TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ 13 አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ሐምሌ…
#መቐለ
በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑካን ቡድን መቐለ ገብቷል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለክልል ትግራይ የሰብዐዊ ድጋፍ እንዲደረግና ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በትግራይ ክልል ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር የሰላም ውይይት እንዲያደረጉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።
በዚህ መሰረት የልዑካን ቡድን ዛሬ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ ገብቷል።
@tikvahethiopia

#መቐለ በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑካን ቡድን መቐለ ገብቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለክልል ትግራይ የሰብዐዊ ድጋፍ እንዲደረግና ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በትግራይ ክልል ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር የሰላም ውይይት እንዲያደረጉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። በዚህ መሰረት የልዑካን ቡድን ዛሬ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ ገብቷል። @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ተገናኝተዋል።
Credit : EOTC TV
@tikvahethiopia
Credit : EOTC TV
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ተገናኝተዋል። Credit : EOTC TV @tikvahethiopia
ልዑካን ቡድኑ በመቐለ የሚኖረው ቆይታ ምን ይመስላል ?
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ልኡክ ዛሬ ጥዋት መቐለ ገብቷል።
ቆይታው ለሁለት ቀን ይሆናል።
ለልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ አቀባበል ተደርጓል።
ቀጥሎ በመቐለ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ፀሎት ይከናወናል።
በመቀጠል ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በመጓዝ ከሲኖዶስ የተላከ ሰብአዊ እርዳታ ካስረከቡ በኋላ አጭር ውይይት ይካሄዳል።
ውይይቱ በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ እና የትግራይ አብያተ ክርስትያናት አባቶች አንድነት መቀጠልና ማጠናከር ላይ ያተኩራል።
ከውይይቱ በኋላ በጦትነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች በተጠለሉበት በተለምዶ በመቐለ 70 ካሬ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ጉብኝት ይካሄዳል።
ጉብኝቱ ተፈናቃዮቹ በቀጣይ እንዲቋቋሙ የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን አስተዋፅኦ ምን መሆን እንዳለበት የሚያመላክት ሆኖ አጭር ቡራኬና መግለጫ በቅዱስ ፓትርያርኩ ይቀርባል።
ቀጥሎ ከትግራይ ብፁአን አበውና የኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስተያን አመራሮች ግንኙነትና ውይይት ይካሄዳል።
በቦታው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሃይማኖታዊ አስተምህሮና ምክር ይሰጣል።
የዛሬ የሰኞ ሃምሌ 3 /2015 ዓ.ም ጉብኝት ማጠቃለያ በዚህ ይሆናል።
ነገ ማክሰኞ ሃምሌ 4 /2015 ዓ.ም ጥዋት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጉብኝቱ ዓላማና ቆይታ የሚመለከት ለጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ለብፁአን አበው መግለጫ ያቀርባሉ።
መግለጫው ተከትሎ ውይይት ከተካሄደ በኋላ ጉብኝቱ ይጠናቀቃል።
ከጉብኝቱ ማጠቃለያ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራው ልኡክ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሽኝት ይደረግለታል።
መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ አባል ነው።

#MoE አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ መሰረትም ፦ - ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣ - የተማሪዎች ምረቃ…
" . . . ሁሉም ለምረቃ ብቁ የሆነ ዕጩ ተመራቂ ተማሪ በምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፋል " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት
' ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ' በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ።
መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ” የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት (CGPA 2.00>) ያላቸው ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፉ የነበረ መሆኑን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አስታውሷል።
አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ዲግሪ ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸውን እንዲያሟሉ ይጠበቃል ብሏል።
የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ለምዘና ብቁ ሲሆኑ በየሦስት ወሩ መፈተን እንደሚችሉም ህብረቱ ገልጿል።
ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌለው እጩ ምሩቅ በደረጃ ዝቅ ያለ የት/ት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችል በመመሪያ መቀመጡንም አሳውቋል።
ያለገደብ ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌላቸው ዕጩ ምሩቃን በደረጃ ዝቅ ያለ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችሉ በመመሪያ መቀመጡን ህብረቱ የላከልን መግለጫ ያሳያል።
የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት / የወጪ መጋራታቸውን ከፍለው ሲያጠናቅቁ በሚሰጣቸው፤ የወሰዱትን የትምህርት አይነቶች ከነውጤታቸው በሚያሳየው ማስረጃ ላይ መሆኑን ህብረቱ ጠቁሟል።
በሌላ በኩል ዕጩ ተመራቂ ተፈታኞች በመውጫ ፈተና ወቅት ተከታዮቹን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ አሳስቧል።
- የሚፈተኑበትን ኮምፒውተር ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ፈትሸው እንዲጠቀሙ።
- ፈተናውን በሚሰሩበት ወቅት የኮምፒውተር ገመዶች በሰውነታቸውም ሆነ በሌላ ነገሮች እንዳይነኩ እና እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ።
- ወደ መፈተኛ ክፍሎች ሲገቡና እና ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ መመሪያዎችን እንዲያከብሩ።
- ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት ችግሮች ካጋጠሙም ወድያው መፍታት ስለሚቻል እንከን ሲያጋጥማቸው በየመፈተኛ አዳራሹ ለተመደቡ የICT ባለሙያዎች በፍጥነት እንዲያሳውቁ፤
- የሚያጋጥሟቸው የትኛውም ተግዳሮቶች በግቢያቸው ላለው ህብረት በማመልከት ከግቢው አቅም በላይ ከሆነ በሚመለከተው አካል እንዲፈታ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝቧል።
More : @tikvahuniversity

" . . . ሁሉም ለምረቃ ብቁ የሆነ ዕጩ ተመራቂ ተማሪ በምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፋል " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ' ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ' በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ። መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ”…
ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ዕጩ ምሩቃን ላይ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ይህ የመውጫ ፈተና ከቀናት በፊት ለጤና ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የትምህርት መርሀግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዕጩ ምሩቃን ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
የመውጫ ፈተናው እስከ ሐምሌ 8 /2015 ድረስ መሰጠቱን የሚቀጥል ሲሆን የፈተናው ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ምናልባትም ፤ ዕጩ ምሩቃን ይህንን ፈተና ባያልፉ ያለገደብ ደጋግመው ፈተናውን ወውሰድ ይችላሉ።
አሁን ባለው ሁኔታ ትምህርት ሚኒስቴር ይህን ፈተና በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ያቀደ ሲሆን ቀጣዩ ፈተና ጥር / የካቲት ወር ለመስጠት ታስቧል።
ተፈታኞች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል።
በሌላ በኩል ዕጩ ምሩቃን ይህን ፈተና ቢየልፉም ባያልፉም በተቋማቸውን የሴኔት አሰራር መሰረት ለምረቃ ብቁ ሆነው ከተገኙ በምረቃ መርሀግብር ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
ፎቶ ፦ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እና ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተላከ

ልዑካን ቡድኑ በመቐለ የሚኖረው ቆይታ ምን ይመስላል ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ልኡክ ዛሬ ጥዋት መቐለ ገብቷል። ቆይታው ለሁለት ቀን ይሆናል። ለልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ አቀባበል ተደርጓል። ቀጥሎ በመቐለ ቅዱስ ሚካኤል…
#Update
ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ መቐለ ትግራይ ሲደርሱ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካብኔ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ በትግራይ ጊዚያዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በተለያዩ ማህበራትን የማህበረሰብ ወኪሎች እና ወጣት ዘማርያን ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎ በመርኃግብሩ ቢገለጽም በስፍራው የትግራይ ክልል የሃይማኖት አባቶች ፣ ዘማርያን #እንዳልተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በመቀጠል ልዑኩ በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እገዛ የሚውል 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በፕላኔት ሆቴል በተደረገ መርኃግብር ላይ ያስረከበ ሲሆን በትግራይ ያሉ የሃይማኖት አባቶች ግን በሥፍራው አልታደሙም።
ደጋፉን የተቀበሉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከቅድስት ቤተከርስትያንዋ የተበረከተውን ድጋፍ የዘገየ ቢሆንም የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በቅዱስ ሲኖዶሱና በትግራይ አብያተ ክርስትያናት አባቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከተካሄደው ጦርነት ተያይዞ አንዳንድ ጳጳሳት ባደረጉዋቸው ከሃይማኖት ያፈነገጡ ንግግሮች ግንኙነቱ እንዲሻከር ምክንያት መሆኑና፤ ይህን ቅሬታ የፈጠረው አለመግባባት በመመካከር በውይይት ለመፍታት የሚደረገው ጥረት የረፈደ ቢሆንም የሚደገፍ ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ፥ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቤተከርስትያንዋ በጀመረችው ጥረት የወደሙ ቤተእምነቶችን ከመገንባትና የተጎዱ የሃይማኖት አባቶች ከመደገፍ በዘለለ የተፈጠረው መቃቃር እንዲሻር በልዩ ጥንቃቄና ፅናት በመስራት ግንኙቱ ተሻሽሎ ትክክለኛ መንፈሳዊ ሂወት እንዲቀጥል ለማድረግ በሚሰራው ስራ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባሰሙት ቃል በትግራይ የተካሄደው ጦርነት ለማቆም ቅዱስ ሲኖዶሱ በግዜው ድምፁ ባለማሰማቱ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል ፣ ይቅርታው የበለጠ እንዲጠናከር ውይይት እጅግ አሰፈላጊ መሆኑ በመገንዘብ የትግራይ የሃይማኖት አባቶች ተባባሪ እንዲሆኑ አባታዊ ምክር አስተላልፈዋል።
ያለፈው ዘግናኝና አሳፋሪ ጦርነት ለማቆም የትግራይና የፌደራል መንግስት ሃላፊዎች በፕሪቶሪያ የፈረሙት ስምምነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሃይማኖት አባቶች ይህንን ፈለግ ተከትለው በመወያየት መግባባት እና አንድነት መፍጠር ይገባቸዋል ብለዋል።
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በተመራው የሰላም ልዑክ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች ተገኝተዋል።