TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮንትሮባንድ

የመንግሥት ሆኑ ሌሎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ተቋማት ለኮንትሮባንድ ንግድ መቆም መፍትሔ ከመሆን ይልቅ፣ ሕገወጥ ንግድን የሚያባብሱ ሆነው አግኝተናቸዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኃላፊዎች ገለጹ፡፡

በየአካባቢው ያሉ ተቋማት በኮንትሮባንድ ዙሪያ የሚያከናውኑትን በሚመለከት ሲያስረዱ፣ ድርጊቱን በመቃወም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የመንግሥትና ሌሎች አካላት እንዳሉ ሁሉ፣ " ከችግሩ ጋር አብረው የሚኖሩና የሚተገብሩም " እንዳሉ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ተናግረዋል፡፡

የተቋማቱን ስምና አድራሻ ሳይገልጹ እነዚህ ተቋማት ምንም እንኳን ዕርምጃ እየተወሰደባቸው ቢሆንም፣ የኮንትሮባንዲስቶቹ አካልና ተባባሪ ሆነው እየሠሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

" ሁኔታ የሚያመቻቹ፣ የሚያሳልፉ፣ መረጃ የሚሰጡ፣ ሕገወጦችን የሚከላከሉላቸው፣ የሚደብቁ፣ እንዳይያዙና እንዳይመረመሩ የሚያደርጉ፣ ዕቃዎቻቸውን በሽፋን የሚያሳልፉ፣ ሐሰተኛ ሰነድ በመሥራት የሚተባበሩ… " ሲሉ አቶ ደበሌ በሕገወጥ ንግድ ላይ " ቀላል ቁጥር የሌላቸው " ተቋማት እንዴት እንደሚሳተፉ አብራርተዋል፡፡

ስለኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድ ሲነገር እነዚህ ችግሮች በበርካታ ተቋማት እንደሚፈጸሙ፣ ወደታችኛው የአስተዳደር አካል ሲወረድ ደግሞ ችግሮቹ " በጣም በከፍተኛ ደረጃ እየሰፉ ነው " ሲሉ ኮሚሽነሩ ይገልጻሉ፡፡

ችግሩን በመቃወም አስተዋጽኦ እያበረከቱ ካሉ ተቋማት መካከል፣ ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከገቢዎች ሚኒስቴር በተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ዓቃቢያነ ሕጎች፣ የክልል የፀጥታ አካላትና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንደሚገኝበት አስረድተዋል፡፡

ኮንትሮባንዲስቶች ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው በርካታ መንገዶች እንዳሉ ሁሉ፣ ከሁለት ሺሕ ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመውን ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ክፍል እስከ ኬንያ ድንበር ድረስ ያለውን ሥፍራም ለዝውውር እንደሚጠቀሙበት ተገልጿል፡፡

በችግሮቹ ግዝፈትና አስከፊነት ልክ አቅም ያላቸው ተቋማትን መገንባት አንደኛው ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ፣ እንደ ሕግ አስከባሪ ዓይነት ተቋማትንም በሚገባ ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ኮሚሽነሩ አውስተዋል፡፡

አቅምን ከመገንባት ባለፈም የሚወሰደው ዕርምጃ ትልቅ ሊሆን እንደሚገባና ከዚህ በፊት የተወዱት ዕርምጃዎችም ጥሩ እንደሆኑ ሲገልጹ፣ በተጠናቀቀው ዓመት ብቻ እስከ 80 ቢሊዮን ብር የተገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች እንደተያዙ ገልጸዋል፡፡

" ይህ ቁጥር የሕገወጥነትን ጉልበት በልኩ የሚናገር፣ የተወሰደውን ዕርምጃ በልኩ የሚናገር፣ ቀጣይ ምን መሥራት እንደሚገባንም የሚናገር ነው " ሲሉ አቶ ደበሌ ቃበታ ከሰሞኑን መናገራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
የዘመኑን የክፍያ መንገድ ይቀላቀሉ!
********
ካርድዎን ወደ ስልክ ነካ
Tap to Phone (TTP)
********
በንክኪ አልባ ካርድ የክፍያ ተቀባዩን ስልክ ነካ በማድረግ ብቻ ክፍያ መፈፀም የሚያስችል!
አሁን በፐብሊክ አውቶብሶች ላይ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡
#ፈጣን #ቀላል #አስተማማኝ
#CBE #VISA #TTP
#Axum #EthiopianAirlines

የአክሱም ኤርፖርትን ለመጠገን የእቃዎች ግዥ መጀመሩ ተነግሯል።

ትግራይ ባስተናገደችው አስከፊው ጦርነት ወቅት ክፉኛ የወደመው የአክሱም ኤርፖርት እስካሁን ተጠግኖ ወደስራ አልተመለሰም።

የአክሱም ህዝብ ኤርፖርቱ ባለመጠገኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ነው።

በተለይም የተለያዩ አልባሳትን፣ ባህላዊ ጌጦችን እያዘጋጁ የሚሸጡ፣ ከቱሪዝም ገቢ የሚያገኙ ወገኖች ኤርፖርቱ ስለሌለ ስራ መስራት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

በንግድ ዘርፍ ላይ ያሉ ወገኖች ብዙ ደክመው የሚያዘጋጇቸውን ቁሳቁሶች እና ባህላዊ አልባሳት የሚገዛቸው እንዳጡ አመልክተዋል።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዑክ ከኣክሱም ነዋሪዎች ጋር ምክክር አድርጎ ነበር። በዚህም ወቅት የአክሱም ኤርፖርት ጥገና ዋነኛው አደጀንዳ እንደነበር ታውቋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መ/ቤት የክልሎች የጥገና ሂደት አስተባባሪ አቶ ተወልደ ግርማይ ፤ አየር መንገዱ ለኤርፖርቱ ጥገና የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች መገብየት እንደጀመረ አሳውቀዋል።

አቶ ተወልደ ፤ " ምን አለ ? ምን ቀረ ? የሚለውን ለይተን ኤርፖርቱን ለመጠገን የሚያስፈልጉን መሳሪያዎች በመግዛት ላይ ነን። በግዢ ሂደት ላይ ያሉ አሉ። " ብለዋል።

ጥገናው ለህዳር ጽዮን በዓል ይደርሳል ?

ጥገናው ለህዳር ጽዮን ማርያም በዓል አይደርስም ተብሏል።

በየአመቱ ኣክሱም ከተማ የሚከበረው የህዳር 21 ጽዮን በዓል በተለይም ከጦርነት በፊት እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎች ከሀገር እና ከውጭ ይገኙበት እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይ ያለው የሰላም ሁኔታም እጅግ በርካታ ሰዎች ወደ ከተማው በብዛት እንዲገቡ እድል የሚፈጥር ነው።

ነገር ግን እስከ በዓሉ ድረስ ያሉት ውስን ቀናት ስለሆነ የኣክሱም ኤርፖርት ተጠግኖ የመጠናቀቅ እድል የለውም ተብሏል።

አቶ ተወልደ ግርማይ ፤ " የህዳር ጽዮን በዓልን ለማድመቅ የሽረ እንደስላሰ ኤርፖት አስፈላጊ በሆነ መሳሪያዎች እንዲሁም የቦይንድ አውሮፕላን የሚያርፉባቸው ስፍራዎች ለማስተካከል፣ ለማጠናከር እና ለማስፋፋት ባለሞያዎች ተሰማርተዋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GAT ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ዛሬ መሰጠት ጀምሯል። ይሁን እንጂ በመጀመሪያው ቀን የፈተና አሰጣጡ ላይ የተወሰነ የቴክኒካል ችግር አጋጥሞ እንደነበር ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተረድቷል። ችግሩ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተከሰተ መሆኑ ተመልክተናል። ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን በተሳካ መልኩ መስጠታቸውንም ሰምተናል። የቴክኒክ ችግር ያጋጠማቸው ዩኒቨርሲቲዎች የዛሬውን ፈተና…
#GAT

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ዛሬ ይጠናቀቃል መባሉ ይታወቃል።

የመግቢያ ፈተናው ከመስከረም 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥቅምት 01/2016 ዓ.ም ሲሰጥ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የፈተና አሰጣጡ ላይ የቴክኒክ/የሲስተም ችግር አጋጥሞ እንደነበር ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተረድቷል።

ችግሩ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተከሰተ ሲሆን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ፈተናውን በተሳካ መልኩ መሰጠቱን ተመልክተናል።

የቴክኒክ/የሲስተም/የኔትወርክ ችግር ያጋጠማቸው ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን ወደሌላ ቀናት በማሸጋሸግ መስጠታቸው ተገልጿል።

ዋናው ፈተና ከመሰጠቱ በፊት ወጥነት ባይኖረውም ዩኒቨርሲቲዎች ለ4 ቀናት የመለማመጃ ፈተና (Mock Exam) መስጠታቸው ይታወቃል።

በሌላ በኩል የፀጥታ ችግር ባለባቸውና ኔትወርክ በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የGAT አመልካቾችን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ያለው ነገር የለም።

በእነዚህ አመልካቾችና በአጠቃላይ የፈተና አሰጣጡ ሒደት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን መግለጫ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

Via @tikvahuniversity
በሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ተማሪዎችን ሲያስተምሩና ደመወዝ ሲበሉ የቆዩ ግለሰቦች ተፈረደባቸው።

ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማሰራት በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ 3 ግለሰቦች ያለ ብቃታቸው እና ያለ ሙያቸው ሲያስተምሩ በመገኘታቸው ክስ ተመስርቶባቸው ውሳኔ ተላለፈባቸው።

1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ፣
2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ፣
3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ የተባሉት ግለሰቦች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ውስጥ " አንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት " በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ያለ ሙያቸው እና ያለ ብቃታቸው ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ተይዘው የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ ፦ ከአርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ #በባዮሎጂ መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 10/04 /2011 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያየ የደመወዝ መጠን #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 215 ሺህ 739 ብር ተከፍሎታል።

2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ #በእንግሊዘኛ  መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከ04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 800 ብር ተከፍሎታል።

3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ በሂሳብ ትምህርት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 008 ብር ደመወዝ ተከፍሎታል።

ሶስቱም ተከሳሾች ያለሙያቸውና ብቃታቸው ሲያስተምሩ በቆዩባቸው ጊዜያት በተማሪዎች ላይ በገንዘብ የማይተመን እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እና በመንግሥት ላይ ባልተገባ መልኩ በተቀበሉት ደመወዝ 455, 755 የሚገመት ብር ጉዳት አድርሰዋል።

ዓቃቤ ህግ በፈፀሙት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማዘጋጀት እና በመገልገል በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቷል።

የበሉትን ደመወዝም እንዲመልሱ በክሱ ላይ ቀርቧል።

የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ናቸው በማለት ሶስቱም ተከሾች ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ እንዲሁም ያለአግባብ የበሉትን አጠቃላይ 455,755 ብር ለመንግሥት እንዲመልሱ ውሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
ስልክዎን በመጠቀም ብቻ እንዴት የአፖሎ ዲጂታል አካውንት መክፈት እንደሚችሉ ለማወቅ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.iss.one/BoAEth/1018

#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #howto #howtovideo #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ድጋፍና ልማት ማህበር ዋና ፃሃፊ የነበሩት ወታደር ጌታሁን ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ማህበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት አሳውቋል።

የማህበሩ ዋና ፀሀፊ የነበሩት ወታደር ጌታሁን ማሞ ባደረባቸው ድንገተኛ እመም ነው በቀን 01/02/2016 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየቱ።

ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ይፈፀማል ነው የተባለው።

@tikvahethiopia
በትግራይ ክልል " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት መታወጅ ተከትሎ ከቦታ ወደ ቦታ ለሚደረግ ጉዞ ከፍተኛ የትራንስፓርት እጥረት አጋጥሟል።

ያልተገባ የዋጋ ጭማሪም እየተደረገ ነው። 

የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክበር ቀን ስነ-ሰርአት ጥቅምት 2 ታውጆ ጥቅምት 6/2016 ዓ.ም እንደሚጠቃለልና ተዛማጅ ጉዳዮች አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታታይ ዘገባዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል በመቐለ በሚገኙ ሁለቱ መነሃሪያዎች ያለውን ወቅታዊ የትራንስፓርት ሁኔታ ለመታዘብ ጥቅምት 1 እና 2  ከሌሊቱ 10:00 ሰአት ጀምሮ ቅኝት በማካሄድ ትዝብቱ አጋርተዋል።

ህዝቡ ወደየ አከባቢው በመሄድ የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ ለመሳተፍ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በሁለቱም መነሃሪያዎች ረጃጅም ሰልፎች ይሰለፋል።

የህዝብ መጓጓዣ ተሸከርካሪዎች በብዛት በመነሃሪያ ውስጥ ሲሆኑ የትራንስፓርት ስራ እንዲሰሩ ያልተፈቀደላቸው ጨምሮ የተወሰኑት ደግሞ ከመነሃሪያ ውጭ ዋጋ ጨምረው ይጭናሉ።

የዋጋ ጭማሪው ከሃምሳ በመቶ እስከ እጥፍ ማለትም እስከ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ሲከፈል የነበረው 200 ብር ወደ 800 እስከ 1000 ብር ከፍ ማለቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በአካል ታዝበዋል።

የትራንስፓርት እጥረቱ ከመቐለ ወደ ሌሎች ከተሞች ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ከተሞች ወደ መቐለ ጭምር ማጋጠሙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ወደ መኾኒ ራያና ወደ ምስራቃዊ ዞን ሓውዜን ከተማ ስልክ በመደወል አረጋግጧል።

ብርሃነ ገብረ የተባለ ከመቐለ ወደ ዓድዋ ለመጓዝ በተለምዶ ላጪ መነሃሪያ ተብሎ በሚጠራው ተገኝቶ በሰጠው አስተያየት ፤ " ትራፊክ ፓሊሶች ችግሩ እያዩ እርምጃ አይወሰዱም በርካታ መኪኖች ከመነሃሪያ ውጭ በመደበቅ 200 ብር የነበረውን ወደ 800 ፤ 600 ብር የነበረው ደግሞ ወደ 1500 ብር ከፍ በማድረግ ይጭናሉ ፤ አስተማሪና ችግር ፈቺ እርምጃና መፍትሄ የሚሰጥ በመጥፋቱ በሺ የሚቆጠር ተጓዥ ተጉላልተዋል እኮ ለምን ? " ሲል ጠይቋል። 

ከመኾኒ ራያ ወደ መቐለ ለመጓዝ ከሌሊቱ 10:00 የተነሳው አቶ ሃፍሩ ኪሮስ ደግሞ 200 ብር ይከፈልበት የነበረው 600 ብር እንዲከፍል መጠየቁ ተናግሯል።

ወዲ ተካ የተባለው ሓውዜን ከተማ ነዋሪ ደግሞ በመንገድ ትራንስፓርት ሰራተኞች ፣ በትራፊክ ፓሊስና በፀጥታ አካላት መካከል ያለው ያለመናበብ ችግር አሽከርካሪዎች በህገወጥ እንዲሰሩ በር በመክፋቱ ተጓዦች ለከፍተኛ የዋጋ ጭማሪና እንግልት መጋለጣቸው በማህበራዊ የትስስር ሚድያ ሃሳቡ አጋርቷል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአሽከርካሪዎችና ረዳቶች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ የትራንስፓርት ፍሰቱ ነጠላ በመሆኑ ማለት ሄደው ተመላሽ ተጓዥ ስለማይገኝ በቆየው ታሪፍ ማገልገል እንደሚያከስራቸው  ይናገራሉ።

የመንገድ ትራንሰፓርትና የትራፊክ ፓሊስ አባላት በሰጡት አስተያየት ድግሞ አሽከርካሪዎቹ ህዝቡ በየአከባቢው የመርዶ ስነ-ሰርአቱ እንዲሳተፍ የሚያደርገው ከቦታ ወደ ቦታ የመጓጓዝ ሁኔታ ከአደጋ የፀዳ እንዲሆን ትርፍ ከመጫንና በፍጥነት ከማሸከርከር እንዲቆጠቡ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ላይ መሆናቸው ያስረዳሉ።

ሰራተኞቹና ትራፊክ ፓሊስ አባላቱ አክለው እንዳሉት ፣ ባለው ወደ አንድ አቅጣጫ ያተኮረ የትራስፓርት ፍሰት አሽከርካሪዎች ለኪሳራ እንዳይጋለጡ ከነበረው ዋጋ  እስከ 10 በመቶ ጭማሪ በማድረግ እንዲያገለግሉ መፈቀዱንና ከመነሃሪያ ውጭ ያለ መውጫ ፍቃድ የሚጭኑና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ እየተቀጡ መሆናቸው የትራንስፓርት ህጉ እንዲከበር ተጓዦችና አሸከርካሪዎች ተባባሪ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።  

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል ፤ የሚያልፉ ተማሪዎችም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለፁት ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ እንጥራለን  " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ " ፈተናው ዛሬ በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ተጀምሯል። " - የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።…
#Update

በትግራይ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተጠናቀቀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮው ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ መጠናቀቁ አሳውቋን።

የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ፤ አገር አቀፍ ፈተናው በተያዘለት ዕቅድ እንዲጠናቀቅ ያደረጋችሁ ከፌደራል እስከ ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርሲቲዎች ያላችሁ ተቋሞች፣ የትምህርት ኣመራሮች እና መምህራን፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያላችሁ የፀጥታ እና ደህንንት ተቋሞች እና ኣመራሮች፤ ከተለያዩ ኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጣችሁ ፈታኞች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን "  ብለዋል።

ኃላፊው " ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ተፈታኝ  ተማሪዎቻችን ከናንተ የሚጠበቀው ሁሉ ስለደረጋችሁ ለናንተም የላቀ ምስጋና ይገባችኋል " ሲሉ አክለዋል። 

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ/ም  ለአራት ተከታታይ ቀናት በትግራይ ክልል ሲሰጥ የቆየውን የ12 ክፍል አገራዊ ፈተና ከ9,000 በላይ ተማሪዎች መፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያሳያል።

ብሔራዊ ፈተናው የተሰጠው በመቐላ፣ አዲግራት፣ አክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ውጤቱን ባጠረ ጊዜ ለማሳወቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia