TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የሩስያ ፕሬዜዳንት ፑቲን ቻይና ገብተዋል። ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና የስራ ጉብኝት ለማድረግ እንዲሁም " የቤልት ኤንድ ሮድ " ዓለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ቻይና ገብተዋል። በሁለት ቀን የቻይና ቆይታቸው ወቅት ከሀገሪቱ ፕሬዜዳንት እና ከሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል። ፑቲን በተለይ ሀገራቸው ከ #ዩክሬን ጋር ወደ ጦርነት ከገባች በኃላ እምብዛም ከሀገር ሲወጡ እንዳልነበር…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ ፑቲን እና #የኒውክሌር_ማዘዣ ብሪፍኬዝ / ባርሳቸው ወይም “ ቼጌት ” በካሜራ እይታ ውስጥ መግባቱ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቦ እየተቀባበሉት ነው።

ይህ መሰሉ ቪድዮ ሲሰራጭ ብዙም ያልተለመደ ነው።

የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቀናት በፊት ወደ ቻይና ማቅናታቸው ይታወሳል።

ትላንት ረቡዕ ፑቲን #ቤጂንግ ውስጥ በደህንነቶች ተከበው ወደ ስብሰባ ሲያመሩ በካሜራ እይታ ውስጥ የገቡ ሲሆን አብረዋቸው (ከኃላ) እያንዳንዳቸው ብሪፍኬዝ / ቦርሳ የያዙ ሁለት የሩሲያ የባህር ሃይል መኮንኖች ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች ታይተዋል።

እነዚህ መኮንኖች የያዙት የኒውክሌር ጥቃትን ለማዘዝ የሚያገለግለውን የኒውክሌር ብሪፍኬዝ/ቦርሳ ወይም ቼጌት የሚባለውን ነው ተብሏል። ይህ በአስፈላጊ ሰዓት የኒውክሌር ጥቃት የሚታዘዝበት ቦርሳ አስፈላጊውን ኮዶች የያዘ ነው።

ከላይ በተያያዘው ቪድዮ ካሜራው አንደኛውን ቦርሳ አቅርቦ ሲያሳይ ተስተውሏል።

የሩስያን የኒውክሌር ብሪፍኬዝ በተለምዶ የሚያዘው በባህር ኃይል መኮንን ነው። 

ይህ ብሪፍኬዝ / ቦርሳ በማንኛውም ጊዜ ከፕሬዚዳንቱ አጠገብ የማይለይ ቢሆንም ብዙም በካሜራ እይታ ውስጥ አይገባም / አይቀረጽም።

አንዳንዶች ይህ የማዘዣ ብሪፍኬዝ #በቪድዮ_ተቀርፆ እንዲሰራጭ የተደረገው ሆን ተብሎ ለባላንጣዎቻቸው መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ብለውታል።

ከፑቲን በተጨማሪ ፤ የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትርም በተመሳሳይ የኒውክሌር ብሪፍኬዝ / ቦርሳ አላቸው።

ሌሎች " ኒውክሌር " የታጠቁ ሀገራት በተመሳሳይ የማዘዣ ቦርሳ ከመሪዎቹ አጠገብ ባይጠፋም በቪድዮ እይታው ውስጥ እንዲገባ አይደረግም።

ለአብነት የአሜሪካው ፕሬዜዳንት " ኒውክሌር ፉትቦል " የሚባል ተንቀሳቃሽ የኒውክሌር ማዘዣ ያላቸው ሲሆን ፕሬዜዳንቱ ዋይትሀውስ በማኖርቡበት ጊዜ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጥቃት እንዲፈፀም የሚያዙበት ነው።

Video Credit - Reuters

Via @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia
#ሾኔ

ከ500 በላይ የሾኔ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ ተሰማ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ሐዲያ ዞን ሾኔ ከተማ ፣ ላለፉት 3 ወራት የተቋረጠባቸው ደመወዝ እንዲከፈላቸው ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የገለጹ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች በሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ ቪኦኤ አማርኛ ዘግቧል።

በጊዜያዊ ውል የተቀጠሩትን ጨምሮ ከ500 በላይ የሆስፒታሉ ጠቅላላ ሠራተኞች እንደተስማሙበት በጠቀሱት በዚሁ የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት ከ600 ሺህ በላይ ለሚሆን ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሉ ሥራ ከአቆመ 7 ቀን እንዳለፈው ሠራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

አንድ ስማቸውን ለደህንነታቸው ሲባል እንዲገለፅ ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ሰራተኛ ፤ " የባጀት እጥረት እየተባለ፣ ከባጀቱም ከፍቶ አሁን ደግሞ የነሃሴ ፣ መስከረም ሙሉ ወር ደመወዝ አልተከፈለም። አምናም ደሞዝ ሳይከፈል ቀርቶ ብዙ ባለሞያዎች ስራ ለቀው ሲሄዱ ነበር። እኛ ያለነውም ደመወዝ ሳይከፈለን ስራ መስራት አንችልም ብለን ነው ለቀን የወጣነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለረሃብ እና ለአደጋ ተጋልጠናል፤ ደመወዝ ሳይከፈል እንዴት እንሰራለን ? እኛ እየተራብን ምንድነው የምንሰራው መጀመሪያ እኛ እራሱ መታከም አለብን ፣ እኛ መዳን አለብን ብለን ነው ያቆምነው፤ ከሁለት ዓመት በፊትም ያልተከፈለ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አለ የሁለት ወር ክፍያ የት እንደሄደም አይታወቅም። ማንም ባለሙያውን እንደ ባለሙያ እየቆጠረው አይደለም በሚል ነው በቁጣ ለቀን የወጣው " ሲሉ አክለዋል።

" በከተማው ሌላ ሆስፒታል የሌለ ሲሆን ያሉት የተወሰኑ ጤና ጣቢያዎች ነበሩ እነሱም ከተዘጉ ቆይተዋል። ለምን ተዘጋ ? የሚል አካልም የለም " ብለዋል።

የሆስፒታሉ የተኝቶ ታካሚዎች ክፍል አስተባባሪ ዶ/ር ፋብዩ አየለ ፤ " ከ7 ቀን በፊት የድንገተኛ ክፍል ብቻ የተወሰኑ ሰዎች ተመርጠው ይሰሩ ነበር ፤ ይከፈላችኃል ተባለ ዛሬ ነገ ሲባል 72 ሰዓት ሆነ የሚከፍል የለም ከዛ በኃላ ነው ሁሉንም ክፍሎች ለመዝጋት የወሰኑት። አብዛኛው ሰራተኛ ከሌላ ቦታ የመጣ አለ፤ የቤት ኪራይ፣ የሚበላ የሚጠጣ ያጣ አለ የሚከፍለውን ያጣው አብዛኛው ሰራተኛ ወደ ቤት ሄዷል ቤተሰቡ ጋር እዚህ ተወላጅ የሆነውም ቤት ኪራይ፣ መብላት መጠጣት አለ 3 ወር ሙሉ አልተከፈለንም። አሁንም እየጠየቅን ነው ልንከፍል አንችልም የተሰጠን ብር ጎሏል አይነት ነገር ነው የሚያወሩት " ብለዋል።

ዶ/ር ፋብዩ ፤ ከዚህ ቀደምም 2012 የሁለት ወር የትርፍ ሰዓት ክፍያ መበላቱን፣ በ2015 የጥቅምት ወር በተመሳሳይ እንዳልተከፈለ አስታውሰው አሁን በጣም ሲከፋ ሰራተኛው ስራ ማቆሙን ጠቁመዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ተድላ አካሉ፤ ሆስፒታሉ ሥራ ማቆሙን አረጋግጠዋል።

በተለይ የድንገተኛ ክፍልና ማዋለጃ ክፍል አገልግሎት ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ከ3 ቀን በፊት አንስቶ እሱም እንደተቋረጠ ገልጸዋል።

የአካባቢው ነዋሪ ሆስፒታሉ አገልግሎት እየሰጠ ባለመሆኑ ወደሌሎች አካባቢዎች ለመሄድ መገደዱን ጠቁመዋል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ተሰማ ሆስፒታሉ ሥራ ማቆሙን ባይክዱም መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።

የሐዲያ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ኦልባሞ ከሬድዮ ጣቢያው ስልክ ሲደወልላቸው #ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ጠቅሰው " እዚያው ሆስፒታሉን ጠይቁ " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ ከ600 ሺህ በላይ ህዝብ ተደራሽ ያደርጋል፣ በቀንም እስከ 200 ታካሚ ያስተናግዳል የተባለለት ሆስፒታል ስራ በመቆሙ ህዝቡ እንግልት እየደረሰበት ይገኛል።

መረጃው የቪኦኤ ሬድዮ (ዮናታን ዘብዲዮስ) ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል።

እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

- በ2014 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ፦

• ወደ መንግሥት ተቋማት ተመድበው የሬሜዲያል ትምህርት ከተከታተሉት 105,00 ተማሪዎች 63,033 ተማሪዎች አልፈዋል።

• በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው  ከተፈተኑት ውስጥ 44,500 ተማሪዎች 27,587 ተማሪዎች አልፈዋል።

በአጠቃላይ ወደ 145,000 ገደማ ተማሪዎች ሬሜዲያል ገብተው በዛው በተቋማቸው ከ30% እንዲሁም ከማዕከል 70% ተፈትነው ከ50% እና በላይ አምጥተው ያለፉት 90,620 ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች ዘንድሮ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ያለፉት ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች 27,267 ገደማ ናቸው። በቀጥታ ፌሽማን / አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በአጠቃላይ በ2014 ዓ/ም ተፈትነው ሬሜዲያል ያለፉና በ2015 ዓ/ም 50 በመቶ አምትጥተው በቀጥታ ያለፉትን ጨምሮ 117,887 ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። (90,620 ከሬሜዲያል፤ 27,267 ከ2015 ዓ/ም አላፊዎች)

- ዘንድሮ በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡት 191, 509 ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች ናቸው፤ እነዚህ በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል።

#MoE #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#SUNChips

መምጣቱ ላይቀር የሚያስጠብቀን የእረፍት ቀን ደርሷል! ዘና ፈታ እንበል! #መክሰስTime ደርሷል- ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
Looking forward to snacking on the weekend with SUNChips. #SUNChips 😋 #SunnyMoments. ☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia 
#ትኩረት

" #የጨረር_ሕክምና ባለመኖሩ ከ700 በላይ ሕሙማን አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም " - ዓይደር ሆስፒታል

የዓይደር ሆስፒታል የካንሰር ሕክምና ማዕከል ኃላፊ ክብሮም ህሉፍ ( ዶ/ር ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ የጨረር ሕክምና ባለመኖሩ ከ700 በላይ ሕሙማን አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም።

" ባለፈው ሦስትና አራት ወራት ውስጥ ወደ 800 የሚሆኑ ሪፈር የተፃፈላቸው ፔሸንቶች አሉ " ያሉት ኃላፊው፣ " በመቐለ ዩኒቨርስቲ የተጀመረው የጨረር ሕክምና አግልግሎት መስጫ ህንፃ ግንባታ የፊኒሽንግ ሥራው ስላልተጠናቀቀ ታካሚዎቻችንን ወደ ጥቁር አንበሳ፣ ጅማና ሀረሚያ ሪፈር እያልናቸው ነው " ብለዋል።

አክለውም፣ " ከጦርነት ጋር ተያይዞ፣ የትራንስፖርት መወደድ፣ ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ ሪፈር ከተባሉት ታካሚዎች መካከል እዚያ የሚደርሱት 10 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። 90 በመቶዎቹ ሕክምና እያስፈለጋቸው አይሄዱም። ምናልባት 80 ወይም 100 የሚሆኑ ታካሚዎች ናቸው የሚሄዱት፣ ቀሪዎቹ ወደ 700 ታካሚዎች ግን እየተጠባበቁ ያሉት ምናልባት እኛ ህንጻውን ከጨረስነው ነው፣ ካልሆነ ግን ሕመሙ ምን እንደሚያደርጋቸው እየጠበቁ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ክብሮም (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ ፣ " የጨረር ሕክምና ኢትዮጵያ ውስጥ ስድስት ነበር ለመትከል የታሰበው የዛሬ ስድስት፣ ሰባት ዓመታት። ጥቁር አንበሳ፣ ጅማና ሀረማያ ጀምረዋል። የሀዋሳው ተተክሎ አልቋል፣ የጎንደሩም እንደዚሁ ተቃርቧል" ሲሉ ተናግረው፣ " የእኛ የመቐሌው ግን በዚህ በነበረው ጦርነት ምክንያት፣ ከኮሮና ጋር ተያይዞ፣ መቐሌ ዩኒቨርሲቲ በገጠመው የበጀት እጥረት ሕንፃው ማለቅ አልቻለም " ብለዋል።

የጨረር ሕክምና አገልግሎት መስጫ ሕንፃ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም፣ የሕንፃውን የፊንሺንግ ሥራዎች በማጠናቀቅ፣ ተገዝቶ የተቀመጠውን ማሽን በመገጣጠም አግልግሎቱን ለመጀመር ቢያንስ ከ60 እስከ 80 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚጠይቅ ኮንትራክተሮች ተናግረዋል ብለዋል።

አክለውም፣ "በዶ/ር ሊያ የተመራ ልዑክ መቀሌ መጥቶ ነበር ከዚህ በፊት፣ በመጡበት ጊዜ ሕንፃውን ለመጨረስ ቃል ገብተው ነበር የሄዱት" ሲሉ አስታውሰው፣ " የፊኒሽንግ ሥራዎችን ለመጨረስ ብር ሊያግዙን ነበር አሁን ግን ሌሎች ቅድሚያ የሚያስፈልጋቸው የጤና ተቋማት አሉ በሚል እነርሱም እንደማይችሉ ነግረውናል። ትልቁ ችግራችን የጨረር ሕክምና ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ከ100 በላይ የካንሰር ሕሙማን መሞታቸውን ሆስፒታሉ ከአምስት ወራት በፊት ገልፆ ነበር። አሁን የመድኃኒት እጥረቱ እንደተቀረፈና እንዳልተቀረፈ እንዲያብራሩ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ "አሁን አዲስ አበባ ያሉት መድኃኒቶች እየመጡልን ነው። ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በተወሰነ መልኩ ከእስከዛሬው አንፃር መሻሻሎች አሉ። ብለዋል።

"አሁንም የተወሰኑ የመድኃኒት እጥረቶች አሉ ያሉት ክብሮም (ዶ/ር) ፣ ምን ያህል ተመላላሽ የካንሰር ታካሚዎች እንዳሉ ሲያስረዱም፣ እስክ 1,500 ተመላላሽ የካንሰር ሕሙማን እንዳሉም ገልጸው፣ "አሁን ትልቁ ያለው ችግራችን የጨረር ሕክምና ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/TikvahEthiopia-10-19

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ማስተካከል ይችላሉ ብሏል።

ሚኒስቴሩ ፤ ያልፉ ተማሪዎች ምርጫቸውን ማስተካከል የሚችሉት በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አስገንዝቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቀው ምርጫቸው ውስጥ በማካተት መመደብ እንደሚችሉም የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። #MoE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል። እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - በ2014 ዓ/ም…
#MoE

" አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል "  - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፤ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በአግባቡ እንደሚሰራበት አመልክተዋል።

" በምንም አይነትና መስፈርት አግባብ የሌለውና አድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።

" እያንዳንዱ ተማሪ በጠየቀው በችሎታው ፣ በሚገባው ቦታ እንዲመደብ እናደርጋል " ያሉት ሚኒስትሩ " አንድና ብቸኛው ከዛ የምንወጣበት አስቸኳይ የሆነና ቅርብ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የህክምና ጉዳይ ሲኖር ነው " ብለዋል።

" የህክምና ኬዞችንም ስንመለከት ከዶክተር ወረቀት ማምጣት ብቻ ሳይሆን በቦርድ ደረጃ ተነጋግረውበት ያ የህክምና ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመማር የማያስችል ነው፤ ለህይወቱ/ቷ አስቸጋሪ ነገር ያመጣል ከተባለ ብቻና ብቻ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፤ " ለአንድ የመንግሥት ባለስልጣን ፣ አንድ የምክር ቤት አባል፣ አንድ ዝም ብሎ ሃብታም ነኝ ብሎ ለሚያስብ ሰው ከሚገባው ውጭ ለልጁ የሚሰጥ ምንም ነገር የለም " ብለዋል።

ከምደባ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጥያቄዎች እየተጠየቁ መሆኑን ያልደበቁት ፕ/ር ብርሃኑ " ስልኮች ይደወላሉ ነገር ግን የምንሰጠው መልስ አንድ ነው ፤ ' ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው። በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው ከዛ ውጭ ባለ ሌላ መስፈርት ማንንም እድል አንሰጥም ' የሚል ነው " ብለዋል።

" ከዚህ ውጭ የተሰራና የሚሰራ ስራ ካለ አሳዩን፤ ንገሩን እናስተካክላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ለምደባ በሚል ጉዳይ እሳቸውም ጋር የሚመጡ እንዳሉ ገልጸው " ለሁሉም የምለው አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል ፤ ትክክለኛ ጥያቄ አለን ካላችሁ በትክክለኛው ሂደት እለፉ ከዛ ውጭ ግን የሚመጣ የአቋራጭ መንገድ የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

#MoE #Tikvah_Ethiopia

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በወገን ሴንድ ገንዘብ ወደ አገር ቤት በነፃ ይላኩ!

ቪዛ ወይም ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው በወገን ሴንድ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store በማውረድ ይጠቀሙ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.wegensend.wegensend&hl=en&gl=US

የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.iss.one/BoAEth
#Oceanስክሪፕቶ

ድርጅታችን በከፍተኛ  ጥራት የሚያመርተውን "Ocean" ስክሪፕቶ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚያከፋፍሉለት ውስን ወኪል ነጋዴዎች አወዳድሮ በመምረጥ መመደብ ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራቹ ፍላጎትና  አቅም ያላችሁ አከፉፉዮች  ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ለወኪል አከፋፋይ ያዘጋጀነውን የልዩ ሽያጭ ዋጋ ስምምነት ውል በማድረግ የድርጅታችን ወኪል ይሁኑ::

+251901835555
+251901832222
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2014 ዓ.ም እና 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ውጤት ያመጡ እና በፖሊስ የሙያ ዘርፍ ሀገራቸውን ለማገልገል #የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ተቋሙ ለ4  አመታት በ " ፖሊስ ሳይንስ ዲግሪ " አስተምሮ በመኮንንነት (ረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ) በማስመረቅ በተለያዩ የፌደራል ፖሊስ የስራ ክፍሎች አስመድቦ ለማሰራት እንደሚፈልግ ነው የገለፀው።

በተጨማሪ በ "ፎረንሲክ ሳይንስ ዲግሪ" አስተምሮ በመኮንንነት (ረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ) በማስመረቅ በፎረሲክ ምርመራ የላብራቶሪ ሙያተኝነት (ኤክስፐርት) በማስመደብ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በተቋሙ በ  " ፖሊስ ሳይንስ ዲግሪ " ለመማር የሚያስፈልጉ የመመልመያ መስፈርቶች ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ ሲሆን ከነሱም ውስጥ ፦

- አመልካቾች ከማንኛውም ወንጀል ነፃ ስለ መሆኑ ከሚኖርበት ወረዳ ፖሊስ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

- ለፖሊስ አካል ብቃት ስልጠና ብቁ የሆነ አካላዊ አቋምና አዕምሮ ጤንነት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

- በ2014 ዓ/ም እና 2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር መቁረጫ ውጤት ያላቸው  የትምህርት ማስረጃቸውንም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

- የ #ሪሚዳል_ትምህርት ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ከሆነም ማስረጃ ማቅረብ አባቸው።

- አመልካቾች እድሜያቸው ከ18 እስከ 28 ዓመት መሆን አለበት።

- ቁመት ለወንድ 1.65 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 1.55 እና ከዚያ በላይ፣
ሲሆን የተስተካከለ የሰውነት ክብደት 18.5-24.9 kg/m) ያለቸው ሊሆኑ ይገባል።

- ከተመረቁ በኋላ 7/ሰባት/ አመት በተማረበት የፖሊስ ሙያ በየትኛውም የአገሪቱ ክልልና የፖሊስ የስራ መደቦች ላይ ተመድቦ ለመስራት ፍቃደኛ መሆን አለበት።

- ሴት አመለካቾች ከእርግዝና ነፃ መሆን አለባቸው።

- ሁሉም አመልካቾች ከዚህ በፊት የፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊት ስልጠና ያልወሰዱ መሆን ያለባቸው ሊሆኑ ይገባል።

ለ " ፎረንሲክ ሳይንስ ዲግሪ " ከላይ ያሉት አብዛኛው መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው ፦
- ዜግነት #ኢትዮጵያዊ
- የ12ኛ ክፍል #በተፈጥሮ_ሳይንስ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በ2014 ዓ/ም እና በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መቁረጫ ውጤት ያላቸው
- በተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዳል ትምህርት ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል።

በሁለቱም የዲግሪ ትምህርት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን የሚቀላቀሉት በራሱ በተቋሙ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ሲችሉ ብቻ ነው።

የት እና እስከመቼ መመዝገብ ይቻላል ?

ማመልከት የሚቻለው እስከ ጥቅምት 22/2016 ዓ/ም ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ነው።

ተማሪዎች በአካባቢያቸው በሚገኝ በሁሉም የክልል እና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ።

ለመዝገባው የትምህርት ማስረጃቸውን የ8ኛ ፣ የ10ኛና 12ኛ ክፍል ካርድ እና ትራንስክርፕት ኦርጅናል ከማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ አለባቸው።

#ደመወዝ / #ክፍያን በተመለከተ

ዕጩ መኮንኖች በትምህርት ላይ በሚቆዩበት ጊዜያት ከ3 ወር የሙከራ (recruit) ጊዜ ቆይታ በኋላ እስከሚመረቁ ድረስ የኪስ ገንዘብ/ደመወዝ ታስቦ ይከፈላቸዋል ተብሏል።

ስልክ ካስፈለጋችሁ ፡ 0116735564

(ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ በምስሉ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
ዛሬ " ገርቢ " ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በምስራቅ ሸዋ ዞን ፤ በአዳሚ ቱሉ ወረዳ ውስጥ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው ከአዳሚ ቱሉ ወረዳ ወደ #ባቱ ከተማ ሲጓዝ የነበረ ዳማስ ተሽከርካሪ እና በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረ ቶዮታ ቪ ኤይት (v8) መኪና  " ገርቢ " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በመጋጨታቸው ነው።

በአደጋው 4 ሰዎች ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ 3 ሰዎች የህክምና ተቋም ከደረሱ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል። በአጠቃላይ በአደጋው 7 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ሌሎች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኤፍ ቢ ሲ የባቱ ኮሚኒኬሽንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

(የአደጋውን ሁኔታ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል የላከልን ሣሚ ተስፋዬ የሚባል የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው)

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የኢሰመኮ 3ኛ ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፎች እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር ላይ ተሳተፉ !

መኖሪያ ቤት/ቦታ ማለት ለአንድ ሰው ወይም ለአንድ ቤተሰብ ምን ማለት ነው ?

ሕይወት፣ ትርጉም ያለው ሕይወት፣ ምንድን ነው ? የአንድ ኢትዮጵያዊት ሴት፣ ወይም የአካል ጉዳተኛ ወይም የተፈናቃይ ወይም የአረጋዊ ሕይወት ምን ይመስላል ?

በሕይወት እና በመኖሪያ ቤት ዙርያ እነዚህን እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለኪነጥበብ አፍቃሪዎች፣ ለኪነጥበብ ሙያ ተማሪዎች፣ ባለሞያዎች እና አማተሮች እንዲሁም ለመገናኛ ብዙኃን አባላት እና ሌሎችም በኪነጥበብ እና በሰብአዊ መብቶች መካከል ያለውን ትስስር ማሳየት ለሚፈልጉ ሁሉ፣ በኢሰመኮ አዘጋጅነት በሚካሄደው የ3ኛው ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር የቀረቡ ናቸው።

ኑ፣ ተሳተፉ፣ አብረን እንድናሰላስል የሚረዱ የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ሥራዎቻችሁን ለዕይታ አቅርቡ!
በውድድሩ ለመሳተፍ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዝርዝሩን በዚህ ይመልከቱ - https://bit.ly/46sReAw