ቪድዮ ፦ በጀርመን ፤ #ስቱትጋርት ከተማ ቅዳሜ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ሁከቱ የተፈጠረው የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች በከተማዋ የባሕል ፌስቲቫል ማዘጋጀታቸውን ተከትሎ ተቃዋሚዎች ሥነ-ስርዓቱን ለማወክ ሁከት ከፈጠሩ በኋላ ነው።
ተቃዋሚዎቹ በጀርመን ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት አድርሰው በአጠቃላይ 26 የፖሊስ አባላት የተጎዱ ሲሆን ከ6 የማያንሱ አባላት ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
የስቱትጋርት ከተማ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ወደ ስፍራው የተሰማራው ፖሊስ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያልጠበቀው ከባድ አመጽ አጋጥሞታል ብለዋል።
ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ተቃዋሚዎቹ ፦
- በዱላ፣
- በሚስማር፣
- በብረት፣
- በጠርሙስ እና በድንጋይ የጀርመን ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
ሁከቱን ተከትሎ 228 ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተገለጸ ሲሆን በሁከቱ ምን ያክል ኤርትራውያን ጉዳት እንደደረሰባቸው እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በእስራኤል መዲና ቴል አቪቭ መሰል ሁከት ተከስቶ የአገሪቱን መንግሥት ማስቆጣቱና ጠ/ ሚንስትር ኔታኒያሁ አፍሪካውያን ስደተኞች በሙሉ " በአስቸኳይ " ከእስራኤል ምድር ለማባረር የሚያስችል እቅድ እንዲወጣ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል።
Via BBC
Video - Social Media
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ነገ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ በይፋ ይጀምራል። ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ከነገ ጀምሮ በከተማው ውስጥ በሚገኙት ሁሉም የትምህርት ተቋማት የ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ የሚጀምር ይሆናል። ነገ ለሚጀምረው ትምህርት በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙት የትምህርት ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም…
ፎቶ ፦ የ2016 ዓ/ም ትምህርት ዘመን መደበኛ ትምህርት በአዲስ አበባ ዛሬ ተጀምራል፡፡
መደበኛው ትምህርት በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡
በትምህርት ማስጀመሪያ መርሐግብሩ የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች መሰጠቱንም ቢሮው ገልጿል፡፡
#AAEB
@tikvahuniversity

#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት / ባለስልጣናት " ማን ይነካኛል " የሚል የአምባገነን ባህሪ የተላበሱ አሉ ሲል ገለፀ።
አንዳንድ የፌዴራል ተቋማት፣ የክልል ቢሮ የስራ ኃላፊዎች የተወሰኑ የከተማ አስተዳደሮች ከህዝቡ የሚቀርቡ አስተዳደራዊ በደሎችን ለመስማት እንኳን ፍቃደኛ የማይሆኑ መኖራቸውን አመልክቷል።
ከፌዴራል ተቋማት የሚበዙት መስሪያ ቤቶች የዕንባ ጠባቂ ተቋሙ የሚሰጣቸውን ጥቆማ እና ምክረ ሃሳቦች የሚቀበሉ ቢሆንም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተባባሪ አለመሆኑ ተገልጿል።
" የፌዴራል ተቋማት ላይ ሙሉ በሙሉ የተሻለ ነው " ያለው ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ፤ ይህ አንድም አቻ ተቋማት በመሆናቸው ከዚህ ባለፈ የግንዛቤ ደረጃው የተሻለ ስለሆነ መሆኑ ገልጿል።
ከፌዴራል ተቋማት ውስጥ በተለይ የፌዴራል ፖሊስ እና ጉምሩክ ኮሚሽን ምክረ ሃሳቦችን ያለመቀበል ፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመፈፀም ያለመተባበር ነገር እንዳለ አመልክቷል።
ከፌዴራል ፖሊስ ይልቅ የጉምሩክ ኮሚሽን የተቋሙን ምክረሃሳቦች በመቀበል ረገድ የተሻለ እንደሆነ ገልጿል።
የዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤ የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ " አንድ አባል 7 ዓመት ካገለገለ በኃላ ስራ መልቀቅ እንደሚችል በሚያዘው የራሳቸው ደንብ መሰረት ወጥትነት ያለው ስራ አይሰሩም ለግማሹ መልቀቂያ ይሰጣሉ ለግማሹ አይሰጡም ፤ ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ነው የሚሰሩት " ብሏል።
ይህ ለተቋሙ ከሚደርሱ ኬዞች መካከል አንዱ እንደሆነ ገልጿል። የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ወይ ደንባቸውን ያሻሽሉ አልያም ደንቡን መሰረት አድርገው መስራት ይኖርባቸዋል ብሏል።
ከተቋሙ ለሚሰጣቸውን የመፍትሄ ሃሳብ ባለመተባበራቸው ጉዳዩን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን ገልጿል።
በክልል ደረጃ መፈረጅ ባይቻልም ያለው ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል ያለድ ተቋሙ ለአብነት ሲዳማ ክልል ይርጋለም ከተማ አስተዳደር ቅንነት የሚጎላቸው ናቸው ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በተመሳሳይ ቅንነት የጎደላቸው ናቸው ብሏል።
በአማራ ክልል አብዛኛው ከተሞች የተሻለ ነገር ቢኖራቸውም ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተባባሪ አይደለም ሲል ገልጿል።
ኦሮሚያ ክልል አዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የመተባበር ችግር እንዳለባቸው ጠቁሟል። ሌሎቹ ከሁለቱ በተሻለ እንደሚተባበሩ ገልጿል።
በአጠቃላይ በክልል ደረጃ ጎራ ከፍሎ መመደብ ባይቻልም ፤ ተቋሙ የሚሰጣቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች የማይተገብሩ እንዳሉ ተመላክቷል።
አንዳንዶቹ አስፈፃሚዎች / ባለስልጣናት ትብብር የማያደርጉት እና የመፍትሄ ሃሳብ የማይቀበሉት " ማን ይነካኛል " በሚል የአምባገነናዊ ባህሪ ነው ያለው የህዝብ ዕንባ ጠባቂ " ይህም ነው ከቦታ ቦታው ልዩነት የፈጠረው " ሲል ገልጿል።
" የግንዛቤ ችግር ነው ብሎ መውሰድ አይቻልም " ያለው የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም " የቅንነት ችግር አለ፣ አንዳንድ የመንግሥት አስፈፃሚዎች በሹመት የሆነ ቦታ ላይ ሲቀመጡ ህብረተሰቡን ማገልገል እንዳለባቸው ማወቅ ሲገባቸው እራሳቸውን እንደ ልዩ ፍጡር አድርገው የሚያስቡ ዜጎችን በአግባቡ የማያስተናግዱ፣ የሚያጉላሉ አካላት አሉ ይህ ከግንዛቤ ችግር ሳይሆን ካላቸው አምባገነናዊ ባህሪ የተነሳ ነው " ሲል አሳውቋል።
በአንፃሩ ህዝብን በቅንነት የሚያገለግሉ እንዳሉ ጠቁሟል።
ባለፈው ዓመት ብቻ ተቋሙ ከ200,000 በላይ ሰዎች አቤቱታ የቀረበለት ሲሆን ይህ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነና ቁጥሩ እንዲህ ከፍ ያለው " ከተሞችን ለማልማት " በሚል የሚፈናቀሉ ሰዎች መብዛታቸው አንዱ መንስኤ ነው ተብሏል።
መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ነው።

#ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት / ባለስልጣናት " ማን ይነካኛል " የሚል የአምባገነን ባህሪ የተላበሱ አሉ ሲል ገለፀ። አንዳንድ የፌዴራል ተቋማት፣ የክልል ቢሮ የስራ ኃላፊዎች የተወሰኑ የከተማ አስተዳደሮች ከህዝቡ የሚቀርቡ አስተዳደራዊ በደሎችን ለመስማት እንኳን ፍቃደኛ የማይሆኑ መኖራቸውን አመልክቷል። ከፌዴራል ተቋማት የሚበዙት…
" እራሳቸውን እንደ ልዩ ፍጡር አድርገው የሚያስቡ የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት አሉ " - ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሚሰጣቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ፣ ምክረሃሳቦች ለመቀባል ስለማይፈልጉ አካላት እንዲሁም ለተቋሙ ትብብር ስለማያደረጉ አካላት የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ለሸገር ኤፍ ኤም ከተናገሩት ፦
" አንዳንድ የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት ' ማን ይነካኛል ' የሚል አይነት የአምባገነን ባህሪ ያላቸው አሉ።
...የቅንነት ችግር አለ ፤ ሁለተኛ አንድ የመንግሥት አስፈፃሚ አካል ወደ ሹመት የሆነ ቦታ ላይ ሲመጣ ህብረተሰቡን ነው የሚያገለግለው፤ ህብረተሰቡን የማገልገል ኃላፊነት አለብኝ ብለው የሚያስቡ እንዳሉ ሁሉ የማያስቡም አሉ።
ልክ እራሳቸውን እንደ ልዩ ፍጡር አድርገው የሚያስቡ ፣ ዜጎችን በአግባቡ የማያስተናግዱ፣ የሚያጉላሉ የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት አሉ። "

Photo
#ኢትዮጵያ #ባሌ
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባባሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና እና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በተካሄደው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የዓለም ቅርስ ጉባኤ ላይ የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በአለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተመዘገበው በኢትዮጰያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው።
በትላንትናው ዕለት የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር #በዓለም_ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።
#የቱሪዝም_ሚኒስቴር

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሎጎ (ንግድ ምልክት) መግለጫዎች፡-
👉 የበር ምልክት (Possibility, Destination) በይቻላል መንፈስ ወደ ታላቁ የስኬት ጫፍ መድረስን ፤ በህይወት የለውጥ ውህደት ውስጥ የምንደርስበትን ጫፍ ማሳያ ነው፡፡
👉 የቁልፍ ምልክት (Success and Opportunity) በታማኝነት በመስራት እድልን ወደ ስኬት በመቀየር የገንዘብዎ/የስራዎ ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን አመላካች ነው፡፡
👉 የእንግሊዝኛው ፊደል G እና B Global BANK የሚለውን ስያሜ የመጀመሪያ ፊደላት ይወክላሉ፡፡
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

A_HRC_54_55_AdvanceUneditedVersion.docx
79.2 KB
#ETHIOPIA #UN
ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት እንዲቆም ስምምነት ከተፈረመ አንድ አመት ሊሞላው ቢቃረብም አሁንም ግፍ፣ የጦር ወንጀሎች እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ነው ሲል በተመድ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አሳወቀ።
ኮሚሽኑ የሰላሙ ሁኔታ አሁንም ያልተረጋገጠ መሆኑን ጠቁሟል።
ኮሚሽኑ ባወጣው ባለ 21 ገጽ ሪፖርቱ ከህዳር 3 ቀን 2020 ጀምሮ በግጭቱ ውስጥ በተሳተፉ #ሁሉም_አካላት የተፈፀሙ መጠነ ሰፊ አሰቃቂ ድርጊቶችን አስፍሯል።
ከእነዚህም ውስጥ ፦
- የጅምላ ግድያ፣
- አስገድዶ መድፈር፣
- ረሃብ፣
- የትምህርት ቤቶች እና የህክምና ተቋማት ውድመት፣
- የግዳጅ / በኃይል ማፈናቀል እና የዘፈቀደ እስራት ይገኙበታል።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሀመድ ቻንዴ ኦትማን ፤ " የሰላም ስምምነቱ መፈረሙ በአብዛኛው የመሳሪያ ድምፅ ጸጥ ያሰኘው ቢሆንም ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በትግራይ ያለውን ግጭት አልፈታም ወይም ምንም አይነት አጠቃላይ የተሟላ ሰላም አላመጣም " ብለዋል።
" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
በአማራ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርስ የመብት ጥሰት እና በትግራይ እየተፈጸመ ያለ ግፍን የሚገልጹ ሪፖርቶች እንዳሉት ኮሚሽኑ አሳውቋል።
ኮሚሽኑ ያፋ ባደረገው ሪፖርት፤ የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ጥሰቶችን መፈፀም መቀጠላቸውን አመልክቷል። ይህም ስልታዊ የሆኑ አስገድዶ መድፈር፣ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃቶችን እንደሚያካትት አመልክቷል።
ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት ሃይሎች ይፈፀማል ስላለው የሰላማዊ ዜጎች እስራት እና የማሰቃየት ድርጊትን በተመለከተ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።
በተጨማሪም ፤ በቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ተወላጅ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያሳዩ በርካታ ሪፖርቶችን እንዳገኘ አሳውቋል።
ኮሚሽኑ ፤ የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ እና ለጭካኔ ወንጀሎች የሚያጋልጡ ሁኔታዎች መኖራቸው በእጅጉ እንደሚያሳስበው አመልክቷል።
ይህ ሁኔት በኢትዮጵያ እንዲሁም በሰፊው ቀጣና መረጋጋት ላይ እንዲሁም በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ህፃናት ላይ እንድምታ እንዳለው ገልጿል።
https://www.ohchr.org/en/press-releases/2023/09/ethiopia-nearly-one-year-after-ceasefire-un-experts-warn-ongoing-atrocities
(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

#ትግራይ
የመስቀል በዓል " ለሰላም ለመልሶ ግንባታ ስነ-ልቦናዊ ማገገም " በሚል መሪ ቃል በመላ ትግራይ በድምቀት እንደሚከበር የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል።
ቢሮው የ2016 ዓ.ም የመስቀል በዓል አከባበር የሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ለሚድያዎች ሰጥቷል።
የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ.ር ኣፅብሃ ገ/እግዚአብሔር ፤ በዓሉ ኮሮና ተከትሎ በትግራይ በተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ላለፉት ሶስት አራት አመታት በአደባባይ እንዳልተከበረ አውስተዋል።
" የመስቀል በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ በዓል ነው " ያሉት ዶ/ር አፅብሃ ፤ " በዓሉ የቆየ ትውፊትና ሃይማኖት በጠበቀ መልኩ ከማክበር በዘለለ ፣ በደም አፋሳሹ ጦርነት የተጎዳ የህዝብ ስነ-ልቦና በሚታከምበትና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የሚያስታውሱ መልእክቶች በማስተላልፍ ጭምር ይከበራል " ብለዋል።
በዓሉ በመላ ትግራይ ይከበራል ያሉት የቢሮ ሃላፊው ፤ በተለይ በመቐለ በዓዲግራትና ከኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ነፃ በሆኑ የኢሮብ ቀበሌዎች ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስነ-ሰርአቶች በሚያንፀባርቅ ልዩ ድምቀት እንደሚከበር ገልፀዋል።
በዓሉን ለማድመቅ እስከ መስከረም 16 / 2016 ዓ.ም የሚዘልቁ በመቐለና ዓዲግራት ዘመናዊና ባህላዊ የስፓርት ወድድሮች እንዲሁም የክልሉ የቱሪዝምና የባህል ፀጋዎች ማልማት ፣ መጠበቅ ፣ ጦርነቱ ከካደረሰባቸው ውድመት መልሶ መገንባት ያተኮረ የፓነል ውይይት በማካሄድ መስከረም 17 በሚካሄደው የደመራ ማብራት ስነ-ሰርአት እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ነው።