#Irreecha2016
አባ ገዳዎች እና ሃዳ ሲንቄዎች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫው የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አንድነትንና ሕብረትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል ብለዋል።
የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27/2016 ዓ.ም በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ እንደሚከበር ይፋ አድርገዋል።
የቱለማ አባገዳና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ፀሓፊ አባገዳ ጎበና ሆላ ፤ " የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት እሴትን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል " ሲሉ ገልጸዋል።
'' ኢሬቻ እርቅና ሰላም በመሆኑ የዘንድሮው ኢሬቻ በደስታ፣ በአንድነትና በፍቅር ይከበራል '' ብለዋል።
የሲኮ መንዶ አባገዳና የህብረቱ አባል አባ ገዳ አሊይ መሐመድ ሱሩር ፤ " ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት በመሆን በዓሉን ማክበር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ቄሮዎች፣ ቀሬዎችና ፎሌዎች ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የበኩላቸውን እንዲዉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሃዳ ሲንቄ አፀዱ ቶላ በበኩላቸው ፤ '' ኢሬቻ ሰላም መሆኑንና የሰላም እናት መሆናችንን በአንድነት የምናሳይበት በዓል ነው '' ብለዋል።
'' ኢሬቻ የይቅርታ፣ የተጣለ የሚታረቅበት፣ የተለያዩ የሚገናኙበትና ፈጣሪ የሚመሰገንበት በዓል ነው '' ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም " በዓሉ ያለምንም ችግር እንዲከበር፣ በሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር እንዲፀና ሃዳ ሲንቄዎች በትብብር ይሰራሉ " ብለዋል።
ሃዳ ሲንቄ ጫሊ ቱምሳ ፤ " ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ማንነት መገለጫ በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ መከበር አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
ወጣቶችና ሴቶች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በዓሉ ያማረና የተሳካ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ኢዜአ / ፋይል
@tikvahethiopia

#ኢትዮጵያ #ጌዴኦ
በሳውዲ አረቢያ ፤ ሪያድ 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ስብሰባው ፤ በኢትዮጵያ የቀረበው የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር ፋይል በኮንቬሽኑ መሰረት መርምሮ #በዓለም_ቅርስነት እንዲመዘገብ በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን የቱሪዝም ሚኒስቴር አሳውቋል።
ይህም በኢትዮጵያ የተመዘገቡት የባህልና ተፈጥሮ ቅርሶች ወደ 10 እንዲያድጉ አድርጓል ፤ ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር ፋይል ምዝገባ ከኮንሶ ከተመዘገበ ከ12 አመት ( እ.ኤ.አ ከ2011) በኃላ በዓለም ቅርስነት የተመዘበ ነው።
#ቱሪዝም_ሚኒስቴር

TIKVAH-ETHIOPIA
" ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 /01/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ። ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።…
#AddisAbaba
ነገ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ በይፋ ይጀምራል።
ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ከነገ ጀምሮ በከተማው ውስጥ በሚገኙት ሁሉም የትምህርት ተቋማት የ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ የሚጀምር ይሆናል።
ነገ ለሚጀምረው ትምህርት በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙት የትምህርት ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት በቂ የሆነ ዝግጅት አድርገው የተማሪዎችን ለዓመቱ ትምህርት መገኘት ብቻ እየጠበቁ ይገኛሉ ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ ለ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ዝግጅት በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶችን የማደስ፣ ግብዓቶችን የማሟላት ፣ ከአጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ ጋር የመምከር ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።
በነገው ዕለት በከተማዋ ትምህርት የሚጀምረው #በሁሉም የትምህርት ተቋማት ውስጥ ነው።

#GudafTsegay🇪🇹
የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ሪከርድ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።
በዩጂን በተደረገ የ " ዳይመንድ ሊግ " ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የ5,000ሜ የዓለም ሪከርድን በመስበር አሸንፋለች።
14:00.21 በሆነ ሰዓት የገባችው ጉዳፍ ፀጋይ የዓለም ሪከርዱን ከኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን በመንጠቅ ሪከርዱን የግሏ ማድረግ ችላለች።
" ትኩረቴ የነበረው የዓለም ሪከርዱን መስበር ነበር " ያለችው ጉዳፍ በተመዘገበው ድል በጣም ደስተኛ መሆኗን እና በቀጣይ ከአስራ አራት ደቂቃ በታች ለመግባት እንደምትጥር ከድሉ በኋላ ተናግራለች።
ጉዳፍ ያሸነፈችበትን ውድድር ቪድዮ " X " ላይ መመልከት ይቻላል 👇
https://twitter.com/tikvahethiopia/status/1703549856315240553?t=Pmq3yq4O_vIS4WWyatvJGw&s=19
Video Credit - Lynne Wachira / RTS TV
Via @tikvahethsport

Jasiri Talent Investor Programme - Cohort 5 provides you
with comprehensive ecosystem support! 🌍 Tap into our vast network
of partner organizations, startup communities, and resources.
Leverage the collective power of the ecosystem to build a successful venture. Apply now at jasiri.org/application
ecosystem! #StartupEcosystem #Cohort5 #EntrepreneurSupport.