TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Update ከጥቅምት 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ተፈፃሚ የሚሆነው የትግራይ የሃዘን ቀን ማሰፈፀምያ መመሪያ ይፋ ሆነ። ከመስከረም 21/2016 ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆንና የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ፊርማ ያረፈበት 18 አንቀፆችን የያዘ የትግራይ የሃዘንና መርዶ " መመሪያ ቁጥር 022016 " ምን ይላል ? የመርዶና የሃዘን ስነ-ሰርአቱ ጥቅምት 2…
#ትግራይ
" የሚቋረጥ የትራንስፓርት አገልግሎት የለም ፤ ባንኮች ግን ለሁለት ቀን ዝግ ይሆናሉ " - የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት
የትግራይ የአርበኞች ኮሚሽን ም/ቤቱ በትግራይ ክልል ደረጃ የታወጀው " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት አስመልክቶ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ስብሰባው የህክምናና የትራንስፓርት አገልግሎት የማይቋረጥ ሲሆን የባንከ አገልግሎት ግን ጥቅምት 3 እና 5 /2016 ዓ.ም ለሁለት ቀን ዝግ ይሆናል ብሏል።
በትግራይ ደረጃ የሚከናወነው " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት ጥቅምት 2 አመሻሽ በይፋ በሚድያ ተነግሮ ከጥቅምት 3 አስከ 5 ባሉት ሶስት ቀናት በተመሳሳይ ሰአት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቁጥጥር ስር ባሉ ሁሉም የክልሉ አከባቢዎች በጥብቅ ድስፒሊን እንደሚተገበር ምክር ቤቱ አስታውቀዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንትና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ፤ * የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ ትግራዋይ ያለ ልዩነት ያስተሳሰረ የጋራ አጀንዳ ነው " ብለዋል።
ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቁጥጥር ስር ባሉት አከባቢዎች ተግባራዊ የሚሆነው የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ህዝቡ በቀበሌ ደረጃ በማሰባሰብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሰርአቱ በጠበቀ መልኩ እንዲፈፀም የሚያስተባብሩ አራት ንኡሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ስራ ጀምረዋል ብለዋል።
ኮሚቴዎች የሚድያና የማነሳሳት ፣ የመርዶ ፣ የህግና የፋይናንስ መሆናቸውን ያብራሩት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ፤ ኮሚቴዎቹ የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ በተያዘለት እቅድ እንዲፈፀም ፣ ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም የወጣ መመሪያ የሚጥስ ደግሞ ከገንዘብ እስከ የእስራት ቅጣት እንዲጣልበት ለመከታተል ሃላፊነት የተሰጣቸው እንደሆኑ ገልጸዋል።
በተያያዘ " የሰው ህይወት በማጥፋት ፣ ሴት ልጅ በመድፈርና ለጠላት ሚስጥር በመስጠት ወንጀል " ከሚጠየቁ ተብለው በእስራት ላይ ከሚገኙት ውጭ ያሉ የህግ ታራሚዎች በፀጥታ አስከባሪ በመታጀብ ቤታቸው ድረስ በመሄድ የቤተሰቦቻቸው መርዶ እንዲካፈሉ የትግራይ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት መወሰኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ፊርማ ያረፈበት 18 አንቀፆች የያዘ የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ማስፈፀምያ መመሪያ ቁጥር 022016 ከመስከረም 21/2016 ዓ..ም ጀምሮ መተግበር ጀምረዋል።
መመሪያው " የሰማእታት አስከሬን ከቦታ ወደ ቦታ ማንቀሳቀስ የሚከለክል " ሲሆን ፤ ይህንን መመሪያ የጣሰ ከብር 50 ሺህ እስከ ሶስት አመት አስራት እንደሚቀጣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

የእስራኤልና ፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት በቀጣይ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ? ዋና ነጥቦች ፦ ▪️ሃማስ ፤ " ወራሪ " ናት በሚላት #እስራኤል ላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመሩንይህ ኦፕሬሽንም #ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ እንደሆነ ገልጿል። ▪️ እስራኤል ፤ " አሸባሪ " የምትለው የሃማስ ቡድን ጥቃት መክፈቱ ከባድ ስህተት መሆኑን በመግለፅ ለእያንዳንዱ ድርጊቱ…
#Update
የእስራኤል እና የፍልስጤም ሀማስ ጦርነት ዛሬም ለተከታታይ ቀን እጅግ ተባብሶ መቀጠሉን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።
የአሁኑ ጦርነት ከመቼውም የከፋ ነው ተብሏል።
ጦርነቱ እስካሁን የምን ያህል ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ ?
እስራኤል ፦ 1,200 ሰዎች ሞተዋል። 3,418 ተጎድተዋል።
ጋዛ ፦ 950 ፍልስጤማውያን ሞተዋል። 5,000 ተጎድተዋል።
በእስራኤል እና ጋዛ ድንበር ቅርብ ርቀት ላይ በነበረ አንድ የሙዚቃ ዝግጅ ላይ ሀማስ በፈፀመው ጥቃት የሞቱ ከ260 በላይ ሰዎች አክሬን መነሳቱ የተነገረ ሲሆን አሁንም ድረስ በሃማስ እጅ የሚገኙ ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች አሉ ሲል ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ከእስራኤል እና ፍልስጤማውን ባለፈ የአሜሪካን ጨምሮ እስራኤል ውስጥ የነበሩ የሌሎች ሀገራት ዜጎች በሃማስ ጥቃት መገደላቸው ተነግሯል።
2 ሚሊዮን ህዝብ ባለበት በጋዛ ሰርጥ ውሃ፣ ምግብ፣ነዳጅ የለም ተብሏል። ሰዎች መሄጃ አጥተው ተቀምጠዋል።
ሃማስ በእስራኤል ላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ጀመርኩ ካለ በኃላ እስራኤል በተለይ በአየር እየወሰደችው ባለው አፀፋ በጋዛ የሚገኙ ህንፃዎች፣ ቤቶች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።
አንድ የፍልስጤም ጋዜጠኛ ከዚህ ቀደም 6 ጊዜ ያህል በጋዛ የተካሄደ ጦርነት መዘገቡን ገልጾ ይኸኛው እጅግ በጣም የከፋውና ፍፁም ደም አፋሳሽ እንዲሁም ምንም ህግ የሌለበት ነው ብሏል።
እስራኤል በሃማስ ጥቃት ህፃናት እና ሴቶች ሳይቀሩ መገደላቸውን የገለፀች ሲሆን ሃማስ በተመሳሳይ እስራኤል በምትፈፅመው ድብደባ በርካታ ህፃናት እና ሴቶች መገደላቸውን ገልጿል።
ሀገራት በጦርነቱ የተለያየ አቋም ይዘዋል። አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራባውያን ሀገራት ሃማስን " አሸባሪ " ሲሉ አውግዘው ከእስራኤል ጎን መቆማቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ ከድጋፍ ቃል በዘለለ ወታደራዊ ድጋፍም እያደረገች ነው።
ኢራን " እየሩሳሌም እና ፍልስጤም " ነፃ እንዲወጡ ከፍልስጤም ተዋጊዎች ጎን መሆኗን አስረግጣ ተናግራለች። እንደ ሩስያ እና ቻይና ያሉ ኃያላን ሀገራን ጦርነቱ እንዲበርድ ተኩስ እንዲቆም የሚል አቋም ይዘዋል። ቱርክ ይህ አስከፊ ጦርነት ይበርድ ዘንድ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አደርጋለሁ ብላለች።
ሌላው የእስራኤል ጎረቤት ከሆኑት ሌባኖስ (ሂዝቦላህ ቡድን) እንዲሁም ከሶሪያ አቅጣጫ እስራኤል ላይ መሳሪያ የተወረወረ ሲሆን ይህ ጦርነቱን ይበልጥ አስፋፍቶ ሌሎች ሀገራትም ገብተውበት የከፋ ሁኔታ እንዳይፈጠር አስግቷል።
ያም ሆነ ይህ ጦርነቱ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ እርስ በእርስ ከሚፋለሙት የታጠቁ ኃይላት ባለፈ እጅግ በርካታ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን እያረገፈ ይገኛል።
ምንም እንኳን ጦርነቱ መካከለኛው ምስራቅ ቢገኝም ዳፋው ለዓለም እንዳይተርፍ ይሰጋል። ከወዲሁ ነዳጅ ዋጋው እየናረ ነው።
ተጫማሪ መረጃዎችን በ @BirlikEthiopia ማግኘት ይችላሉ።

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ። በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰው ከፍተኛ ጦርነት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ማድረጉ ተዘግቧል። የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ4 % በላይ መጨመሩ ተነግሯል። ባለፉት ሳምንታት ወደ 96 ዶላር ደርሶ የነበረው የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፉት ቀናት ጥሩ የሚባል ቅናሽ እያሳየ መጥቶ ነበር። ነገር ግን ቅዳሜ በሃማስ እና እስራኤል መካከል…
#ነዳጅ
በመካከለኛው ምሥራቅ በእስራኤልና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ መፍጠር የጀመረው የዋጋ ጭማሪ ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ የበለጠ ሰማይ ሊነካ ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ የነዳጅ ዋጋን ወደ ተጠቃሚው ለማስተላለፍ በወሰነው መሠረት እስሁን ድረስ በአማካይ ከአሥር በመቶ በላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረገ የመጣ በመሆኑ በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊፈጥር የሚችለው የዓለም የነዳጅ ዋጋ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ ከማስተላለፍ ሊቆጠብ እንደሚገባ የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክኤ መክረዋል።
የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክሌ ምን አሉ ?
" በመካከለኛው ምሥራቅ የሚከሰት ጦርነትና አለመረጋጋት በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።
በቀዳሚነትም የዓለም የነዳጅ አቅርቦትና ገበያ የሚታወክ በመሆኑ፣ ይህ ሁኔታ የሚከሰት ከሆነ አሉታዊ ተፅዕኖው ለኢትዮጵያም የሚተርፍ እና የሚያሰጋ ነው።
የዓለም የነዳጅ ምርትና ገበያ ሰላምን ይፈልጋል። እንዲህ ያሉ ትልልቅ ጦርነቶች በተለይ አገሮች በፖለቲካ አመለካከታቸው ወገንተኝነታቸውን በግልጽ በሚያሳዩበት ወቅት የነዳጅ ግብይት ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።
በተለይ አሁን በተቀሰቀሰው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ የመካከለኛው ምሥራቅ ነዳጅ ባለፀጎች ለአንደኛው ወገን የሚያደላ የፖለቲካ አቋም ለመያዝ ከተገደዱ ይህንን የፖለቲካ አቋማቸውን የሚገልጹት የነዳጅ ምርትና አቅርቦታቸውን በመገደብ እንደሚሆን ቀደም ሲል የነበራቸውን ተሞክሮ ያሳያል።
ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በነዚሁ ወገኖች መካከል በተቀሰቀሰ ጦርነት ነዳጅ አምራች አገሮች በሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል ጎራ ለይተው በመሠለፋቸው በዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ዕክል ፈጥረው ነበር።
አሁንም እነዚሁ ተመሳሳይ አገሮች የሚፋለሙበት ጦርነት በመከሰቱ በነዳጅ ሀብት የታደሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በዋናነትም፣ ኢራንና ሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ አገሮች አንደኛውን ተፋላሚ ወገን ደግፈው ምዕራባዊያኑ ደግሞ ሌላኛውን ወገን ደግፈው የሚቆሙ ከሆነ የዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦትን ሊያስተጓጉልና ዋጋውም ጣሪያ ሊነካ ይችላል።
ይህ ሁኔታ ከተከሰተ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ትልቅ ፈተና ነው።
ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት ቀስ በቀስ የሚያደርገውን የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሠረት ያደረገ ወርኃዊ የችርቻሮ ዋጋ ማስተካከያ ቆም ብሎ ሊፈትሸው ይገባል።
ያልጠበቀውን ጦርነት ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዳለ ኅብረተሰቡ ላይ መጫን የሚያዋጣ አይደለም።
መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት በገበያ ዋጋ እየሠራ ቢሆንም እንዲህ ባሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ግን ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖው ግልጽ ከመሆኑ አንፃር በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየው የዋጋ ንረት ጦርነቱ ሊያስከትል የሚችለውን የዋጋ ጭማሪ ኅብረተሰቡ ላይ እንዲጫን ማድረግ ተገቢ አይሆንም።
ይህ ካልሆነ ግን የዋጋ ንረቱን በማባባስ ማኅበረሰብን ብሎም ኢኮኖሚውን ይጎዳል።
በሌላ በኩል ግን የእስራኤልና የፍልስጤም ጦርነት ከተፋላሚ አገሮች ባሻገር አገሮችን ጎራ ለይተው ወገንተኝነታቸውን እየገለጹ መሆን ምናልባት ትላልቆቹ የነዳጅ አቅራቢዎች ነዳጅ ባያቀርቡ ዓለም ላይ ችግር እንዳይኖር በተቃራኒ ያሉ አገሮች ተጨማሪ ነዳጅ በማቅረብ ገበያውን ለማረጋጋት ሊሞክሩ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ አለ። ይህ ሊሆን የሚችለበት ዕድል ጠባብ ቢሆንም አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ሲታይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው አይቀመስም ብዙ አገሮችን ተጎጂ ያደርጋቸዋል፡፡
በተለይ ከፍተኛ የገቢ ንግድ ያለቸው አገሮች የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትልባቸው ይችላል። ስለዚህ በተለይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ሊያስከትል የሚችለው ተፅዕኖ በማሰብ መንግሥትም ጊዜውን የዋጀ አሠራር ያስፈልገዋል።
በአጠቃላይ ግን የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ዓለም አቀፉን ኢኮኖሚ ይፈትናል፡፡
ጦርነቱ ዛሬ ያቆማል ቢባል እንኳን በብዙ መልኩ ተፅዕኖው ቀላል አይሆንም። በተለይ ዕቃን የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ዘርፎች በሚፈጠርባቸው ሥጋት እንቅስቃሴያቸው ይገደባል፡፡ ከዚህም ሌላ መንቀሳቀስ ከቻሉም ከፍተኛ የኢንሹራንስ ሽፋን የሚጠይቁ መሆኑንና ተያያዥ ጉዳዮች የአቅርቦት ዋጋን ስለሚያስወድዱ የጦርነቱ ግልጽ የሆነ ተፅዕኖ አለው። "
(ከሪፖርተር የተወሰደ)

#Update ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው " 5 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ አሳልፈዋል፡፡ " ብለዋል። ሌሎች 5 ትምህርት ቤቶች ድግሞ ካስፈተኗቸው ውስጥ 95 ከመቶ ተማሪዎቻቸውን እንዳሳለፉ ገልጸዋል። ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦ 1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት (ደብረማርቆስ) 2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት 3. ባህርዳር ስቴም ትምህርት…
#አማራ
በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙ ካሳለፉ 5 ትምህርት ቤቶች 3ቱ በአማራ ክልል የሚገኙ ናቸው።
ሶስቱ ትምህርት ቤቶች ፦
- ደሴ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት፣
- ሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ የአደሪ ትምህርት ቤት
- ባሕር ዳር ስቴም ትምህርት ቤት ናቸው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በማኅበራዊ ሳይንስ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ተማሪም የሐዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው።
እንደ አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ በሐዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት እና በደሴ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት በድምሩ 32 ተማሪዎች 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡
አማራ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ክልሎች ባለፉት አመታት በሰላም እጦት ክፉኛ እየተጎዳ ቢሆንም መሰል ትልልቅ ውጤቶች መመዝገባቸው ለቀጣይ ተስፋ ሠጪ ነው ተብሏል።
የአማራ ክልል ተማሪዎች የጥይት ድምጽ እየሰሙ ተምረዋል፤ የጥይት ድምጽ እየሰሙ ተፈትነዋል፡፡ አብዘኛዎቹ የክልሉ ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት በወደሙ እና በተዘረፉ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተገድደዋል፡፡ በፈተና ወቅት በተፈጠረ አለመረጋጋት ፈተናውን አቋርጠው የወጡ ተማሪዎችም ነበሩ።
ይህ ሁሉ ቢሆንም በሀገር አቀፉ ፈተና የተገኘው ውጤት አጥጋቢ ባይሆንም፣ ሰላም ከተረጋገጠ፣ የተረጋጋ እና የተስተካከለ ትምህርት መሥጠት ከተቻለ ግን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ያሳየ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
ቢሮው እንደ ሀገር የተዘመገበው ውጤት ዝቅተኛ መሆኑን ገልጾ በትምርት ስርዓቱ ላይ በርካታ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብሏል።
ከታች ጀምሮ መሥራት ከተቻለ ውጤት ማምጣት የሚችሉ ልጆች አሉንም ሲል ገልጿል።
በአማራ ክልል ጦርነት እና ግጭት በፈጠሩት ሥነ ልቦናዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተፈተኑ ተማሪዎች መኖራቸው ያስታወሰው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች ጫናውን ተቋቁመው ያስመዘገቡት ውጤት ጥሩ መሆኑን አመልክቷል።
ወደ ፊት መሥራት ከተቻለ ተስፋ የታየበት መሆኑንም ገልጿል።
ቢሮው በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ትምህርት ሰጭ ነው ያለ ሲሆን የተሻለ ዜጋ ለማፍራት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ማስፋት ያስፈጋል ብሏል። በክልሉ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑንም አሳውቋል። #AMC

"ብልሆች ወደ ህልማቸው ለመድረስ ይቆጥባሉ!" ከባንካችን ጋር አብረው ሲሰሩ ለስኬትዎ ብርቱ አጋር በመሆን የድርሻችንን እንወጣለን ፡፡
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!
#globalbankethiopia #GBE #banksinethiopia #fintech #bank #finance #ethiopia #ethiopian #digitalbanking #Globaldigital

#ቴሌግራም
ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) ይጠቀማሉ ?
የተለያዩ የዲጂታል መተግበሪያዎችንና አገልግሎቶችን ስንጠቀም ቀዳሚው ነገር ደኅንነቱን የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ይህም በሁለት አይነት መልኩ መመልከት ይቻላል።
የመጀመሪያው የምንጠቀመው መተግበሪያም ይሁን ድረ-ገጽ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል ሲሆን ሁለተኛው በራሳችን የምናደርገው የደኅንነት ማረጋገጫ ሂደቶችን ማጠንከር ነው።
💻 የደኅንነት ማረጋገጫ ሂደቶችን እንዴት ማጠንከር ይቻላል ?
- የምንጠቀመው የይለፍ ቃል (Password) በቀላሉ ተገማች መሆን የለበትም። በተቻለ መጠን ጠንካራ የይለፍ ቃል [ ፊደል፣ ቁጥርና ምልክቶችን ያካተተ] ቢጠቀሙ ይመከራል።
- ተጨማሪ የደኅንነት መጠበቂያ ሥርዓቶችን መጠቀም ያስፈልጋል። ይህም ድንገት እንኳን ሰዎች የይለፍ ቃላችንን (Password ) ቢያገኙት በዚህኛው በሁለተኛው የደኅንነት መጠበቂያ መያዝ እንችላለን። ይህም በአብዛኛው ጊዜ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) በመባል ይታወቃል።
- ስልክ ቁጥራችን በዚህ ሰዓት አንዱ ትልቁ የደኅንነት ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን የሂሳብ አካውንት ቁጥራችን ጭምር ነው። በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የምንጠቀመው ሲም ካርድ በስማችን መውጣቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ ይህ ካልሆነም ሲም ካርዱ በእጃችን እያለ በስማችን ማዞር ይጠበቅብናል። በአንጻሩ በስማችን ተከፍቶ የነበረ ሲም ካርድ ካለ አሁን የሚገለገለው ግለሰብ ስሙን ወደ ራሱ እንዲያዞርም ማድረግ ይጠበቃል።
- የበመልዕክት ሚላኩልንን የማረጋገጫ ቁጥሮች (OTP) በምንም መልኩ ለሌሎች አሳልፈን መስጠት አይጠበቅብንም። በተመሳሳይ የትኛውም አካል የሚስጢር ቁጥራችንን ቢጠይቀን መናገርም ሆነ መላክ አይኖርብንም።
💻 ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) ባልጠቀምስ ?
- የይለፍ ቃል (Password) የሚያገኝ/ የሚያቅ ሰው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ግል አካውንቶ ይገባል።
- ተሳስተው በተለያዩ መንገዶች የሚላኩ ሊንኮችን ቢከፍቱና ስልክና የይለፍ ቃል እንዲያስገቡ ተጠይቀው ቢያስገቡ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ የማይጠቀሙ ከሆነ የግል አካውንቶ የሌሎች መጠቀሚያ ይሆናል።
💻 ቴሌግራም ላይ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) እንዴት መጠቀም እችላለሁ ?
በቴሌግራሞት ላይ Setting የሚለው ላይ ገብተው Privecy and Security በመጫን Two-Step verification የሚለውን ON በማድረግ የይለፍ ቃል መፍጠር እንዲሁም የይለፍ ቃሉን ቢረሱት መልሰው የሚያገኙበትን ኢሜይል አስገብተው የደኅንነቶን ደረጃ ከፍ ማድረግ ይችላሉ። [ ሙሉ ሂደቱ ከላይ በምስሉ ተያይዟል።]
#StaySafeOnSocialMedia
#DigitalLiteracy
Via👋 @TikvahethMagazine
ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) ይጠቀማሉ ?
የተለያዩ የዲጂታል መተግበሪያዎችንና አገልግሎቶችን ስንጠቀም ቀዳሚው ነገር ደኅንነቱን የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ይህም በሁለት አይነት መልኩ መመልከት ይቻላል።
የመጀመሪያው የምንጠቀመው መተግበሪያም ይሁን ድረ-ገጽ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል ሲሆን ሁለተኛው በራሳችን የምናደርገው የደኅንነት ማረጋገጫ ሂደቶችን ማጠንከር ነው።
- የምንጠቀመው የይለፍ ቃል (Password) በቀላሉ ተገማች መሆን የለበትም። በተቻለ መጠን ጠንካራ የይለፍ ቃል [ ፊደል፣ ቁጥርና ምልክቶችን ያካተተ] ቢጠቀሙ ይመከራል።
- ተጨማሪ የደኅንነት መጠበቂያ ሥርዓቶችን መጠቀም ያስፈልጋል። ይህም ድንገት እንኳን ሰዎች የይለፍ ቃላችንን (Password ) ቢያገኙት በዚህኛው በሁለተኛው የደኅንነት መጠበቂያ መያዝ እንችላለን። ይህም በአብዛኛው ጊዜ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) በመባል ይታወቃል።
- ስልክ ቁጥራችን በዚህ ሰዓት አንዱ ትልቁ የደኅንነት ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን የሂሳብ አካውንት ቁጥራችን ጭምር ነው። በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የምንጠቀመው ሲም ካርድ በስማችን መውጣቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ ይህ ካልሆነም ሲም ካርዱ በእጃችን እያለ በስማችን ማዞር ይጠበቅብናል። በአንጻሩ በስማችን ተከፍቶ የነበረ ሲም ካርድ ካለ አሁን የሚገለገለው ግለሰብ ስሙን ወደ ራሱ እንዲያዞርም ማድረግ ይጠበቃል።
- የበመልዕክት ሚላኩልንን የማረጋገጫ ቁጥሮች (OTP) በምንም መልኩ ለሌሎች አሳልፈን መስጠት አይጠበቅብንም። በተመሳሳይ የትኛውም አካል የሚስጢር ቁጥራችንን ቢጠይቀን መናገርም ሆነ መላክ አይኖርብንም።
- የይለፍ ቃል (Password) የሚያገኝ/ የሚያቅ ሰው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ግል አካውንቶ ይገባል።
- ተሳስተው በተለያዩ መንገዶች የሚላኩ ሊንኮችን ቢከፍቱና ስልክና የይለፍ ቃል እንዲያስገቡ ተጠይቀው ቢያስገቡ ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ የማይጠቀሙ ከሆነ የግል አካውንቶ የሌሎች መጠቀሚያ ይሆናል።
በቴሌግራሞት ላይ Setting የሚለው ላይ ገብተው Privecy and Security በመጫን Two-Step verification የሚለውን ON በማድረግ የይለፍ ቃል መፍጠር እንዲሁም የይለፍ ቃሉን ቢረሱት መልሰው የሚያገኙበትን ኢሜይል አስገብተው የደኅንነቶን ደረጃ ከፍ ማድረግ ይችላሉ። [ ሙሉ ሂደቱ ከላይ በምስሉ ተያይዟል።]
#StaySafeOnSocialMedia
#DigitalLiteracy
Via
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እንስትዋ በሦስት ወር የትዳር አጋርዋ በግፍ ተገደለች።
ግድያው የተፈፀመው በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን በምትገኘው የዓዲ ጉደም ከተማ ሲሆን ፤ ተጠርጣሪው በፓሊስ ቁጥጥር ሰር ውሏል።
በግፍ የተገደለችው እንስት ኪሮስ ሕሉፍ ትባላለች። የግፍ ግድያ ፈፅሞባታል ተብሎ የተጠረጠረው የሶስት ወር የትዳር አጋርዋ የሆነ ትራፊክ ፖሊስ ነው።
ተጠርጣሪው ትራፊክ ፖሊስ ሙሉጌታ ገ/ዋህድ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት የሦስት ወር የትዳር አጋሩ ከሆነቸው ኪሮስ ሕሉፍ በተፈጠረው አለመስማማትና ጭቅጭቅ ታጥቆት የነበረው " ኤፍ ዋን ቦንብ " በማፈንዳት ባለቤቱ ወድያውኑ ህይወትዋ ሲያልፍ በተጠርጣሪው እና በሟችዋ አባት ሃለቃ ሕሉፍ ካሕሳይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።
የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ሴቶች ማህበር በእንስትዋ የተፈፀመው የግፍ ግድያ በማውገዝ ጉዳዩ በህግ መከታተል መጀመሩን አሳውቋል።
የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሴቶች ማህበር መስከረም 29/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በእንስትዋ ላይ በተፈፀመው የግፍ ግድያ እንደማህበር ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል የግፍ ተግባሩ በእጅጉ እናወገግዛለን ብሏል።
በሴቶች ላይ የሚፈፀም አሰቃቂ ተግባር መቆም አለበት ያለው መገለጫው ፤ ማህበሩ አሰቃቂና አስደንጋጭ ያለለውን ወንጀል በአፈጣኝ በፍትህ እንዲዳኝ በተደራጀ አኳሃን ከፀጥታ አካላት በመቀናጀት አሰራለው ብሏል።
የማህበሩ መግለጫ በማከል የግፍ ወንጀሉ በሌሎች እንዳይደገም በግፍ ፈፃሚው ተጠርጣሪ ህግ አስተማሪ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አሳስቧል።
በትዳር አጋሮች መካከል የተፈጠረ አለመስማትና ጭቅጭቅ የህይወት ግድያ ማስከተሉ በርካታ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ትግራዎት የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎችን ያሳዘነ ሲሆን ደርጊቱ በማውገዝ 'ባለትዳሮች ከስሜታዊ ተግባር በመራቅ መነጋገርና መግባባት ማስቀደም እንዳለባቸው ' ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

Video
ኤርዶጋን ምን አሉ ?
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ዙሪያ ይህን ብለዋል ፦
- በሲቪሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ወይም በሲቪል አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ትክክል አይደለም፤ አንቀበለውም።
- በእስራኤል ግዛት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንቃወማለን።
- በጋዛ ውስጥ ንጹሃን ያለየ ' #ጭፍጨፋ ' በፍጹም አንቀበልም።
- አሳፋሪ ዘዴዎችን በመጠቀም የሚካሄደው ግጭት ፣ ጦርነት ሳይሆን ' ጭፍጨፋ ' ነው።
- ማንኛውም አካል ፍልስጤማውያንን 🇵🇸 ለመቅጣት ዓላማ ካላቸው ውሳኔዎች መራቅ አለበት።
- ሽምግልና እና ፍትሃዊ ዳኝነትን ጨምሮ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን።
በእስራኤል እና በፍልሥጤሙ ሃማስ መካከል ቅዳሜ የጀመረው ደም አሳፋሽ ግጭት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ሃማስ ወደ ቴላቪቭ እና ማዕከለኛው እስራኤል ሮኬቶችን ሲያስወነጭፍ ውሏል።
እስራኤል የምትወስደውን የአስፀፋ እርምጃ አጠናክራ ቀጥላለች። ሠራዊቷን ጋዛ ድንበር ላይ በማከማቸት ላይ እንደሆነችና የምድር ጥቃት ሊደረግ እንደሚችል እየተጠበቀ ይገኛል። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይም ወደ " ጋዛ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነን " ማለታቸው ተዘግቧል።
በጦርነቱ ሌሎች ኃይሎች እንዳይሳተፉበት ተሰግቷል ፣ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ " አሜሪካ እስራኤል የምትፈፅመው ጥቃት አጋር ናት " ያለ ሲሆን ለሚፈፀመው ግድያ፣ ወንጀል እና ጋዛ ላይ ለተደረገው ከበባ ተጠናቂነት አለባት ብሏል።
#አሜሪካ እና አጋሮቿ የ " ሂዝቦላህ " የታጠቀ ኃይልን " ከእስራኤል ጋር ጦርነት ውስጥ ለመግባት አትሞክር አርፈህ ተቀመጠ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የየመኑ " ሁቲ ኃይል " አሜሪካ በቀጥታ ጦርነቱ ላይ ወታደራዊ ተሳትፎ ካደረገች ከወንድሞቻችን (ሃማስ) ጋር በመሆን ጦርነቱን እንቀላቀላለን በሚሳኤል እና ድሮን እንዲሁም በሌሎች አመራጮች የታገዘ ጥቃት እስራኤል ላይ እንከፍታለን ሲሉ ዝተዋል።
More 👉 @BirlikEthiopia
https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል።
የአሁኑ ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑን ከቀናት በፊት መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ በወረቀት ነው የሚሰጠው።
ይህ የፈተና አሰጣጥ አካሄድ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ፣ በመንግሥት በጀት ፣ በትምህርት ቢሮዎች ላይ ጫናውን እንደሚቀንስ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አመልክቷል።
የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶቹ እየተደረጉ ሲሆን የሶፍትዌር ስራው ከወዲሁ መጠናቀቁ ተገልጿል።
የዘንድሮውም ምዝገባ በኦንላይን ሲሆን፣ ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ ይደረጋል ፤ በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ ይሄዳል ተብሏል።
የተሻሉ የፈተና አዘጋጆች፣ ፈተናዎች እንዳይሰረቁ የሳይበር ጥበቃ፣ የደህንነት ካሜራዎች ፣ የተቋማት ትብብር (ኢንሳ፣ ፈተናዎች አገልግሎት) ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የፈተና ህትመት ዝግጅት ከዚህ ቀደሙም በተሻለ መልኩ ጠንካራ ስራ በጋራ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ እራሳቸውን ለመመዘኛ ፈተናው ብቁ እና ዝግጁ እያደረጉ መሄድ ያለባቸው ሲሆን መምህራን፣ ወላጆች፣ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተማሪዎችን እያገዙ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማደርግ አለባቸው።
በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ገብተው ባለፉት ሁለት ብሄራዊ ፈተናዎች ማለትም በ2014 እና 2015 ከተፈተኑት አጠቃላይ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥተው ያለፉት እጅግ ጥቂት ናቸው።
በ2014 ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 30,034 ወይም 3.3 በመቶ ብቻ ሲሆኑ በ2015 ፈተና 845,099 ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ የቻሉት 27,267 ወይም 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።
በተለይ ፈተናው በየአካባቢው ካሉ ትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ወጥቶ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበው ውጤት ብዙሃኑን ያስዳነገጠ እንዲሁም የትምህርት ስርዓቱ ያለበትን አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ያመላከተ ሆኗል።

Don't let this life-changing opportunity slip away! Apply now and open the doors to the resources and support that will help you transform your entrepreneurial dreams into a beautiful reality. Visit jasiri.org/application
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ
የመጀመርያ ዙር ቆይታውን በባህርዳር፣ ሁለተኛ ማረፊያውን ድሬዳዋን ያደረገው አውደርዕዩ በብዙዎች ተወዳጅነትን አትርፏል።
በሀዋሳም ግሩም ቆይታውን ቀጥሎ ያደረገው አውደ ርዕዩ አሁን የመጨረሻና የማጠቃለያ ጉዞውን ለማድረግ ወደ አዲስ አበባ አቅንቷል።
ከጥቅምት 2 - 6/2016 በበቃና ስቱዲዮ በ15 የፎቶግራፍ ባለሙያዎች የተዘጋጁት የፎቶግራፍ ስብስቦች የሚቀርቡ ሲሆን ከአውደርዕዩ ባለፈ ነጻ የፎቶግራፍ ስልጠናን ጨምሮ የጥይቄና መልስ ግዜዎች ከፎቶግራፍ ባለሙያዎቹ ጋር ተዘጋጅተዋል።
በተዘረሩት ቀናት ላይ በፎቶ አውደርዕዩ ላይ በመገኘት የዘወትሯን ኢትዮጵያ አብረውን ይቃኙ! ኑ! የአንድነታችንን ውበት በጋራ እናድንቅ!
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ በአዲስ አበባ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማህበር (አአፎባማ) ከUSAID እና ግራር፣ የጠቢባን መናኸርያ ጋር በመተባበር በሚካኤል ጸጋዬ ዋና አዘጋጅነት የቀረበ ነው።
https://linktr.ee/everydayethiopia

#ደራ
በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጭ ብሎ የሚጠራው መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የሚለው በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ አደረሱት በተባለ ጥቃት በርካታ ንጹሐን ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የዓይን እማኞች ገልጸዋል።
ለደኅንነቴ ሲባል ሥሜ አይጠቀስ ያሉ የደራ ወረዳ ነዋሪና ባላቸው መረጃ ብቻ፣ ታጣቂ ቡድኑ ከመስከረም 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በከፈተው የተኩስ ጥቃት ተገድለዋል፣ ቆስለዋልና ታግተዋል ያሏቸውን ከ50 በላይ ሰዎች ሥም ዝርዝር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።
እኚሁ ነዋሪ በገለጹት መሠረት፣ ይህ ቁጥር እርሳቸው የሚያቋቸው ሰዎች ብቻ እንጅ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ200 እንደሚልቅ፣ ባሳለፍነው ሳምንት የቅዱስ ገብርኤል እና የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያናት መቃጠላቸውን አስረድተዋል።
" ህዝቡ አሁንም ስደት ላይ ነው በዱር ጫካ እያደረ ነው ። ከ1,000 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል። ከ200 በላይ ንፁሃን በዘራቸው ምክንያት ተገለድለዋል። አሁንም እየተገደሉ ነው " ብለዋል።
በተጨማሪም፣ " ከትላንት በስቲያ (መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ስምንት መኪና ሙሉ ሰዎች አግተው ወስደዋል " ያሉት የአካባቢው ነዋሪ፣ " ትላንት ደግሞ (መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም) አንድ መኪና ህዝብ አግተዋል እያንዳንዱ ከ500ሺሕ እስከ 2 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል" ሲሉ አክለዋል።
ታጣቂ ቡድን ተኩስ የከፈተባቸውና ንጹሐን ተገደሉባቸው፣ ቤት ተቃጠለባቸው የተባሉት ቀበሌዎችን እንዲገልጹ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረብላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነዋሪዎቹ፣ ዴኘ፣ ቆሮ ጉንዶ በርበሬ፣ ሰለልኩላ፣ ሳላይሽ፣ ሰለልኩላ በሚባሉ ቀበሌዎችና ከተሞች መሆኑን ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ ያነጋገራቸው የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች በበኩላቸው፣ በደራ ወረዳ የአማራ ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ብለው የሚሞግቱ የኦሮሞ ተወላጆችም እስርና ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው ብለዋል።
ሌላኛው ሥሜ ባይጠቀስ ያሉ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ በሰጡት ቃል፣ " የፋኖ ታጣቂዎችም በርካታ ቁጥራቸው ገና በትክክል ያልታወቀ ሰዎችን ገድለዋል " ብለዋል።
የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሺበሺ አያሌው እየደረሰ ነው ለተባለው ጥቃት ምን ምላሽ እንዳላቸው ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ " በወረዳዋ የሚገኘው የጸጥታ ሃይል በቂ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።
አስተዳዳሪው፣ " የሽብር ቡድኑ ንፁሃን ላይ ጥቃት ከፍቷል በ8 ቀበሌዎች በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም አረጋግጠዉልናል" ሲል ዘግቧል ጣቢያው።
ከዚህ በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ያላቸውን ምላሽ ለማካተት ለሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ያደረገው ሙከራ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም።
ይሁን እንጅ የኦነግ ሸኔ፣ የፋኖ ታጣቂዎችም ሆኑ የወረዳውና የዞኑ ባለስልጣናት ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ የምናስተናግድ ይሆናል።
መረጃው በአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።