TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የ2016 ዓ/ም የአክሱም ፅዮን ንግስ በዓል እጅግ በድመቀ ሁኔታ ተከብሯል። የዘንድሮው በዓል ጦርነት እንዲቆም የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ሁለተኛው ሲሆን ካለፈው አመት የበለጠ ቁጥር ያለው ምዕመን በዓሉን መታደሙ ተነግሯል። ወደ ከተማው የገቡ ቱሪስቶችም ካለፈው ዓመት የተሻለ ነው። የፎቶ ባለቤቶች ፦ ሚካኤል መታፈሪያ እና ትግራይ ቴሌቪዥን @tikvahethiopia
#Axum
የአክሱም ከንቲባ አቶ አበበ ብርሃነ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል በዘንድሮው የአክሱም ጽዮን ማርያም ንግስ በዓል ላይ ለመታደም ከዛው ከትግራይ ክልል እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከግማሽ ሚሊዮን / 500 ሺህ ሕዝብ በላይ ወደ ስፍራው መጓዙን ገልጸዋል።
@tikvahethiopia

ፎቶ ፦ የወራቤ - ቦዠባር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት እየተሰራ ይገኛል።
ለዚህ መንገድ ግንባታ 2.77 ቢሊዮን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን 41.3 ኪ.ሜ ርዝመት አለው።
የተቀመጠው የሙሉ በሙሉ ግንባታ የማጠናቀቀያ ጊዜ ሁለት ዓመት ነው ተብሏል።
የአስፓልት መንገዱን የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ እየሰራ ያለው የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ በተያዘለት በጀት ፣ ጊዜ እና የጥራት ደረጃ መንገዱን ሰርቶ ለማስረከብ በቂ የሰው ኃይል፣ ማሽን ፣ ማቴሪያል መድቦ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አሳውቋል።
የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ምን አለ ?
- በተያዘው በጀት ዓመት ቢያንስ 50 ከመቶ በላይ የሚሆነውን ስራ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ነው።
-የተለያዩ የአፈር ስራዎችን የሚሰሩ 03 ክሩዎች እና የስትራክቸር ስራዎችን የሚሰሩ 02 ክሩዎች ተዋቅረው ወደስራ ገብተዋል።
- የአስፓልት ጠጠር የማምረት ስራ ለንኡስ ተቋራጭ ተሰጥቶ የፓድ ተከላ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የሞቢላይዜሽን ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡
- ለሙሊት የሚሆን ማቴሪያል የማምረት ስራው በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
ይህ የወራቤ -ቦዠበር መንገድ የረጅም ጊዜ ጥያቄ ሲሆን በዚህ መንገድ ሳቢያ የአካባቢው ህዝብ ክፉኛ ችግር ላይ እንደወደቀና መንገዱ እንዲሰራለት በተደጋጋሚ ድምፁን ሲያሰማ እንደነበር ይታወሳል።
Photo Credit - የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት

" ለጅቡቲ ጉምሩክ ደብዳቤ ፅፈናል " - የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን
በጅቡቲ ጉምሩክ የወደብ ጭነት መዘግየት ችግር የተፈጠረ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሳውቋል።
የጂቡቲ ጉምሩክ " ከ20 ሺህ ዶላር በታች የክፍያ ደረሰኝ የያዙ ጭነቶች ወደ ኢትዮጵያ #እንዳያልፉ " በሚል መመሪያ እቃዎች እንዳይንቀሳቀሱ እንዳገደ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዘርይሁን አሰፋ በሰጡት ቃል ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ለጅቡቲ ጉምሩክ ደብዳቤ መፃፉን ገልጸዋል።
" ኢትዮጵያ እቃዎችን በጂቡቲ ወደብ በኩል የምታዘዋውር መሆኑን ተከትሎ መሰል ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ " ይጠበቃል ያሉት አቶ ዘርይሁን " እቃ አስመጭዎች ለደረሰባቸው ችግር ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ስራዎች እየተሰሩ ናቸው " ብለዋል።
" በጂቡቲ 2 ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች አሉን " ያሉት ዳይሬክተሩ ችግሩ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሻ አስረድተዋል፡፡
ችግሩ ከ3 ሳምንታት በላይ ያስቆጠረ መሆኑን ተከትሎ ጭነቶች ወደብ ላይ በሚቆዩበት ወቅት ከሚከፈለው ገንዘብ መጠን ጋር ተያይዞ ጉዳቱ የከፋ መሆኑን አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የአሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን ያሳውቃል።

#Teklehaimanot
የኩላሊት ፣ የፊኛ፣የፕሮስቴትና የሽንት ቱቦ ህክምናዎች ፦
ልምድ ያካበቱ የኩላሊት፣ የፊኛ፣የፕሮስቴትና የሽንት ቱቦ ህክምና ሰብስፔሻሊስት ሃኪሞቻችን ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ።
• የ24 ሰዓት የኩላሊት እጥበት
• የኩላሊት እጥበት ለሚደርጉ ታካሚዎች ክትትል ማድረግ፣
• ለኩላሊት እጥበት የደምስር ቱቦ ማስገባት እና ቋሚ የደምስር መፍጠር
• ከኩላሊት ንቅለ ተከላ በኋላ ክትትል ማድረግ
• ሆድ ሳይከፈት በቪድዮ የታገዘ የጠጠር፣ ፕሮስቴትና የፊኛ ዕጢ ቀዶ ህክምና
• የኩላሊትና ቴስቲኩላር ካንሰር ቀዶ ህክምና
• የቫሪኮሲል፣ የወንድ ብልት መሰበር ፣የፔሮይንስ ህመም፣ የፕሪያፒዝም፣የወንዶች ዘር ፍሬ ህመሞች እና የሽንት ቧንቧ ጥበት ህክምናዎች።
ስልክ ፦8175 / 0940 33 33 33
Facebook: https://www.facebook.com/teklehaimanothospital
Instagram: https://www.instagram.com/teklehaimanotgeneral
Telegram: https://t.iss.one/teklehaimanothospital1
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/teklehaimanot-general-hospital/
Twitter: https://twitter.com/TeklehaimanotG4
Website: www.teklehaimanothospital.com
E-mail: [email protected]

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SUNChips #SunnyMoments #ሰንቺፕስ #ሰኒሞመንት #መክሰስTime
አንድ ላይ እስከሆንን ድረስ የእረፍት ጊዜያችን እና የኛ #ሰኒሞመንትስ ☀️ በሰን ቺፕስ እንደፈካ ነው!
የምንጋራው ሰን ቺፕስ ለምንጋራው ጊዜያት! 😋
Together where we are, our #SunnyMoments ☀️and snack time are paired with Sun Chips, in the perfect size so that we can all enjoy shared memories. 😋
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

#makeway
በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የጤና ወጪ ውስጥ
ለሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የሚመደበው ገንዘብ ከጤና አገልግሎት ፍላጎት አንፃር እጅግ አነስተኛ መሆኑንና ከአጠቃላይ የጤና ወጪ ለሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የሚመደበው 12 በመቶ ብቻ መሆኑን የስነ ተዋልዶ ጤና ማኅበራት ጥምረት (CORHA) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የጥምረቱ የጤና እንክብካቤ ፋይናንሲንግ ቴክኒክ አማካሪ የሆኑት አቶ ሚደቅሳ አዱኛ ጤና ሚኒስቴር በየሁለት ዓመቱ የጤና ወጪ ጥናት እንደሚያወጣ አንስተዋል።
በፈረንጆቹ 2016 እስከ 2019 ያለውን ጊዜ በማካተት በተጠናው ጥናት መሰረትም ከሀገሪቱ አጠቃላይ የጤና ወጪ 12 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዘርፉ ካለበት ችግር አንፃር እጅግ አናሳ መሆኑን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የሥነ-ተዋልዶ ጤና ወጪ ከምስራቅ አፍሪካ አቻዎቿ ጋር፤ በተለይም ከብሩንዲና ኬንያ ጋር ሲነጻጸር አናሳ መሆኑን አቶ አዱኛ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልስ አንስተው፥ ሀገሪቱ በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ የምታፈሰው ኢንቨስትመንት የዘርፉን ችግር ያገናዘበ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ቪኤስኦ ኢትዮጵያ፣ ሪድም ዘጀነሬሽን እና የወጣት ሴቶች ክርስቲያን ማኅበር በጋራ " ሜክ ዌይ " የተባለ ፕሮግራም በመፍጠር በጋራ እየሰሩ ሲሆን በዓለም ለ32ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚታሰበውን ፀረ- ጾታዊ ጥቃት ቀንን አስመልክቶም በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ የሚመክር መድረክ ከሰመኑ አሰናድተው ነበር።
በመድረኩ ላይ፤ በሀገሪቱ የሥነ-ተዋልዶ ጤናን ለመጠበቅ ከሚመድበው ገንዘብ ውስጥ #50_በመቶ የሚሆነው ሀብት ለአስተዳዳር ወጪ የሚወጣ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ተደራሽነት የሚገድብ እንደሆነ ተነስቷል።
የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት፥ 23.9 በመቶው የሚሆነው ወጪ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሸፈን ሲሆን 62.7 በመቶው ደግሞ መንግስት ይሸፍናል። ተጠቃሚዎች ደግሞ 12.3 በመቶ የሚሆነውን ያክል ድርሻ እንደሚያወጡና ቀሪው በሌሎች እንደሚሸፈን በጥናቱ ተመላክቷል።
መንግስት የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ዜጎች በነፃ እንዲያገኙ ቢያስቀምጥም ተጠቃሚዎች ለሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት 12.3 በመቶ የሚሆነውን ያክል ድርሻ እያወጡ በመሆኑ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት በሚፈልጉ ግለሰቦች ላይ ጫና አሳድሯል ተብሏል።
በምክክሩ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ መሰራት እንደሚኖርበት ሲገለፅ፥ የጾታዊ ለጥቃት ተጋላጮች ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም የፆታዊ ጥቃትን መከላከል የሚያስችል የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ ማካሄድ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
'' መቼም የትም በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል '' በሚል መሪ ቃል የ16 ቀናት የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ እየተደረገ መሆኑና በሚቀጥሉት ቀናትም ዘመቻው እንደሚቀጥል ተገልጿል።

" የኤችአይቪ/ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል " - አቶ ፍቃዱ ያደታ
ወጣቶችን ጨምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ተብለው በተለዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ እየታየ ያለው የኤችአይቪ/ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነግሯል።
የኤችአይቪ/ኤድስ ሥርጭት ፦
* በቀን ሠራተኞች፣
* በሴተኛ አዳሪዎች፣
* በረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣
* በአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች ላይ ያለው የሥርጭት ምጣኔ በጣም ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።
በጤና ሚኒስቴር የኤችአይቪ/ኤድስና ቫይራል ሄፒታይተስ የመከላከልና የመቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፈቃዱ ያደታ ምን አሉ ?
- የኤችአይቪ ሥርጭት በኢትዮጵያ ከአንድ ፐርሰንት በታች ዝቅ ቢልም የሥርጭት ምጣኔው ከክልል ወደ ክልል የተለያየ ነው።
- ከፍተኛ ሥርጭት ካለባቸው ክልሎች መካከል ፦
• ጋምቤላ ክልል የመጀመሪያው ሆኖ 3.69 በመቶ፣
• አዲስ አበባ ከተማ 3.17 በመቶ፣
• ሐረሪ ክልልና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 3 በመቶ የሥርጭት ምጣኔ አላቸው።
• በሶማሌ ክልል ዝቅተኛ የቫይረስ ሥርጭት ነው ያለው።
- በግጭት ምክንያት #የሚፈናቀሉ ማኅበረሰቦችና የተለያዩ የማኅበራዊና የኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የኤችአይቪ/ኤድስ ዘርፈ ብዙ ማስተግበሪያ ዳይሬክተር ሲስተር ፈለቀች አንዳርጌ ምን አሉ ?
✦ በአገር ደረጃ የሥጋት ቀጣና ተብለው የተለዩ አካባቢዎች አሉ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት 121 ወረዳዎች 48 ወረዳዎች በትኩረት የሚሠራባቸው ናቸው።
✦ ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሉ እነዚህ። ፦
° አፍላ ወጣቶች፣
° የትዳር አጋራቸውን የፈቱና የሞቱባቸው፣
° ሴተኛ አዳሪዎች ሲሆነ ለእነዚህ አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል።
✦ ከቦታ ወደ ቦታ የበሽታው ሥርጭት የተለያየ ነው። በአዲስ አበባ የሥርጭት ምጣኔው 3.4 በመቶ ነው።
✦ የመዘናጋት ሁኔታዎች በሰፊው እየተስተዋሉ ነው። ሞት በመቀነሱ ምክንያት " ኤችአይቪ/ኤድስ የለም " የሚሉ ሰዎች ተበራክተዋል።
✦ ከ20 እስከ 25 ዓመት ዕድሜ ክልል ያሉ ወጣቶች " ሞት የለም " በማለት የመዘናጋት ሁኔታዎች እያሳዩ ነው።
✦ በአጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ የሥርጭት ምጣኔ 0.91 በመቶ ነው። በዚህ ሥሌት ከ610‚350 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው እንደሚገኝና ከእነዚህ ውስጥም 8‚257 ያህሉ አዲስ የተያዙ፣ እንዲሁም ከ11 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በአገር ደረጃ ይሞታሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ መሆኑን ያሳውቃል።

የትም የትም ሳይሄዱ ክፍያዎትን
በሲቢኢ ብር ባሉበት ይክፈሉ!
ከ260 በላይ ተቋማት ጋር ትስስር ፈጥረናል!
***********
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለማውረድ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

#RUSSIA
ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች።
የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል።
ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች) ° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ ማካሄዳቸው ተነግሯል።
ፖሊስ በርካታ የተመሳሳይ ጾታ ክለቦችን ውስጥ በመግባት የተወሰኑትን ታዳሚዎች አጠር ላለ ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል።
በተጨማሪም የአንዳንዶች ፖስፖርት ተወስዶ ፎቶ እንዲነሳ ተደርጓል ተብሏል።
ፖሊስ የምሽት ክበቦች ላይ ዘመቻ ያካሄድኩት " አደንዛዥ እፅ ለመፈለግ ነው " ማለቱ ተነግሯል።
ሩስያ ፦
- ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴ ጽንፈኛ ነው በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች አግዷል።
- እግድ የተላለፈው የፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው።
- በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም።
- በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።
- እኤአ 2013 ላይ ከተለመደው ውጪ ያለ ጾታዊ ግንኙነት ላይ የሚደረግ ፕሮፖጋንዳን የሚከለክል ሕግ አውጥታለች።
- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን የሚያመለክቱ ይዘቶች ከመጽሓፍት፣ ከፊልሞች፣ ከማስታወቂያዎች እና ከቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንዲሰረዙ ተደርገዋል።
- በቅርቡ አንድ የሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያ የፕሮፓጋንዳውን ሕግ ጥሷል ተብሎ እንዳይከሰስ በደቡብ ኮሪያ የፖፕ ሙዚቃ ቪዲዮ ላይ የነበረውን የተመሳሳይ ፆታ መግለጫ የሆነውን ቀለም እንዲለውጥ መገደዱን ገልጿል።
መረጃው ከቢቢሲ / አስቶሮዥኖ ኖቮስቲ / ፣ ሮይተርስ፣ አልጀዚራ የተገኘ ነው።