#AddisAbaba #እድታውቁት
" ነገ ህዳር 22 ቀን 2016 ዓ/ም የመሬት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመሮች ጥገና ስለሚከናወን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል " ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።
የመሬት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመሮች ጥገና የሚከናወነው ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንደሆነ አገልግሎቱ ገልጿል።
በዚህም ፦
- ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ፣
- ለገሐር ጀርባ፣
- ለገሐር አሸዋ ተራ፣
- ኤግዝቢሽን ሴንተር፣
- ፍላሚንጎ፣
- ኦሎምፒያ፣
- ደንበል፣
- ደንበል ጀርባ፣
- ፐርፕል ካፌ፣
- ቦሌ ማተሚያ ቤት፣
- ተወካዮች ምክር ቤት መኖሪያ፣
- ፒኮክ መናፈሻ፣
- አስቴር ቡና፣
- ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣
- ኮካኮላ፣
- ኢዩበልዩ ቤተ መንግስ፣
- ኢትዮጵያ ሆቴል፣
- ኢቢሲ፣
- ቤተዛታ ሆስፒታል፣
- ኦሮሚያ ባሕል ማዕከል ጀርባ፣
- ጊዮን ሆቴል፣
- እስጢፋኖስ ድልድይ አካባቢ፣
- ኃይለ ዓለም ሕንጻ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል እንደሚቋረጥ ተገልጿል።
" ደንበኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ " ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል።
@tikvahethiopia

ሰላም ሚኒስቴር ምን አለ ?
* ጋዜጠኞች ምላሽ እንዳይሰሙ እንዲወጡ ተደርጎ ምላሽ በዝግ ተሰጥቷል።
የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ3 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ አቅርቦ ነበር።
የሰላም ሚኒስቴር ባቀረበው ሪፖርት፦
- የጎሣ ግጭቶች #ስለመቀነሳቸው፣
- በክልሎች ውስጥ እንጂ፣ በክልሎች መካከል የሚደረግ ግጭትም እየቀነሰ ስለመሆኑ አስታውቋል።
ከቋሚ ኮሚቴው ግን ብዙ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።
በኢትዮጵያ ውስጥ በንፁሐን ላይ ጉዳት እየደረሰ፤ እየሞቱ፤ እየታገቱ ገንዘብ እየተጠየቀባቸው ስለመሆኑ እንዲሁም የሕዝብ የመንቀሳቀስ መብት እየተገደበ ፣ መንገድም የተዘጋባቸው አካባቢዎችም ያሉ መሆናቸው ተነስቶ ችግሩን ለመፍታት የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ምን ሠሩ ? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።
ግጭቶች መታየት እና የታጠቁ ኃይሎች ሕግን የመጣስ፣ ሰላምን የማደፍረስ ምክንያት ፤ በንፁሃን ዜጎች ሕይወት፣ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ፣ ንፁሃን እየታገቱ ገንዘብ እየተጠየቁ ስለመሆኑ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
ለሚኒስቴሩ አመራሮች ሌሎች ጥያቄዎችም ቀርበው ነበር።
" ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሱ ግጭቶች በተለይ አሁን አማራ ክልል ያለው ፣ ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ያለው ጉዳይ ከግጭትም አልፎ የውስጥ የትጥቅ ግጭት-ከዚያም ሲያልፍ ወደ የእርስ በርስ ወደሚመስል ነገር የሚሄዱ ነገሮች ናቸው የሚመስሉት " የሚል ጥያቄ ተነስቷል።
በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በተመለከተ ግጭቱን #አመላካች ነገሮች አልነበሩም ወይ ? በሚል የግጭት ቅድመ መከላከል ላይ ምን ተሰራ የሚል ጥያቄም ቀርቦ ነበር።
ለዚህና ለሌሎች የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች የሰጡት ምላሽ ምን እንደሆን እንዳይከታተሉ ጋዜጠኞች የሰላም ሚኒስቴርን ሪፖርት እና የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች ብቻ ታድመው እንዲወጡ በሕ/ተ/ም/ቤት የውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመታዘዙ ምላሹን ምን እንደነበር አልታወቀም።
ለምን ይህ ለምን ይሆናል ? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ " በዝግ የሚደረግ " መሆኑን ከመግለጽ በቀር ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም።
የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታየ ደንደአ ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥቂት ጥያቄዎች ለመገናኛ ብዙኃን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ ታዬ ምን አሉ ?
- መገናኛ ብዙሃን የሚኒስቴሩን ምላሽ እንዳይዘግቡ ተቋማቸው አለመከልከሉን ገልጸዋል።
- በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ቅድመ ትንተና እንደነበር፣ ሆኖም ግን " በሚመለከተው " ባሉት በግልጽ ባልጠቀሱት አካል ፋጣን ርምጃ ባላመውሰዱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።
- የአማራ ክልል ጉዳይ- " የተ/ም/ቤት ጭምር ሄዶ ህዝብ ባነገረትበ ጊዜ እንደዚህ አይነት አዝማሚያዎች መኖራቸው ቀድም ብሎ ተለይቶ ነበር። ግን ችግሮችን ከመፍታትና አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነትና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል " ብለዋል።
- መንግሥት ከሕወሓት ጋር እንዲሁም ከኦነግ ሸኔ ጋር የዘለቀበትን ግጭት ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት በበጎ ጠቅሰዋል። በአማራ ክልል ያለውም በዚያው መንገድ " ሊታይ ይችላል የሚል እምነት " እንዳላቸው ገልፀዋል።
- " በመንግሥትም በኩል ረጅም መንገድ ሄዶ፣ በሌላ ወገን ያለውም ያለበት መንገድ አዋጭ እንዳልሆነ በማመን መሀል መንገድ ላይ መነጋገር ያስፈልጋል ተብሎ አቅጣጫ ተሰጥቶ በዛ ደረጃ እየተሰራ ይገኛል የአማራ ክልልም ጉዳይ በዚሁ ማዕቀፍ ሊታይ ይችላል የሚል እምነት አለኝ " ሲሉ ተናግረዋል።
Credit - DW RADIO / ሰለሞን ሙጬ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለስኬትዎ ብርቱ አጋር ነን!
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ: https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
#globalbankethiopia #bankinEthiopia #financeinEthiopia

M-PESA መጣልን!
ከንግድ ባንክ፣ ከአቢሲኒያ ባንክ፥ ከዳሽን ባንክ፣ ከአዋሽ ባንክ እና ከአባይ ባንክ አካውንትዎ ወደ M-PESA አካውንትዎ እንዲሁም ከM-PESA አካውንትዎ ወደ ባንክ አካውንትዎ ገንዘብ በቀላሉ መላክና መቀበል ይችላሉ።
ፕለይ ስቶር/ አፕ ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricomET #FurtherAheadTogether

በኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፤ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅን የማውጣት ሂደት እጅግ መዘግየት እንዳሳስበው ገለጸ።
በአዋጁ መውጣት አስፈላጊነት ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን እና ካቢኒያቸውን ለማግኘት መድረክ እንዲመቻችም ጠይቋል።
ማህበሩ ለአካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ ነጻ የሕግ ድጋፍን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን በየዕለቱ የተለያዩ አቤቱታዎችን እንደሚያስተናግድ ገልጿል።
በዚህም በአካልጉዳተኛው ማህበረሰብ ፦
- በህይወት የመኖር መብት፣
- የእኩልነት መብት፤
- የጤና መብት፤
- የትምህርት መብት፣
- የስራ እና የቅጥር መብት፣
- ፍትህ የማግኘት እና በሌሎች መብቶች ላይ የሚፈጸመው የመብት ጥሰት እየጨመረ መሆኑን እንደተገነዘበ ገልጿል።
ማህበሩ ጉልበት እግኝቶ ለቀጠለው የአካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ የመብት ጥሰት፣ ዋነኛው ምክንያት የአካል ጉዳተኞችን መብቶች የሚያስጠብቅ አዋጅ ለማውጣት የሚስተዋለው ቁርጠኝነት ማጣት እንደሆነ እንደሚያምን ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት የአካልጉዳተኞች መብት ስምምነትን ተቀብሎ ካጸደቀ 13 አመታት የተቆጠረ ሲሆን፤ ለረዥም ግዜ ስምምነቱን ለማስፈጸም ብርታት የሚሆን አዋጅ ለማውጣት የተግባር እንቅስቃሴ አልተስተዋለም ብሏል።
ይሁን እንጂ ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ መንግስት የአካልጉዳተኛውን ማህበረሰብ ፍላጎት እና መብት የሚያስጠብቅ አዋጅ ለማውጣት በእንቅስቃሴ ላይ እንዳለ ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ሊወጣ የታሰበው አዋጅ የአካል ጉዳተኛውን ማህበረሰብ ጥቅም በሚያስጠብቅ ሁኔታ ባጭር ግዜ አጠናቆ ወደተግባር ከማስገባት አንጻር ግን በአስፈጻሚው ዘንድ ሰፊ ክፍተቶች መኖራቸውም አመልክቷል።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ በአጠቃላይ የአካልጉዳተኞችን መብት የሚደነግግ እዋጅ ማውጣት አስፈላጊ እንዳልሆነ በአንዳንድ የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት የሚሰጠው አስተያየት ጉዳዩን በልኩ ባለመገንዘብ እና ግዜው የደረሰበትን የአካልጉዳተኞችን የመብት አተያይ ያልዋጀ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።
ማህበሩ የአዋጁ መውጣት የመንግስታዊ ሀላፊነት ፣ የስታስቲክስ፤ የህግ እና የሞራል መሰረት እንዳለው በጽኑ እንደሚያምን ገልጿል።
በመሆኑም ማህበሩ ፦
- የአዋጁን መውጣት አስፈላጊነት ለማስረዳት ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከካቢኔያቸው ጋር መገናኘት የሚቻልበት መድረክ እንዲመቻች ጠይቋል።
- ረቂቅ ህጉን አጠናቆ ወደተግባር ለማውረድ የሚስተዋለው ዳተኝነት በአስቸካይ እንዲታረም እና ረቂቅ እዋጁን አስመልክቶ የሚሰሩ ስራዎች ባጭር ግዜ ተጠናቀው ህጉ ወጥቶ ወደተግባር እንዲገባ ሁሉም ባለድርሻ አካል ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስቧል።
- ረቂቅ አዋጁ ጸድቆ ከ17.6 ፐርሰንት በላይ ወይም ከሀያ ሚሊየን በላይ የሚገመተው የአካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ ክፍል መብት እንዲከበር፣ ብሔራዊ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት፤ የሲቪክ ማህበራት፤ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት መንግስት ላይ ግፊት በማድረግ እና ለዚህ ማህበረሰብ ድምጽ በመሆን ህጋዊ፣ ታሪካዊ እንዲሁም ሞራላዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።
(ማህበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#NEBE
ወ/ሮ ሜላተወርቅ እና አቶ ታደሰ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው መለየታቸው ተነገረ።
በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እጩ መልማይ ኮሚቴ ከህዳር 3 እስከ 13 ድረስ 56 ጥቆማዎችን በተለያዩ የጥቆማ መንገዶች መቀበሉን ገልጿል። ከእነዚህ መካከል 52ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 4 ደግሞ ሴቶች እንደነበሩ አመልክቷል።
በዚህም በተለያዩ ሶስት ዙሮች በተለያዩ መስፈርቶች 5 ግለሰቦች የተለዩ ሲሆን በመጨረሻም መስፈርቱን ያሟሉ ሁለት እጩዎች መለየታቸው ገልጿል።
በዚህም መሰረት ፦
- ወይዘሮ ሜላተወርቅ ሃይሉ
- አቶ ታደሰ ለማ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።
ሁለቱ እጩዎች የተመረጡት ባላቸው ልምድና ተሞክሮ የፖለቲካ ገለልተኝነት እና ሌሎች መስፈርቶችን አሟልተው በመገኘታቸው ነው ብሏል።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድ ሰብሳቢ የሚያስፈልገው በመሆኑ ሁለቱ እጩዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይቀርባሉ።
በመጨረሻ ፤ ከሁለቱ አንዱ የቦርዱ ሰብሳቢ እንደሚሆኑና ሹመቱም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚፀድቅ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል

ከኤችአይቪ / HIV #የሚያድን አዲስ መድሃኒት ተገኝቷል ?
አጭር ምላሽ ፦ #አልተገኘም
ሰሞነኛው የPrEP ጥናት ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ያወጡትን ዘገባ ሰዎች በተለይም በርካታ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በተሳሳተተ መንገድ ሲረዱትም ተስተውሏል።
አንዳንዶች በሞያው ውስጥ የሌሉና በቂ ግንዛቤ የሌላቸው " ኤችአይቪ / HIV አዲስ መድሃኒት እንደተገኘለት " አድርገው ሲያጋሩም ነበር።
እውነታው ግን HIVን #የሚያድን መድሃኒት ተገኘ አልተባለም።
ከሰሞኑን በእንግሊዝ ሀገር የተደረገው ጥናት ለHIV #ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ከመያዛቸው በፊት የሚወስዱት መድሃኒት ላይ ትኩረት ያሰረገ ነው። ይህ አሰራር አዲስ ሳይሆን ቀድሞም የነበረ ነው።
የጤና ባለሞያዎች ምን አሉ ?
(ዘሪሁን ግርማ,MPH)
ማህበርሰቡ ማዋቅ ያለበት ነገር ቢኖር PrEP በHIV ከታያዝን በኃላ እንደማያገለግል ነው።
የPrEP መድሃኒት በHIV ሳንያዝ ቀድሞ የሚሰጥ የራሱ #መመሪያ ያለዉ ሲሆን የምሰጠዉም ለምሳሌ በHIV ለመያዝ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሠዎች እንደ ግብረስጋ ግንኙነትን በማድረግ ገቢ የሚያገኙ ሠዎች ፣ ለአስገድዶ መደፈር ለተጋለጡና የመሳሰሉት ናቸው።
PrEP ምንድን ነው ?
PREP፣ ወይም ቅድመ-መጋለጥ ፕሮፊላክሲስ፣ በቫይረሱ የመያዝ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ የHIV ኢንፌክሽን አደጋን ለመቀነስ የሚያገለግል ነው።
በHIV #መከላከል ስትራቴጂዎች ውስጥ ጠቃሚ መንገድ ነው
PrEP እንዴት ይሰራል ?
PrEP የሚሰራው የHIV ቫይረስ በሰውነት ውስጥ ዘላቂ የሆነ ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር በመከላከል ነው።
መድሃኒቱ ቫይረሱ ወደ ጤናማ ሴሎች እንዳይገባ እና እንዳይበከል የሚያግድ እንቅፋት ይፈጥራል።
ቫይረሱ እንዲባዛ እና እንዲሰራጭ አስፈላጊ የሆነውን reverse transcriptase የሚባል ኢንዛይም እንዳይሰራ ይከለክላል። ይህንን ኢንዛይም በመዝጋት፣ PrEP ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እራሱን እንዳይፈጥር እና የHIV ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳል።
ወቅታዊ ጥናቶች በPrEP ዙሪያ ምን ይላሉ ?
በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች የPrEPን ውጤታማነት በገሃዱ ዓለም ውጤቶች አሳይተዋል።
በእንግሊዝ በ24,000 ተጠቃሚዎች ላይ የተደረገ ጥናት PrEP በኤችአይቪ የመያዝ እድልን በ86% ቀንሷል።
እነዚህ ውጤቶች በተከታታይ እና በትክክል ጥቅም ላይ ሲውሉ የPrEPን የHIV ስርጭትን ለመከላከል ያለውን ውጤታማነት ያሳያሉ።
ጥናቱ ስለ PrEP የገሃዱ ዓለም ውጤታማነት ማረጋገጫ ይሰጣል እና ይህን የመከላከያ መድሃኒት በቀላሉ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝባል።
* * * * *
" የኤችአይቪ (HIV) መድሀኒት ተገኘ የሚል አውድ ያለው አዘጋገብ አሳሳች ነው " - ዶ/ር አሳልፍ
ዶ/ር አሳልፍ ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የኤችአይቪ (HIV) መድሀኒት ተገኘ " የሚል አውድ ያለው አዘጋገብ #አሳሳች ነው ብለዋል።
ፒአርኢፒ " Pre-exposure prophylaxis" ማለት ለኤችአይቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች (commercial sex workers, health professionals ... etc) ከመጋለጣቸው በፊት / ለቫይረሱ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት/ቀናት ውስጥ የሚወስዱት እስካሁንም በተለያዩ አማራጭ መድሃኒቶች ይተገበር የነበረ መከላከያ መንገድ እንጂ ኤችአይቪን የሚያክም (curative ህክምና) አይደለም ሲሉ አስገንዝበዋል።
" ጥናቱም እንደዛ አይልም " ብለዋል።

#እንድታውቁት
ከለሊት 8 ሰዓት ጀምሮ እስከ ነገ ረፋድ 5 ሰዓት ድረስ ሁሉም በኮር ባንኪንግ ሲስተም የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደሚቋረጡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳውቋል።
ባንኩ ፥ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ከቅዳሜ ህዳር 22 ሌሊት 8፡00 ሰዓት እስከ እሁድ ህዳር 23 ቀን 2016 ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ፦
- ኢንተርኔት ባንኪንግ
- ሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ ሁሉም በኮር ባንኪንግ ሲስተም የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደሚቋረጡ አሳውቋል።
ደንበኞቹም ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንንዲያደርጉ ብሏል።