TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በተለያዩ ጊዜ በምናዘጋጃቸው የማህበራዊ ሚዲያ ውድድሮች በመመሳተፍ ይሸለሙ!

የኢትዮ ቴሌኮም ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ቤተሰብ በመሆን፤ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ያግኙ፤ ከአጭበርባሪዎች ራስዎን ይጠብቁ፤ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜ በምናዘጋጃቸው ውድድሮች በመሳተፍ ይሸለሙ!

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን
ቴሌግራም፡ https://t.iss.one/ethio_telecom
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/ethiotelecom
ትዊተር፡ https://twitter.com/ethiotelecom
ኢንስታግራም ፡https://www.instagram.com/ethiotelecom/
ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/ethio-telecom

ኢትዮ ቴሌኮም
ሰዎች ራሳቸውን ለምን ያጠፋሉ ?

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

ራስን ማጥፋት ማለት ፦ አንድ ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ህይወቱን በራሱ ፍላጎት በተለያዩ ዘዴዎች ተጠቅሞ ራስን የመግደል ድርጊት ነው።

በዓለማችን ከ800,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ራሳቸውን በየአመቱ ያጠፋሉ (World Health Organization) 79% ራስን ማጥፋት የሚፈፀመው ደግሞ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ነው።

ከ15-19 የ እድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ህይወታቸውን ከሚያጡበት ምክንያቶች መካከል ራስን ማጥፋት በ ሶስተኛ ደረጃ ይቀመጣል።

ራሳቸውን ከሚያጠፉበት መንገዶች ውስጥ 20% የሚሸፍነው ደግሞ ገዳይ መርዞችን በመጠቀም ነው።

◾️ሰዎች ራሳቸውን ለምን ያጠፋሉ ?

አንዳንድ ግለሰቦች ራስን ማጥፋት  የሰይጣን ግፊት፣ የሞራል ግድፈት እንዲሁም ጥጋብ ይመስላቸዋል።

ነገር ግን ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው ከከሸፈባቸው ሰዎች መካከል ለድርጊታቸው እንደዋና ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት ከዘጠና ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት የጀርባ ታሪካቸው ሲጠና የአዕምሮ ህመም እንደነበረባቸው ጥናቶች ያሳያሉ።

◾️ራሳቸውን ለማጥፋት ተጋላጭ የሆኑ እነማን ናቸው ?

ራሳቸውን ለማጥፋት ከሚሞክሩ ግለሰቦች መካከል ከ 90% በላይ የሚሆኑት  አንድ የአዕምሮ ህመም ሊኖርባቸው ይችላል። ከዚህ ዉስጥም 80% የሚሆነው የድብርት በሽታ (Major Depressive Disorder) ይሸፍናል::

በተጨማሪ:-

- ከልክ ያለፈ ጭንቀት

- ቋሚ የሆነ አካላዊ ህመም (የስኳር፣ የነርቭ ፣ የካንሰር ህመም)

- ብቻቸውን የሚኖሩ ፣ከሌሎች ሰዎች ድጋፍ የማያገኙ ፣ያላገቡ

- ከቤተሰብ አባል ዉስጥ ከዚህ በፊት ራሱን ያጠፋ ሰው ካለ

- ከዚህ በፊት ራስን ለማጥፋት ሙከራ ያደረገ

- መጥፎ የህይወት ጠባሳ ያሳለፈ (መደፈር ፣ ጉልበት ብዝበዛ)

- እስረኞች

በአንፃሩ ተጋላጭነታቸዉ ይጨምራል ።

◾️ራሱን ለማጥፋት ያሰበ ሰው እንዴት ልናውቅ እንችላለን?

ከታች የተዘረዘሩት ግለሰቡ ራሱን ሊያጠፋ እንደሆነ  አመላካች ንግግሮች  ስለሚሆን ቤተሰብ ወይም የቅርብ ሰዉ ትኩረት ሊሰጥባቸዉ ይገባል:-

- ከፍተኛ የሆነ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እንዳላቸው አዘውትረው መናገር ፤

- ህይወት አሰልቺ እና አድካሚ እንደሆነ በተደጋጋሚ መናገር ፤

- ለቤተሰብ ሸክም እንደሆኑ ማሰማት፤

- ወደ መኝታ ሲሄዱ " ምነው ተኝቼ በቀረሁ "  ማለት፣

- " ምነው ፈጣሪ ህይወቴን በወሰዳት " የሚል ቃል ማዘዉተር ይጠቀሳሉ።

◾️ራስን ማጥፋጥ እንዴት መከላከል ይቻላል?

ከላይ የተጠቀሱት አጋላጭ ሁኔታዎች ካሉ እና ራስን የማጥፋት ሀሳብ በተደጋጋሚ የሚመጣ ከሆነ ወደ አዕምሮ ህክምና ተቋም በፍጥነት በመሄድ እና አስፈላጊዉን ምክር እና ህክምና በማግኘት መከላከል ይቻላል።

(ቲክቫህ ኢትዮ. ይህንን ፅሁፍ አዘጋጅቶ ላቀረበው የቤተሰቡ አባል ዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን ምስጋና ያቀርባል)

@tikvahethiopia
" ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር አይቻልም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ/ም ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ በ2015 ትምህርት ዘመን የሬሜዲያል ትምህርት ተከታትለው 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የፍሬሽማን ኮርስ እንዲማሩ መወሰኑን አስታውሷል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ፦

- ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ፤

- ከአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ ሌላ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ፤

- ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር #የማይችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስገንዝቧል።

ተማሪዎች ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም ሄደው መማር የሚፈልጉ ከሆነ መረጃቸው በአግባቡ ተደራጅቶ እንዲሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

(በሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ተፅፎ ለተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቀላሉ ገንዘብ ለማውጣት M-PESA መጣልን በአቅራቢያችሁ ባሉ ወኪሎቻችን ቀልጠፍ ብለው ገንዘብ ማውጣት ወይም ማስገባት ይችላሉ

M-PESAን ለመጠቀም የሞባይል አፑን ያውርዱ ወይም *733# ይደውሉ

ጉግል ፕለይ ስቶር/ አፕል ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
#Oceanስክሪፕቶ

ድርጅታችን በከፍተኛ  ጥራት የሚያመርተውን "Ocean" ስክሪፕቶ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚያከፋፍሉለት ውስን ወኪል ነጋዴዎች አወዳድሮ በመምረጥ መመደብ ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራቹ ፍላጎትና  አቅም ያላችሁ አከፉፉዮች  ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ለወኪል አከፋፋይ ያዘጋጀነውን የልዩ ሽያጭ ዋጋ ስምምነት ውል በማድረግ የድርጅታችን ወኪል ይሁኑ::

+251901835555
+251901832222
#እገታ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው እገታ መባባሱን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በቅርብ ጊዜ እገታ ተፈፅሞባቸዋል ከተባሉ አካባቢዎች አንዱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ነው።

በዋናው የፌዴራል መንገድ ላይ ወረዳውን አቋርጠው በተሽከርካሪ ሲሄዱ የነበሩ 10 የግንባታ ባለሞያዎች በታጣቂዎች ታግተው 20 ቀናት ያህል ከቆዩ በኃላ የተጠየቁትን የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው ከእገታ ነፃ ወጥተዋል።

ከታጋቾቹ አንዱ እገታውን የፈፀሙት የ #ሸኔ / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች ናቸው ያሉ ሲሆን አጋቾቹ " ለመገናኛ ብዙሃን መረጃ ከሰጠን እንደሚገድሉን አስጠንቅቀውናል " ብለዋል።

በወቅቱ የግንባታ ባለሞያዎቹን ጨምሮ 30 የሚደርሱ የአንድ ድርጅት ሰራተኞች በአንድ ተሽከርካሪ ሆነው ሲጓዙ የነበረ ሲሆን 20 የሚደርሱት ሴቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

ሴቶቹን ለአንድ ቀን ካሳደሯቸው በኃላ በነፃ ሲለቋቸው ሌሎች ታጋቾች ግን አጠቃላይ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለው ከ20 ቀን በኃላ መለቀቃቸውን ገልጸዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳንዲ ወረዳ በፊንጫ ጎደቲ ከ10 ቀናት በፊት 8 አርሶ አደሮች ታግተው እያንዳንዳቸው ከ250 እስከ 300 ሺህ ብር ከፍለው ተለቀዋል።

አንድ የአካባቢው ተወላጅ ፤ ታጣቂዎቹ በቀጥታ ወደ ሰዎች ቤት በመሄድ፣ ስልካቸውንም በመቀማት ነው አግተው የሚወስዱት ብለዋል።

በኃላም ታጋቾች በጎረቤትና በቤተሰብ ስልክ ደውለው አጋቾች የጠየቁት ብር እንዲከፈላቸው ተደርጎ እንደሚለቀቁ አስረድተዋል።

ስምንቱ አርሶ አደሮች ከ 250 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር ተጠይቀው ከብት ያለው ሽጦ ፤ ዘመድ ያላቸውም ተበድረው ከእገታው ወጥተዋል ብለዋል።

ታግተው የተለቀቁት ሰዎች እንደሚናገሩት ፤ እገታውን የሚፈፅሙት መንግስት " ሸኔ " የሚላቸው ኃይሎች እንደሆነ የገለፁት ተወላጁ ከታጋቾች ባገኙት ቃል አጋቾቹ " ታጋዮች ነን ለህዝብ ነው የምንዋጋው ለመኖር የሚያስፈልገንን ገንዘብ ማግኘት አለብን " በሚል ሰዎችን ይዘው እንደሚሄዱ ነው የገለጹት።

" እነሱ ይሁኑ ፤ በእነሱ ስም የተደራጁ ይሁኑ በግልፅ ባይታወቅም አንድ መረጃ ከተናገራችሁ ' በህይወት አትኖሩም ' የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነው የሚለቁት " ያሉት የአካባቢው ተወላጅ " በዚህም የተለቀቁ ሰዎች ምንም ነገር መናገር ይፈራሉ። " ብለዋል።

የሰሞኑን እገታ ብቻ ሳይሆን በ2 ወራት በፊት 3 ሰዎች ታግተው ከ300 ሺህ እስከ 350 ሺህ ብር ከፍለው መውጣታቸውን አመልክተዋል።

በአካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ እየተፈፀመ ባለው እገታ ምክንያት ነዋሪው በስጋት ቄዬውን እየለቀቀ እየሸሸ ነው ሲሉ አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት የ " አሉቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል ፕሮጀክት " ሰራተኞች በታጣቂዎች ታግተዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም ምን ያህል ሰራተኞች እንደሆኑ ባይገልጽም " ሰራተኞቹ ባልታወቁ ኃይሎች መታጋታቸውን አመልክቷል።

የስራ ባልደረቦቻቸው የታገቱት 6 ሰራተኞች እንደሆኑ ገልጸዋል።

እነዚህ ሰራተኞች አሁን ምን ላይ እንዳሉ አይታወቅም። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ባልደረቦቻቸው ለታጋቾች ደህንነት በመስጋት መረጃ ለመስጠት እንደማይፈልጉ ተነግሯል።

ጥቅምት 9 / 2015 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን፣ የኢስት ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች የሆኑ " የቻይና ዜጎች ታግተው " መወሰዳቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ " አዲስ ስታንዳርድ " ዘግቧል።

ነዋሪዎች እንዳሉት የሸኔ ታጣቂዎች ከሀምቢሶ ከተማ በአምስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውን ኢስት ሲሚንቶ ፉብሪካ በመቆጣጠር በቁጥር ያልታወቁ የቻይና ዜጎችን አግተው ወስደዋል።

ታጣቂዎቹ " ፊቼ " ን ለመቆጣጠር በማሰብ ጋረ ሹሂ በሚባል ቦታ ላይ ከመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ጋር ረዘም ያለ እና ከፍተኛ ውጊያ ማድረጋቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸው ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ ሲያፈገፍጉ የቻይና ዜጎች አግተው ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ ፤ ስለተባባሰው እገታ የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል ድርጊቱን የሚፈፅሙት የሽብርተኛ ቡድኑ " ሸኔ ነው " ብሏል።

ይህን የሚፈፀመው የፀጥታ ኃይል ስምሪትን እያየ ነው ሲል ገልጿል።

" ቡድኑ አለሁ ለማለት እና ኪሱን ለማደለብ በንፁሃን ላይ እገታ ይፈፅማል ፣ ያፍናል ፣ ይገድላል " ያለው ክልሉ ፤ " መንግሥት ዜጎች ወጥተው እንዲገቡ ሰላም እንዲረጋገጥ የተቻለውን እየሰራ ነው " ብሏል።

" ሰላም የመላ ህዝብ ነው " ክልሉ " ህዝቡ ተደራጅቶ ሰላሙን ማስጠበቅ ፣ ልማቱን ማስቀጠል አለበት። እኛ እያንዳንዱ ቀበሌ እና ቤተሰብ ላይ የፀጥታ ኃይል ስምሪት መስጠት አንችልም። ስለዚህ ህብረተሰቡ ከመንግሥት የፀጥታ ጋር አብሮ በመስራት ፣ መረጃ በመስጠት ፤ ተደራጅቶ አካባቢውንም መጠበቅ አለበት " ሲል ገልጿል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / ኦነሰ በበኩሉ መሰል ድርጊት እንደማይፈፅም እና እጁ እንደሌለበት ገልጾ " ይህ የሽፍቶች ስራ ነው " ብሏል ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል።

" ሁኔታው በስልጣን ላይ ካለው አካል አቅም በላይ እየሆነነው " ያለው ታጣቂ ቡድኑ " ይህ የሆነው ደግሞ በየቦታው ሽፍታ በመብዛቱ ነው " ሲል ገልጿል።

የታጣቂው ቡድን ፤ " የእገታ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ኃይሎች ከመንግስት ኃይል ጋር ግንኙነት ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል " ብሏል።

" ነፍጥ ይዘው መሰል ድርጊት (እገታ) የሚፈፅሙ ተበራክተዋል ፤ በዚህ ምክንያት በስልጣን ላይ ያለው አካል የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ አቅቶታል " ያለው ቡድኑ " ሰላም እና ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሀገር መንግት ነኝ የሚል አካል ነበር ተጠያቂነት ወስዶ ማስተካከል የነበረበት ይህን ግን እያየን አይደለም ስለዚህ ወንጀለኞች ነፍጥ አግኝተው መሰል ወንጀል ፈፅመው ራሳቸውን እያበለፀጉ ናቸው " ብሏል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የኢሰመኮ 3ኛ ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፎች እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር ላይ ተሳተፉ !

መኖሪያ ቤት/ቦታ ማለት ለአንድ ሰው ወይም ለአንድ ቤተሰብ ምን ማለት ነው ?

ሕይወት፣ ትርጉም ያለው ሕይወት፣ ምንድን ነው ? የአንድ ኢትዮጵያዊት ሴት፣ ወይም የአካል ጉዳተኛ ወይም የተፈናቃይ ወይም የአረጋዊ ሕይወት ምን ይመስላል ?

በሕይወት እና በመኖሪያ ቤት ዙርያ እነዚህን እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለኪነጥበብ አፍቃሪዎች፣ ለኪነጥበብ ሙያ ተማሪዎች፣ ባለሞያዎች እና አማተሮች እንዲሁም ለመገናኛ ብዙኃን አባላት እና ሌሎችም በኪነጥበብ እና በሰብአዊ መብቶች መካከል ያለውን ትስስር ማሳየት ለሚፈልጉ ሁሉ፣ በኢሰመኮ አዘጋጅነት በሚካሄደው የ3ኛው ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር የቀረቡ ናቸው።

ኑ፣ ተሳተፉ፣ አብረን እንድናሰላስል የሚረዱ የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ሥራዎቻችሁን ለዕይታ አቅርቡ!
በውድድሩ ለመሳተፍ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዝርዝሩን በዚህ ይመልከቱ - https://bit.ly/46sReAw
ግሎባል ባንክ

ይገምቱ ይሸለሙ!!

በቴሌግራም ቻናላችን ብቻ የጨዋታውን ትክክለኛ ውጤት ለገመቱ 3 እድለኞች የ200 ብር ካርድ ይሸለማሉ፡፡

የቴሌግራም ቻናላችንን ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለፀ። እንዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ፦ - ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ - ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ - ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ከቆየ በኃላ ነው ተብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ፤ ተገልጋዮች በመደበኛ…
" ... ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " - አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ

ከሰሞኑ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ ጨምሮ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛል።

#የግል አስተያየታቸውን ካጋሩት ውስጥ የቀድሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሱሌማን ደደፎ አንዱ ናቸው።

አምባሳደር ሱሌማን ፤ የተወሰደው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም የይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ይህ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

" እነዚህ ሰዎች ዘርግተው የሚጠቀሙበትና በበርካታ ደላሎች የሚሠራበት ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " ብለዋል።

አምባደሩ ፤ " ዛሬም የኢትዮጵያ ፓስፖርት በበርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በደላሎች ሱቆች ውስጥ በይፋ በመቸብቸብ ላይ ይገኛል  " ሲል ገልጸዋል።

" ዜጎቻችን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ እስከ 60,000 ብር የሚጠየቁበት፣ ከቪዛና ከፓስፓርት እድሳት እያንዳንዱ አገልግሎት ጠያቂ $100 ዶላር ላልታወቀ ግለሰብ ወይም ተቋም የሚከፍልበት አሠራር ዛሬም ስላለ በሥራ ላይ ያለው የኦንላይን ሲስተም scrap ተደርጎ በአዲስ መተካት ይኖርበታል። " ብለዋል።

ኦንላይን የቪዛ ጥያቄ አሁንም ሁለት ሦስት ጊዜ ካልተከፈለበት መልስ እንደማይሰጥ ይታወቃል ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፤ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ፤ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ብለዋል።

" ካሉን ቁልፍ የደህነት ተቋማት መካከል የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መ/ቤት ምን ዓይነት ውርደት/ውድቀት ውስጥ እንደከተተን አይተናል። " ያሉት አምባሳደሩ " ተቋሙ ብቻውን ለዚህ አልበቃም፤ የባሰም እንዳለ ምንም ጥርጥር የለውም፣ በየዕለቱ የምናየውና የምንሰማው ጉዳይ ስለሆነ። " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ በሕጋዊ መንገድ ለማደስ ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የሚጠየቅበት አገር ውስጥ መሆናችንን ስናስብ እጅግ በጣም እንደነግጣለን "ም ብለዋል።

" መንግሥት ብዙ ቅድሚያ የሚሰጣቸው (Priorities) ቢኖሩትም የሥልጣን ብልግናና የአስተዳደር በደሎች፣ በተለይም ሌብነት አሁን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች መካከል መሆን ይኖርባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ኢሚግሬሽን ብቻውን እንዳልበሰበሰ ታውቆ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ኮንፈረንስ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ማቅረብ ለሚፈልጉ የቀረበ ጥሪ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 4ኛውን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አስመልክቶ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ አዘጋጅቷል።

በመሆኑም በኢንፎርሜሽን አሹራንስ ፣ ኢንተሊጀንስ እና ኢንፎርሜሽን ዋርፌር እና ተዛማጅ በሆኑ የሳይበር ደህንነት የምርምርና ጥናት ውጤቶች ላይ ጥናታዊ ጽሁፍና የምርምር ውጤቶችን ማቅረብ የሚፈልጉ ሁሉ እንዲሳተፉ ጥሪ እያስተላለፍን።

የምርምርና ጥናታዊ ጽሁፎችን ከዚህ በታች በተገለጸው ኢ-ሜይል አድራሻ መሰረት እስከ ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም መላክ የምትችሉ ሲሆን በኮንፈረንሱ የተመረጡ የጥናትና ምርምር ውጤቶች እውቅና የሚያገኙ መሆኑን እንገልጻለን።

Email address:  [email protected]
ለበለጠ መረጃ: ተረፈ ፈይሳ +251-9-13-23-90-36

ድረ ገጽ ፌስቡክ ዩትዩብ ቴሌግራም

ትዊተር ቲክቶክ
‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን በቅርብ ቀን
****************
‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች ከጥቅምት 12 እስከ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ በይነ መረብ (ኦን ላይን) ወይንም በሁሉም አዋሽ ባንክ ቅርንጯፎች በአካል በመገኘት ማመልከት ይችላሉ፡፡
Dorgommiin kalaqa hojii marsaa 2ffaa Qaxaleewwan Baankii Awaash yeroo dhihootti kan eegalu yoo ta'u dorgomtoonni yaada kalaqaa qabdan Onkololeessa 12 bara 2016 haga Sadaasa 13 bara 2016 A.L.I tti Marsareetii Baankii Awaashiifi dameelee Baankii Awaash hundatti qaamaan argamuun galmaa'uu ni dandeessu.
https://tatariwochu.awashbank.com
#AwashBank #TATARIWOCHU #Qaxaleewwan #Empowering_The_Visionaries #Coming_Soon #Ethiopia #ኢትዮጵያ
#ደራ_ወረዳ #ትኩረት

በደራ ወረዳ ያለው የፀጥታ ችግር አሁንም #አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ፣ የሰዎች ህይወት እያለፈ ፣ ንብረትም እየወደመ መሆኑን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የደራ ወረዳ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ አንድ የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል የልጆቻቸው እናት የሆነች ሚስታቸውን ከ " ኦነግ ሸኔ " ታጣቂዎች ጋር በመወገን ገድለዋል ብለዋል።

አንድ ቃላቸውን ለ ' ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' የሰጡ የሟች የቅርብ ቤተሰብ ነኝ ያሉ ግለሰብ ፤ " በደራ ጁሩ የተባለ አካባቢ አንድ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል የፓሊስ አባል ከኦነግ ሸኔ ጋር በመወገን የአራት ልጆቹን እናትና የ5 ወር ነፍሰጡር ሚስቱን ገድሏል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው የሟች የቅርብ ቤተሰብ ይህ ግድያ በጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ፤ " ጁሩ " የተባለ አካባቢ ላይ እንደትፈጸመ አስረድተው፣ " የሟቿን እናት ጨምሮ ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል። እኛም ልባችን ተሰብሮ አለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛው የዓይን እማኝ #ጥቅምት_9 በገለጹት መሠረት፣ በደራ ወረዳ " ቆሮ ግንደ በርበሬ " ቀበሌ የኦነግ ሸኔ ጦር አካባቢውን እና መንደሩን ካቃጠለ 2 ሴቶችን እና አንድ ወንድ ገድሏል ሲሉ ከሰዋል።

እንደ ነዋሪው ገለፃ ን በታጣቂ ቡድኑ የተገደሉት ፀጋ እምነት፣ ጌታው አቤቱ እና ለግዜው ስሟን ያላወቁት ሴት ናቸው።

እኚሁ እማኝ ፤ " በመንግሥት ይሁንታ #የደራ_ህዝብ ከፍተኛ የዘር የፍጅት እየደረሰበት ነው " ብለዋል።

ይኸው ዘገባ እየተዘጋጀበት እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ታጣቂ ቡድኑ ያለበትን ሁኔታ ሲያስሩዱም፣ " አሁንም በተለያዩ ቀበሌዎች እንደቀጠለ ነው። መንግሥት ምንም እርምጃ አልወሰደም። አድማሱን እያሰፋ ይገኛል " ነው ያሉት።

እኚሁን ምንጭ ጨምሮ ሌሎች የኦሮሚያ እና የአማራ ተወላጅ የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት ፣  አሙማ ገንዶ፣ ኢሉ ጎደ ጨፌ ፣ ሀርቡ ደሶ ፣ ዴኙ ወቤንሶ ፣ ጁሩ ዳዳ፣ ሀቼ ኩሳዬ፣ ካራ፣ ጎዲማ ሶስት ዋርካ፣ ጊሊ ወዲሳ፣  ቆሮ ግንደ በርበሬ፣ በዮ ኖኖ፣ ደንቢ ብርጄ፣ ባቡ ድሬ፣ ወሬ ገበሮ፣ መንቃታ፣ የተባሉና ላሎችም ቀበሌዎች እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) በታጣቂ ቡድኑ ስር ናቸው ይላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ቃላቸውን በስልክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ፣ መከላከያ በአካባቢው እንዳለ፣ እንደ አጠቃላይ ግን ነዋሪው የጸጥታ ችግር ውስጥ እንደሆነ አስረድተው ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል።

ሌላኛው ነዋሪ በበኩላቸው ፤ " ፋኖ ታጣቂዎችም አልፎ አልፎ ጥቃት እያደረሱ  ነው። በመካከል እየተጎዳ ያለው ንጹሐኑ ነው። መንግሥት እርምጃ ቢወስድ ምን አለ ? " ሲሉ ተይቀው ተጨማሪ ሀሳብ ለመስጠት ተቆጥበዋል።

የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ባለፉት ሳምንታት በርካታ ሰዎች በታጣቂ ቡድኑ እንደታገቱ ፣ ከእገታ ለመለቀቅም ከ500 እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እየተጠየቀባቸው እንደነበር፣ በጥቃቱ ከ200 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ፣ በርካታ ቤቶች እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት እንደተቃጠሉ መግለፃቸው ይታወሳል።

የኦሮሚያ ተወላጆችም ፤ " የፋኖ ታጣቂዎች በርካታ ቁጥራቸው ገና በትክክል ያልታወቀ ሰዎችን ገድለዋል " ማለታቸው አይዘነጋም።

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ በሚጠራው የታጣቂ ቡድን ታገቱ የተባሉ ሰዎች ከምን እንደደረሱ፣ የሟቾች ቁጥር ስንት እንደሆነ፣ የቤት ቃጠሎ ጥቃቱ እንደቆመና እንዳልቆመ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ ፣ " ከ500 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር የከፈሉ ተለቀዋል፣ ያልከፈሉትን ገድሏል " ብለዋል ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ታማኝ ምንጭ።

ሌሎች ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚሰነዝሩትን ግድያ፣ ቃጠሎ፣ እገታ እንዳላቆሙ የሟቾችን ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደተገደሉ አስረድተው፣ ይህን ልጓም ያጣ ጥቃት መንግሥት ቸል ብሎታል የዓለም መንግሥታት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይወቁልን ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ደረሰ እና አልቆምመ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ለአቶ ሺበሺን በስልክና በአጭር ጽሑፍ እንዲያብራሩ ጥያቄ ቢያቀርብም #ምላሽ_ለመስጠት_ፈቃደኛ_አልሆኑም

አቶ ሺበሺ ከዚህ በፊት ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ችግሩን ለመቅረፍ የጸጥታ ኃይል እጥረት እንዳለ አስረድተው ነበር።

በተጨማሪ ከዞኑ አስተዳደር፣ ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ የተደረገው ተመሳሳይ ሙከራ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በደራ ስላለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ያነጋገረ ሲሆን " ክትትል ተጀምሯል ግን ገና አላለቀም " የሚል አጭር ምላሽ አግኝቷል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማና በቀቤና ልዩ ወረዳ 'በወሰን ይገባኛል' ጥያቄ የተነሳው ግጭት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ታማኝ ምንጭ፣ " ግጭቱ ወደ ገጠሩ የመዛመት ሁኔታ ነው የሚስተዋለው። ወልቂጤ ከተማ አልፎ አልፎ  ካልሆነ በቀር የከፋ ነገር የለም " ብለዋል። ወሸርቤ፣ ወልቂጤ ዙሪያ ግጭቱ መዛመት አዝማሚያ ያንዣበበባቸው የገጠር ቦታዎች…
#Update

የጊዜያዊ ኮማንድ ፓስት በወልቂጤ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ እና ወደ መደበኛ ስራው እንዳይመለስ እያደረጉ ነው ያላቸውን ህገ-ወጥ ግለሰቦችን አስጠነቀቀ።

ኮማንድ ፖስቱ ፤ በየቦታው የተለያዩ ትንኮሳዎችን በመፍጠር የከተማው ማህበረሰብ እንዳይረጋጋ እያደረጉ ነው ያላቸውን በስም ጠርቶ ያልገለፃቸውን አካላት በጥብቅ አስጠንቅቋል።

በተጨማሪ ፤ በተሽከርካሪና በእግር የሚንቀሳቀሱ ዜጎች ላይ ህገ-ወጥ ድርጊት እየተፈጸመ እንደሆነ ገልጾ " ይህ መቆም መቻል አለበት " ብሏል። የሚፈፀመውን ድርጊት እንዲሁም ስለፈፃሚዎች በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ይህን ማስጠንቀዊያ ሳይቀበል ወይም ተግባራዊ ሳያደርግ ቀርቶ በህገ-ወጥ ድርጊት የሚሳተፍ የየመዋቅሩ #የቀበሌ_አመራርና ግለሰብ በጸጥታው አካሉ ለሚወሰድበት #እርምጃ ኮማንድ ፖስጡ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ አስጠንቅቋል።

ከሰሞኑን በወልቃጤ ከተማ በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱ፣ ንብረትም መወደሙ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#መቐለ

የመቐለ ከተማ አስተዳደር የተሰው ታጋዮች ቤተሰቦች በዘላቂ  ለማቋቋም የሚያስችል የ 11 ሚሊዮን ብር የመነሻ በጀት መመደቡ አስታወቀ። 

የመቐለ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካሕሳይ በማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፃቸው ባሰራጩት መረጃ መሰረት ፤ የከተማ አስተዳደሩ ጥቅምት 9 ቀም 2016 ዓ.ም ባካሄደው ሰብሰባ የሚከተሉት ወሳኔዎች አስተላልፈዋል።

1. በመቐለ ሰባት ክፍለከተሞች የሚገኙ የተሰው ታጋዮች ቤተሰቦች በ32 ቀበሌዎች በማህበር በመደራጀት የመሰቦ ስሚንቶ ለከተማው ነዋሪ እንዲያከፋፍሉ።

2. ለመነሻ የሚሆን ያለ ወለድ ሰርተው የሚመልሱት 11 ሚሊዮን ብር መመደቡ።  

3. የመቐለ ከተማ አስተዳደር በ32 ቀበሌዎች ስሚንቶ ለማከፋፈል ለሚደራጁት : የማከፋፈያ መጋዘን ሰርቶ እንዲያስረክባቸው።

4. የተሰው ታጋዮች ቤተሰቦች በሰሚንቶ ማከፋፈል ስራ ለሁለት አመት እንዲቆዩ።

5. በሁለት አመት ቆይታቸው የሚያጋጡማዋቸው እንቅፋቶች የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ በመስጠት እንደሚፈታላቸውና እንደሚከታተላቸው ውሳኔ አስተላልፈዋል።

መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያደረሰን።

@tikvahethiopia