሐሴ ወር 2015 በቆላ ሻራ ቀበሌ ለደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ከኃይል እርምጃዎች መቆጠብን ጨምሮ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ማስጀመር እና በሀገራዊ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል።

ኢሰመኮ የላከልን ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
 
" ፍተሻው መጠንከር አለበት ብለን ካመንን እናጠናክራለን ፤ የፍተሻ መጠናከር የሚከፋው ሰው ይኖራል ብለን አንገምትም " - ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ

የከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላምና በድምቀት እንዲከበር በፀጥታው ኃይል በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን አሁን በዓሉን እየተጠባበቀ ይገኛል።

የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፤ " የአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆ የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረኃይል በዛ ስር ያሉ የፀጥታ ተቋማት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ስራ ላይ ናቸው " ብለዋል።

" በመዲናዋ ታህሳስ ወር ውስጥ በተካሄዱ የህግ ማስከበር ዘመቻዎች በርካታ ግኝቶች ተገኝተዋል ፣ ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል የነበሩት ኦፕሬሽኖች የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ትልቅ አውንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

የፀጥታ ኃይሉ ከእምነት አባቶች ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት ማድረጉንም ጠቁመዋል።

" የተለየ ተልዕኮ ያላቸው ሰዎች በተለያየ መንገድ ፍላጎታቸውን ለማንፀባረቅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፤ በተለይ ህትመት ቤቶች አካባቢ በፅሁፍ ፣ በምስል ሊሆን ይችላል የተለያዩ ነገሮችን በመቅረፅ ህገወጥ መልዕክቶች እንዳይተላለፉ ከእምነት አባቶች ጋር ውይይት እና መግባባት ተደርሷል " ብለዋል።

ከበዓሉ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ወጣቶች እየተያዙ ነው፣ ፍተሻዎችም ጠንክረዋል በዚህ ላይ ፖሊስ ምን ይላል ሲሉ የተጠየቁት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ " ፖሊስ በተለያዩ ቦታዎች ያለውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የት ቦታ ፍተሻ መደረግ አለበት ?  ... ፍተሻው መጠንከር የሚገባው ከሆነ እናጠናክረዋለን  ፤ ፍተሻ መጠናከሩ የሚከፋው ሰው ይኖራል ብለን አንገምትም " ሲሉ መልሰዋል።

" ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ በሚደሩ ፍተሻዎች ለወንጀል መፈፀሚያ የሚሆኑ ስለቶች፣ የጦር መሳሪያዎች ሳይቀር በቁጥጥር ስር እናውላለን ፣ የተሰረቁ ሰሌዳዎች፣ መታወቂያ የሌላቸውን ሰዎች የምናገኝበት ሁኔታ አለ " ያሉት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ " በሃይማኖታዊ በዓላት በርካታ ሰው አደባባይ ወጥቶ በሚያከብርበት ወቅት ህግ ማስከበራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ማንም ሰው ካጠፋ መያዝ ካለበት በህግ አግባብ ይያዛል ፣ እኛ የምንፈልገው ባህላዊና ሃይማኖታዊ ገፅታው ብቻ እንዲጎላ ነው ሌሎች መልዕክቶች በፍፁም እንዲተላለፉ አንፈቅድም ፖሊስም አይታገስም " ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምክትል ኮንደር ማርቆስ የሰጡትን ቃል ያዳመጠው ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ከሰጡት ማብራሪያ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#Mekelle #ኣሉላ_ኣባነጋ_ኤርፖርት

" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ግለሰብ

ተሳፋሪዎች የጫነ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ከቀኑ 8:00 ሰዓት አከባቢ አደጋ እንደገጠመው ተሰምቷል።

ለአውሮፕላን ማረፍያው ቅርበት ያላቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ግለሰብ ለመቐለ ኤፍኤም 104.4 በሰጡት ቃል ፤ አውሮፕላኑ መንሸራተት አጋጥሞት ከዋናው መንገድ መውጣቱንና በሰው ህይወት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተናግረዋል።

የአውሮፕላን የአደጋው መነሻ በመጣራት ላይ መሆኑም አስተያየት ሰጪው አክለው ገልፀዋል።

መረጃውን የመቐለ ኤፍ ኤምን ዋቢ በማድረግ ያደረሰን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መቐለ #ኣሉላ_ኣባነጋ_ኤርፖርት

በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች " ወደ መቐለ ሊያመራ የነበረ አውሮፕላን አደጋ አጋጠመው " በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች #ትክክለኛ_አይደሉም

ዛሬ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የመንገደኞች አውሮፕላን መንገደኞችን እንደያዘ በመቐለ " አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ " አደጋ አጋጥሞታል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ግለሰብም ፤ አውሮፕላኑ መንሸራተት አጋጥሞት ከዋናው መንገድ መውጣቱን ገልጸዋል።

በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

የአውሮፕለን አደጋው ዝርዝር መነሻ ላይም ማጣራት እየተደረገ ነው ተብሏል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወትም ዛሬ 8 ሰዓት ላይ አውሮፕላኑ ተንሸራቶ ከዋናው መንገድ በመውጣት አደጋ የገጠመው በመቐለ አለላ አባነጋ ኤርፖርት መሆኑን ገልጸው ፤ በመንገደኞች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም በመቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ስለተፈጠረው ነገር መረጃ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ሆኖ ሳለ አደጋው " ወደ መቐለ ሊበር ሲል በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት " እንደደረሰ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ እየወጡ ያሉት መረጃዎች ትክክል አይደሉም።

መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የችግሩን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የበረራ ቁጥሩ " ኢቲ106 " የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ " አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ " ችግር እንዳጋጠመው ይታወቃል።

ይህ በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?

- የአውሮፕላኑ በረራ ቁጥር ET106/18 ነው።

- ከአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት የተነሳው ቀን 6:30 ላይ ነው።

- ክስተቱ ያጋጠመው በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀኑ 8 ስአት አካባቢ ነው። በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራቶ ወጥቷል።

- ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድን አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወጥተዋል።

- ችግሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ / የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

በተፈጠረው ችግር መጉላላት ለደረሰባቸው መንገደኞችም #ይቅርታ ጠይቋል።

Video Credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።

የከተራና የጥምቀት በዓልን ተከትሎ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ለትራፊክ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በጥምቀት በዓል በርካታ ህዝብ ታቦታትን አጅቦ ከተለያዩ ቤተ-ክርስቲያናት ወደ ጥምቀተ ባህር የሚንቀሳቀስ በመሆኑ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን በተለይም በርካታ ህዝብ በሚታደምበት በጃን ሜዳ ከጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው እስኪመለሱ መንገዶቹ ለተሸከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-

- ከ6ኪሎ አደባባይ እስከ 3ተኛ ሻለቃ ፈረንሳይ ለጋሲዬን መንገድ

- ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ በምንሊክ ሆስፒታል እስከ ቀበና አደባባይ

- ከምንሊክ ሆስፒታል እስከ 6 ኪሎ ታክሲ ተራ

- ከቅድስተ ማርያም ቤ/ክርስቲያን እስከ 6 ኪሎ፣

- ከ6ኪሎ እስከ መነን፣

- ከሀምሌ 19 እስከ ግብፅ ኢምባሲ፣

- ከቅድስተ ማሪያም መነጸር ተራ እስከ ጃንሜዳ፣

- ከግንፍሌ ድልድይ ምንሊክ ሆስፒታል ውስጥ ለውስጥ፣

- ከግንፍሌ መገንጠያ ምንሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣

- ከምንሊክ ሆስፒታል የኋላ በር እስከ ቤላ መገንጠያ ድረስ፣ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳና በዙሪያው ተሽከርካሪ አቆሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ እየገለፀ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትእዛዝ በመቀበል የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia