#ኦሮሚያ
በመንገደኞች ላይ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።
በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ መንገደኞችን አሳፍሮ በሚሄድ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ጥቃት ህይወት መጥፋቱን እና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል።
ግድያው የተፈፀመው ዛሬ አርብ መስከረም 4 ቀን 2016 በ " አንዶዴ ዲቾ " የሚባል ቦታ ላይ መሆኑን ተነግሯል።
ግድያውን በተመለከተ የዞኑ አስተዳደር የፀጥታ ቢሮ ፤ " ድርጊቱ የተፈፀመው ዲቾ ላይ ነው " ያለ ሲሆን ከአንገር ጉተን ወደ ጊዳ በሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው " ሲል ገልጿል።
የፀጥታ ቢሮው የድርጊቱ ፈፃሚዎች " የአማራ ፅንፈኛ ታጣቂዎች " ናቸው ብሏል።
ቢሮው ፤ " በአካባቢው ጸጥታውን የሚያውኩ ታጣቂዎች አሉ። ታጣቂዎቹ በተሽከርካሪ የሚጓዙ ሰዎችን በመንገድ ላይ በማስቆም ነው ድርጊቱ የፈፀሙት " ሲል ገልጿል።
ዲቾ ላይ እስከ 30 የሚደርሱ ሰዎች እንደተገደሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ዘገባዎች ተሰራጭቷል።
ሆኖም ግን የዞኑ አስተዳደር የተገደሉት አምስት ሰዎች እንደሆኑ ገልጿል።
ቃሉን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የሰጠው ተጎጂዎቹ ለህክምና የተወሰዱበት የጊዳ አያን ሆስፒታል ባለሙያ (ለደህንነቱ ስሙ ያልተጠቀሰ) በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አምስት ነው ብሏል።
ባለሙያው " በመጀመሪያ አምስት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ እኛ መጡ " ያለ ሲሆን እነዚህ አስቸኳይ ህክምና ካገኙ በኋላ የአራት ሰዎች አስክሬን ደረሰ ፤ ሆስፒታል ውስጥ ከነበሩት ውስጥ አንዱ በህክምና ላይ እያለ ህይወቱ አልፏል ሲል ተናግሯል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ በህክምና ላይ የሚገኙት እና አስክሬናቸው እነሱ ጋር የመጣ ሰዎች በሙሉ #ወንዶች ናቸው።
" አሁን አራት ሰዎችን እያከምን ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እነሱን ለማዘዋወር ምንም ምቹ መንገድ የለም፣ ጉዳቱ ከአቅማችን በላይ ነው። የደም እጥረት አለብን " ብለዋል ባለሙያው።
በነገው እለትም የጸጥታ ሃይሎች ተጎጂዎችን ወደ ተሻለ ህክምና መስጫ መውሰድ ከቻሉ ይህንን ለማድረግ መታቀዱንም ተናግረዋል።
በህክምና ላይ ያሉ ሁሉም የተጎዱ ሰዎች በጥይት ተመትተዋል ብለዋል።
የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዘገባ ሀሰት ነው ብሏል።
አሁን ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ እና በሌሎች አካባቢዎች ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳትና ማፈናቀል እያደረሱ እንደሆነ የገለፀው የፀጥታ ቢሮው ታጣቂዎቹ ወደ ክልሉ አልፈው የገቡ ሳይሆን በዛው የሚንቀሳቀሱ ፤ ትናንሽ የታጠቁ ቡድኖች ናቸው ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው የ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ነው።
NB. የሟቾች ቁጥርን በተመለከተ የሆስፒታል እና የዞን ባለስልጣናት የገለፁት ቁጥር አምስት ቢሆንም በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ከ30 በላይ እንደሆነ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭተዋል። አንድ የአካባቢው ነዋሪ ደግሞ ከሆስፒታል እና ከወረዳው ባለስልጣናት መረጃ በተለየ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች 7 ናቸው ብሎ ተጨማሪ አስክሬን እየተፈለገ ነው ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃዎችን ሲያገኝ የሚያቀርብ ይሆናል።
@tikvahethiopia