#ቴክኖ
ካሞን 20 የሰልፊ ካሜራን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ አድርጎታል!
የCamon 20 series 30ሜጋ ፒክስል የፊት ለፊት ካሜራ ከልዩ የኤ.አይ እገዛ እና ሱፐር ናይት ሞድ ጋር በመታገዝ በዝቅተኛ ብርሃን ባለበት ቦታ ውስጥም ቢሆን አስደናቂ የራስ ምስሎችን የማንሳት አቅም ባለቤት ያደርገዋል። ካሞን 20 በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያጋሯቸውን ምስሎች ጎልቶ እና ጠርቶ እንዲታይ የሚያደርግ ብቃት ያለው ልዩ የሰልክ ሞዴል ነው። እያንዳንዱ ፎቶ በ ካሞን 20 ይለያል።
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Camon20Series #TecnoMobile #TecnoEthiopia

#ሳፋሪኮም
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

ኦሮሚያ ባንክ ለ2ኛ ጊዜ የESQR ዓለም-አቀፍ የዳይመንድ የጥራት ልህቀት ተሸለሚ ሆነ።
ESQR በቤልጅዬም ብራሰልስ ሀምሌ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ የ2023 የጥራት ልህቀት ዓለማቀፋ የዳይመንድ ሽልማት ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ መሸለሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ESQR ጥራትን ቀዳሚ ያደረጉ፤ በስራ አፈጻጸማቸው የላቁ ከዓለም አቀፍ የተወጣጡ ስመጥር ቢዝነስ ተቋማት በመሸለም የቀደመ ታሪክ ያለው አንጋፋ ተቋም ነው። ከዚህ ቀደም ይህን አለም አቀፍ ሸልማት በማሸነፍ ከበሬታን ካተረፉ ተቋማት መካካል የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይገኝበታል ።
በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ከ42 ሀገራት የተወጣጡ በተለያዩ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው ስኬታማ የሆኑ 49 የንግድ ተቋማት እውቅና ያገኙ ሲሆን ኦሮሚያ ባንክም በዓለም ዓቀፍ ተፅዕኖአቸው የጎሉ የቢዝነስ ተቋማት ተርታ በመሰለፍ ይህንን ሽልማት ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ መቀዳጀቱ አስታውቋል።
በቤልጅየም ብራሰልስ በመገኘት ሽልማቱን የተቀበሉት የባንኩ ዋና ስራ አሰፈጻሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን ኦሮሚያ ባንክ የ2023 ዓለም-አቀፍ የዳይመንድ የጥራት ልህቀት ተሸለሚ በመሆኑ የተሰማቸውን ክብር እና ደስታ ገልጸው ይህ ስኬት የተገኘው ደንበኞችን ማዕከል ያደረገ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ለሰጠነው ልዩ ትኩረት ነው ብለዋል።
በማከልም ይህ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ለጀመርነው ሁሉን ዓቀፍ ተቋማዊ ለውጥ እና የደንበኞቻችንን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ፍላጎት ዕውን ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ያጠነክራል ብለዋል::
ይህን መሰሉ ዓለማቀፍ ዕውቅና ዘመናዊ እና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ይበልጥ የሚያነሳሳን ሲሆን ለደንበኞቻችን የአገልግሎት እርካታ መረጋገጥ የገባነውን ቃል ኪዳን በትጋት ለመፈጸም ተጨማሪ ጉልበት ይሰጠናል።
የባንኩ ዋና ስራ አሰፈጻሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን አክለውም ለዚህ ስኬት አስትዋዕፆ ላበረከቱ ክቡራን ደንበኞች፤ የስራ አመራር ቦርድ፤ ማኔጅምንት እና መላው የባንካችን ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ማለታቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን አስታውቋል፡፡
አስተዳደሩ ፤ በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል ነው ያስገነዘበው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማውን ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ከዚህ ቀደም የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉን አስታውሷል።

#Update ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ መቐለ ትግራይ ሲደርሱ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካብኔ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ…
#Mekelle
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልኡክ ዛሬ ከሰአት በተለምዶ " መቐለ 70 ካሬ " ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች መጠለያ ጉብኝት አድርጓል።
በጉብኝቱ ተፈናቃዮች " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን በስፍራው የነበሩ የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።
ቅዱስ ፓትሪያርኩ ፤ " በውስጣችሁ የሚሰማችሁን እንኳን ተናገራችሁ " ካሉ በኋላ ፤ " ሰሚ ከተገኘ ወደ ቀያችሁ እንድትመለሱ ለሚመለከተው እንናገራለን " ብለዋል።

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አንድ የሬሜዲያል መርሀግብር ተማሪው በመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉን እና ሌሎች ተማሪዎቹም መጎዳታቸውን አሳወቀ።
" ተማሪ ዮሐንስ ፈቃዱ የተባለ በዩኒቨርሲቲያችን በአቅም ማሻሻያ መርሃ ግብር (Remedial Program) በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቶ ወደቤተሰቦቹ ሲመለስ በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል " ሲል ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው ምንም እንኳን ስለደረሰው አደጋ የት እና ስንት ሰዓት እንደሆነ ባይገልጽም ፥ " በተፈጠረው አሰቃቂ አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ (ለተማሪው) መፅናናትን እንመኛለን " ብሏል።
ሌሎች አደጋ የደረሰባቸው ተማሪዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።
ትላንትና እሁድ ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረ ባስ ተገልብጦ የቦረና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉና ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ የመሩት የሰላም ልዑክ የዛሬ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?
- ቀደም ብሎ በወጣ መርሀ ግብር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልዑክ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ በምዕመናን፣ ዘማርያን፣ በክልሉ ሃይማኖት አባቶች አቀባበል ይደረግለታል ቢባልም በስፍራው ከትግራይ አባቶች ፣ ዘማርያን የተገኘ አልነበረም። የተገኙት የመንግስት አመራሮች ነበሩ።
- በመቀጠል እዛው መቐለ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ፀሎት ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ምዕመናን፣ ካህናት ፣ የትግራይ አባቶች አልተገኙም ነበር። ቅዱስነታቸው እና የመሩት ልዑክ የቤተክርስቲያኑ በር የዘግቶባቸው በር ላይ ፀሎት አድርሰው ለመውጣት ተገደዋል።
- በፕላንቴ ሆቴል በተካሄደ ስነስርዓት ልዑኩ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዚህ ስነስርዓት ላይ የትግራይ አባቶች #አልተገኙም። ተገኝተው የነበሩት የክልሉ መንግስት አመራሮች ነበሩ።
- ልዑኩ በመቀጠል በመቐለ 70 ካሬ ተፈናቃዮችን የተመለከተ ሲሆን በዚህ ወቅትም " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት ተፈናቃዮች በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን ለማወቅ ተችሏል።
- ከመቐለ 70 ካሬ የተፈናቃዮች መልከታ በኃላ የሰላም ልዑኩ ከትግራይ ብፁአን አበውና የኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስተያን አመራሮች ጋር ይገናኛል ውይይትም ያደርጋል የሚል መርሀ ግብር ተይዞ የነበረ ቢሆንም ይህም አልተደረገም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ ብፁዓን አባቶች ከጥዋት አንስቶ በነበሩ መርሀግብሮች ላይ ለምን አልተሳተፉም ? የሚለውን ለመጠየቅ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም።