TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ግድና ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " - የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አንገብጋቢ ባሏቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኮንፌዴሬሽኑን አመራሮች እንዲያነጋግሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ በዘንድሮው የሜይ ዴይ በዓል ላይ በአደባባይ ሊያነሳቸው የነበሩ ጥቄያዎችን…
" እኛ አሁንም የሠራተኞች የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሳይስተካከል ዝም አንልም " - የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ለዓመታት ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 ዝቅተኛ የደመወዝ የሚወስነውን " የደመወዝ ቦርድ " ማቋቋም እንደሚገባ መደንገጉን፣ ይሁን እንጂ ለዝቅተኛ ተከፋዮች የኑሮ ሁኔታን የዋጀ የአከፋፈል ሥርዓት ያስተካክላል ተብሎ ሲጠበቅ ዓመታት ያስቆጠረው " የደመወዝ ቦርድ " የማቋቋም ድንጋጌ፣ አሁንም ጆሮ ዳባ መባሉን የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ገልጸዋል፡፡

ኢሠማኮ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ደጅ ቢጠናም፣ አሁንም የዝቅተኛ ሠራተኞች ጉዳይ ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን አቶ ካሳሁን አስረድተዋል፡፡

ተገቢውን ቅደም ተከተል በመከተል በሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ትኩረት እንዲያገኝ ኢሠማኮ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ባለማግኘቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕልባት እንዲገኝ አቤቱታ ማቅረቡን አክለዋል፡፡  

ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄው መቅረቡን ገልጸው፣ " የሚሰጡትን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው " ብለዋል፡፡

ኢሠማኮ በየዓመቱ በሚከበረው የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) በኑሮ ውድነት ምክንያት በሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መፍትሔ እንዲያገኝና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ምጣኔ እንዲሻሻል፣ በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ሊያቀርብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካለት መቅረቱ ይታወሳል፡፡

በሰላማዊ ሠልፉ ሊነሱ የታሰቡ ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው አካላት ቢቀርቡም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ወደ ሥራ እንዲመለስ ከመፍቀድ በዘለለ ወሳኙ የሠራተኞች የህልውና ጥያቄ መፍትሔ እንዳልተሰጠው ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡

" እኛ አሁንም የሠራተኞች የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሳይስተካከል ዝም አንልም " ያሉት ፕሬዚዳንቱ " ሌሎች ሕጋዊ አማራጮችን በመጠቀም መፍትሔ ለማግኘት እንሠራለን " ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ተካልኝ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም የራሱ የሆነ አሉታዊም አዎንታዊ ጎን አለው ብለዋል፡፡

የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም ከሥራ አጥነትና ከኑሮ ውድነት አኳያ፣ ለሚተላለፈው ኢኮኖሚው መቋቋም ይችላል የሚለውን ጉዳይ ለማየት ጥናት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎ ሚኒስቴር አገር አቀፍ የኢኮኖሚው ሁኔታ ተፅዕኖ መፍጠር አለመፍጠሩን በጥናት ከመለየት በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ግለሰብ ለመኖር የሚያስፈልገው ወርኃዊ ገቢ ጭምር እየታየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

" የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም አሁን ካለው አገራዊ ሁኔታ አንፃር መታየት ስላለበት፣ በድጋሚ ጥናት እየተደረገበት ነው " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንፃር አስቸጋሪና ውስብስብ በመሆኑ፣ ቦርዱን ለማቋቋም እንደገና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወሰንባቸውን አካባቢዎች ለመለየት ዳሰሳ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የደመወዝ ቦርድ ለማቋቋም አሁን ባሉ አገር አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የፖለቲካዊ ሁነቶች አስቻይና ከልካይ ሁኔታዎችን ያማከለ እንዲሆን ያለመ ብሔራዊ የዳሰሳ ጥናት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
በ10 ሴኮንድ በሲቢኢ ብር ከፍያዎን ፈፅመው ነዳጅ ይቅዱ!
=================
እርስዎ ብቻ ወደ ነዳጅ ማደያ ከመምጣትዎ አስቀድመው

• የሲቢኢ ብር አገልግሎትዎ በአግባቡ እንደሚሠራ ያረጋግጡ፣
• ሲቢኢ ብርን መጠቀም ካልጀመሩም ወደ *847# በመደወል፣ ወይም የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ በራስዎ ይመዝገቡ፤ በተጨማሪም
• በሲቢኢ ብር አካውንትዎ በቂ ገንዘብ መኖሩን ያረጋግጡ እንጂ

በ10 ሴኮንድ ብቻ ነዳጅ ቀድተው ይመለሳሉ!

ስለ ሲቢኢ ብር አገልግሎት በቂ መረጃ ለማግኘት ወደ 951 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ!
*****
የሲቢኢ ብር መተ
ግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#ኢትዮጵያ

በሀገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ለ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ፈተና ይቀመጣሉ።

ፈተናው በክልሎች እንዲሁም በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰኔ 26 እና ሰኔ 27 /2015 ዓ/ም እንደሚሰጥ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በዘንድሮው ዓመት በሚሊዮን ሚቆጠሩ ተማሪዎች ፈተናው ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግዙፎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ኦሮሚያ እና አማራ በድምሩ ከ830 ሺህ በናይ (አማራ 347,666 ፤ ኦሮሚያ 484,994) ተማሪዎችን ፈተና ላይ ያስቀምጣሉ።

በደቡብ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ75 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና ላይ የሚቀመጡ ሲሆን በሌሎች ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ በርካታ ሺዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

እንደ ክልል ትምህርት ቢሮዎች መረጃ በአጠቃላይ በመላው ሀገሪቱ ፈተናውን የሚወስዱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ናቸው።

ነገ መሰጠት የሚጀምረው ፈተና ሙሉ ቀን (ጠዋት እና ከሰዓት) እንደሚሰጥ የታወቀ ሲሆን ተፈታኞች እርሳስ፣ ላጲስ እና ማስመሪያ ብቻ ወደ ፈተና ማዕከላት ይዘው መሔድ ይችላሉ።

ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ዲጂታል ሰዓት እንዲሁም ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይዞ በፈተና ማዕከላት መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ወላጆችም ልጆቻችሁ የተከለከሉ ቁሳቁሶችን ይዘው ወደ መፈተኛ ጣቢያ እንዳይሄዱ ክትትል አድርጉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

በቅርብ ቀናት በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ዓርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ/ም ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ እንዲጓዝ ውሳኔ አስተላልፏል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓንሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል።

ወደ መቐለ በሚደረገው ጉዞ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የሰላምና አቀራራቢ ኮሚቴ አባላት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር አብረው ይጓዛሉ።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#ኤክሶደስ

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት፤ አድራሻችን 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0979099909/ 0911039377
  √በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በሀገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ለ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ፈተና ይቀመጣሉ። ፈተናው በክልሎች እንዲሁም በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰኔ 26 እና ሰኔ 27 /2015 ዓ/ም እንደሚሰጥ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በዘንድሮው ዓመት በሚሊዮን ሚቆጠሩ ተማሪዎች ፈተናው ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግዙፎቹ የኢትዮጵያ…
የ8ኛ ክፍል ክልልና ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ ሰኞ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው ለሁለት ቀናት ይሰጣል።

በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች (አ/አ እና ድሬዳዋ) እንዲሁም በክልሎች በሚሰጠው በዘንድሮው ዓመት የ8ኛ ክፍል ፈተና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይፈተናሉ።

ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia
#AddiAbaba

" ነዋሪዎች በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በ54 የመኖሪያ ቤት የሕብረት ስራ ማሕብራት ከ4 ሺህ በላይ የጋራ የመኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት ግንባታ ዛሬ መጀመሩን የአ/አ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

ስራው ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ " የነዋሪው ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ አማራጭ አሰራሮችን እና ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንገኛለን " ብለዋል።

" የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀውን ይህን አማራጭ ተጠቅመው በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ ፤ የቤት ልማት አማራጮች ላይ ትኩረት በማድረግ የከተማውን የቤት ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

ቢሮው ፍላጎት እና አቅሙ ያላቸውን የ20/80 እና የ40/60 ቤት ልማት ኘሮግራም ተመዝጋቢ የነበሩትን በ54 በጋራ ህንፃ ህብረት ስራ ማህበር በማደራጀት ወደስራ ለማስገባት ሲሰራ የቆየውን ስራ አጠናቆ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ እንደተጣለ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ቪድዮ ፦ በፈረንሳይ ሀገር ፤ አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መገደለን ተከትሎ የተቀሰቀሰው አመፅ አሁንም ቀጥሏል።

በዚሁ አመፅ በርካታ ተቋማት ተዘርፈዋል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በታዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የአፕል፣ ዛራ፣ ናይክ የመሳሰሉ ትልልቅ ድርጅቶች ዘረፋ ሲፈፀምባቸው ታይቷል።

በተጨማሪም በማርሴ ከተማ አንድ  የ " ቮልስ ዋገን " ተሽከርካሪ መሸጫ በአመፀኞች ሲዘረፍ ታይቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ፤ የመኪና መሸጫ ውስጥ የገቡ አመፀኞች አዳዲስ መኪናዎችን እያሽከረከሩ ሲወጡ ይታያል።

ከዚህ ባለፈ በፈረንሳይ አመፀኞች የቤት አስቤዛ በሚሸጥባቸው መደብሮች እየገቡ ዘይትን እና ሌሎች አስቤዛዎችን ዘርፈው ሲወጡ ታይተዋል።

የፈረንሳይ መንግሥት ፤ በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ ለመቆጣጠር እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል አሰማርቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኦሮሚያ ክልል፣ " አሊ ዶሮ " ላይ ከታገቱት ሹፌሮች እና ረዳቶች መካከል በአጋቾች የተጠየቀውን ብር ከፍለው የተለቀቁ ስለመኖራቸው ቪኦኤ ሬድዮ ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ቃላቸውን የሰጡ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን 1 ሚሊዮን ብር ከፍለው ከእገታው እንዳስለቀቁ አመልክተዋል። ከታገቱት አሽከርካሪዎች ውስጥ ሰባቱ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ዐማኑኤል ከተማ ወጣቶች እንደሆኑ…
ልጃቸውን ከእገታ ለማስለቀቅ አንድ ሚሊዮን ብር የተጠየቁት መምህር ብዙ ዋጋ ከፍለው ልጃቸውን በህይወት አግኝተውታል።

ቅዳሜ ሰኔ 10/2015 ወደ ጎጃም ሲሄዱ ከታገቱት ወደ 30 ሹፌሮችና ረዳቶች መካከል አንደኛው የአማኑኤል ከተማው መምህር  አንለይ መኩሪያ ልጅ ነው።

መምህሩ ለልጃቸው የተጠየቁት አንድ ሚሊዮን ብር ነው።

ይህን ያህል ገንዘብ በ40 ዓመታት የማስተማር ስራቸው አግኝተው እና ኖሯቸው እንደማያውቅ ፤ በደሞዝ በቀጥታ እጃቸው የገባው ገንዘብ ቢታሰብም አንድ ሚሊዮን ሊደርስ ስለመቻሉ እርግጠኛ አይደሉም።

አይደለም አንድ ሚሊዮን ብር ሊኖራቸው እሳቸውን እራሱ የሚደጉመው ይኸው የታገተባቸው ልጃቸው ነው።

ግን ልጅ ነውና ከዚህ የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ መከፈል ያለበት ዋጋ መከፈል ስለነበረበት ልጃቸውን ለማስለቀቅ በአጋቾ የተጠየቁትን ገንዘብ ማፈላለግ ጀመሩ።

ከተጠየቀው የማስለቀቂያ ገንዘብ ውስጥ እዚህ ግባ የሚባል ብር እጃቸው ላይ የሌላቸው መምህር አንለይ በእርዳታ መቶ ሺህ ብር ብቻ አገኙ ፤ ቀሪው 900 ሺህ ብር ለማግኘትና የልጃቸውን ሕይወት ለመታደግ ሲሉ ዕዳ ውስጥ ገቡ።

ጎረቤቶቻቸው ከልጅ የሚበልጥ ነገር የለም ብለው ቤታቸውንም ቢሆን ሽጠው እንደሚከፍሉ በመግለፅ 1 ሚሊዮን ብር አሰባስበው ሞሉላቸው።

አጋቾቹ ብሩን በባንክ አንቀበልም በማለታቸው ብሩን ተሸክመው ከአማኑኤል ተነስተው አጋቾቹ ወደ ነገሯቸው የመቀበያ ስፍራ  ፤ እገታው ከተፈፀመበት አቅራቢያ ገብረ ጉራቻ ይዘው ሄዱ።

ገንዘቡን በማዳበሪያ የተሸከሙት መምህር ፤ ገርበ ጉራቻ ከደረሱ በኋላ አስተርጓሚ ቀጥረው ከከተማው 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ቦታ ተጓዙ።

ከዚያች ቦታ እንደደረሱ አንድ ግለሰብ ሲጠብቃቸው አገኙ። ለአጋች ነኝ ላለው ሰው ሲደውሉ ብሩን የሚቀበለው ይህ ግለሰብ መሆኑን ነገራቸው።

ይህ ሲሆን ግን ልጃቸው የት እንዳለ አያውቁም። ተስፋ ያደረጉት ብሩን እንደሰጡት ልጃቸው በዚያው አቅራቢያ እንደሚለቀቅላቸው የነበረ ቢሆንም ከአጋቾች የተሰጣቸው መልስ የሰጣቸው መልስ  ፦

" ገንዘቡን ፈትተን አሳይተን አስረከብነው። ብሩ ከሰባት ሰዓት ጉዞ በኋላ ዋናዎቹ አጋቾች ጋር ይደርሳል። ከዚያ በኋላ ብሩ ተቆጥሮ አድሮ ሙሉ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ይነገርሃል "  ብለው ሸኙኝ "  የሚል ነበር።

በማግስቱ ግን ልጃቸው ተለቆ በአካል አገኙት።

መምህሩ ፤ " በአንድ ሚሊዮን ብር ነፍሱን የገዛሁት ልጄ፣ ረጅም ርቀት የተጓዘበት ጫማው ተቀዶ እና እግሮቹ አባብጠው ሳገኘው እንደገና እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ። የአገሩ ሰው እስኪገረም ድረስ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ "  ሲሉ ተናግረዋል።

መምህር አንለይ እና የሌሎች ታጋች ቤተሰቦች በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ከአጋቾቹ ጋር ስለሚያደርጉት ግንኙነት ሆነ ስለተጠየቁት ገንዘብ ለማሳወቅ ከፀጥታ አካላት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አላደረጉም።

ለዚህም አንደኛው ምክንያት ፖሊስ በጉዳዩ ውስጥ ከገባ ታጋቾቹ በታጣቂዎቹ ሊገደሉ ይችላሉ የሚል ሲሆን ሌላኛው ጉዳዩ አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው በመሆኑ ከመንግሥት ኃይሎች የተሰወረ ነው ብለው ባለማመናቸው ነው።

" መንግሥት እና ሕግ ባለበት አገር የአሁኑን በእዚህ ሁኔታ ፈታነው። " ያሉት መምህር አንለይ " ቀጣይስ? ልጄ ድጋሚ ላለመታገቱ ምን ዋስትና አለኝ ? ሥራ አቁም እንዳልለው አቅም የለኝም። እንዲያውም ከፍተኛው ስጋቴ የወደፊቱ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በነገራችን ላይ ይህ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ነው። በርካቶች ሚዲያ ላይ ያልቀረቡ ታሪኮች ይኖራሉ። ሀገር ሰላም ብለው ከቤት ወጥተው የታገቱና ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ብዙ ናቸው።

የመምህር አንለይ መኩሪያን ታሪክ ያጋራው ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia